ር.ሊ.ጳ ፍራነችስኮስ በመጋቢት 06/2012 ዓ.ም ያደረጉት የብስራተ ገብርኤል ጸሎት!
ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር እንጸልይ
Angelus
Angelus Dómini nuntiávit Mariæ.
Et concépit de Spíritu Sancto.
Ave Maria...
Ecce ancílla Dómini.
Fiat mihi secúndum verbum tuum.
Ave Maria...
Et Verbum caro factum est.
Et habitávit in nobis.
Ave Maria...
Ora pro nobis, sancta Dei génetrix.
Ut digni efficiámur promissiónibus Christi.
Orémus.
Grátiam tuam, quǽsumus, Dómine,
méntibus nostris infunde;
ut qui, Ángelo nuntiánte, Christi Fílii tui incarnatiónem cognóvimus, per passiónem eius et crucem, ad resurrectiónis glóriam perducámur. Per eúndem Christum Dóminum nostrum.
Amen.
Gloria Patri... (ter)
Requiem aeternam...
Benedictio Apostolica seu Papalis
Dominus vobiscum.Et cum spiritu tuo.
Sit nomen Benedicat vos omnipotens Deus,
Pa ter, et Fi lius, et Spiritus Sanctus.
Amen.
የግብርኤል ብሥራት
የእግዚኣብሔር መልአክ ማርያምን አበሰራት
እርሷም በመንፈስ ቅዱስ ጸነስች
ጸጋ የሞላሽ ማርያም ሆይ……
እነሆኝ የእግዚኣብሔር አገልጋይ
እንዳልከኝ ይሁንልኝ
ጸጋ የሞላሽ ማርያም ሆይ……
ቃል ሥጋ ሆነ
በኛም አደረ
ጸጋ የሞላሽ ማርያም ሆይ…….
ቅድስት የአምላክ እናት ሆይ ለምኝልን
ክርስቶስ ለሰጠን ተስፋ የተገባን እንድንሆን
እንጸልይ
እግዚኣብሔር ሆይ በመላኩ ምሥራች የልጅህን የእየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን እንዳወቅን በሕማሙና በመስቀሉ ወደ ትንሣኤ ክብር እንድንደርስ ጸጋህን ስጠን ብለን በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ እንለምንሃለን።
አሜን።
ለአብ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን 3x ጊዜ
ጌታ ሆይ ለሞቱት ሰዎች የዘለዓለምን ዕርፍት ስጣቸው የዘለዓለምን ብርሃን አብራላቸው በሰላም አሳርፋቸው።
የመጨረሻ ቡራኬ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወይም በሌላ
እግዚኣብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን
ከመንፈስህም ጋር
የእግዚኣብሔር ሥም የተመሰገነ ይሁን
ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም
እረዳታችን የክርስቶስ ሥም ነው
እርሱ ሰማይና ምድርን ፈጥሯልና
ሁሉን የሚችል እግዚኣብሔር አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይባርካችሁ።
አሜን።
መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው ጸሎት ምንድነው?
የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።