ፈልግ

እኛ ማነን?

የቫቲካን ዜና አዲሱ የቅድስት መንበር እንቅስቃሴ መረጃ ማሰራጫ መንገድ ነው። ይህም እ.አ.አ. በሰኔ 27/ 2015 ዓ.ም ላይ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ የግል ተነሳሽነት አዲስ በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደር የመገናኛ ብዙዐን ጽሕፈት ቤት እንዲመሰረት ባወጁት አዋጅ መሰረት የተቋቋመ ነው።

የቫቲካን ዜና ቀለል ያሉ የድጂታል መስተጋብር ጽንሰ ሐሳቦችን በመጠቀም ቀጣይነት ባለው መልኩ  በመገናኛ ብዙዐን ዘርፍ የሚታዩትን አዳዲስ ለውጦችን እና የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም በቂ ምላሽ የሚሰጥ የዜና አውታር ነው። የቫቲካን ዜና ብዙ ቋንቋዎችን፣ መድብለ ባህሎችን፣ የተለያዩ ዓይነት የመገናኛ ብዙዐን አውታሮችን፣ የተለያዩ ዓይነት የማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎችን እና የተለያዩ ዓይነት የመገናኛ መሳሪያዎችን የሚጠቀም ነው።

ለመጀመሪያ ጊዜ በስድስት ቋንቋዎች ማለትም  በጣሊያንኛ፣ በእንግሊዘኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በጀርመንኛ፣በእስፓኒሽና በፖርቹጊዝ ቋንቋዎች የተጀመረው ስርጭት ቀስ በቀስ ሥርጭቱን ወደ ሰላሳ ሦስት ቋንቋዎች በማሳደግ እያስተላለፈ ይገኛል። እነዚህን ቋንቋዎችን በመጠቀም አራት ዋና ዋና የዜና ዘርፎች በመጠቀም ሦስቱ በቀጥታ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን፣ የቅድስት መንበርን፣ በተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያንን የሚመለከቱ መረጃዎችን የሚያቀርብ ሲሆን በአራተኛው የዜና ዘርፍ ደግሞ ዓለምን የሚመለከቱ ዜናዎችን ያቀርባል።

ቤተክርስቲያን እያካሄደች የምትገኘውን የተልዕኮ ተግባር በመደገፍ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ወንጌልን የምሕረት ቃል  አሁን ባለው ዘመናዊ ዓለም ባሕል ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ውስጥ ለማስረጽ እያደርገች የምተገኘውን ጥረት መደገፍ የቫቲካን ዜና ዋናው ዓላማ ነው። ለእዚህም ተገባሩ ማስፈጸሚያ የሚሆን የመመሪያ መስፈርት የሚጠቀመው “ሐዋሪያዊ እና ሚስዮናዊ ተገባራት በሙሉ ለየት ባለ መልኩ ለተቸገሩ፣ ድኽ ለሆኑ በችግር ላይ ለሚገኙ ሰዎች ለየት ያለ ትኩረት በመስጠት መካሄ ይኖርባቸዋል” የሐዋርያዊ ተልዕኮ መመሪያ የሚለው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ  እ.አ.አ. በግንቦት 4 ቀን 2017 መመሪያ ነው። አገናኝ መስመር፡ 

ዶ/ር ፓውሎ ሩፊኒ፡ የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙሃን ኤዲቶሪያል የበላይ ጽ/ቤት የበላይ ኃላፊ እና ዶ/ር አንደሬያ ቶርኔሊ ኤዲቶሪያል ዳይሬክተር