ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ልባችን ውስጥ የሚከናወነውን ነገር ለማወቅ አንዴ ቆም ብለን ማሰብ ይኖርብናል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ እንደሚያደርጉ ይታወቃል። በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በኅዳር 02/2016 ዓ.ም ባደርጉት አስተንትኖ ልባችን ውስጥ እየተከናወነ የሚገኘውን ነገር በሚገባ ለመረዳት ቆም ብለን ማሰብ ይኖርብናል ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

የዛሬው ቅዱስ ወንጌል የእያንዳንዱን ሰው የሕይወት ትርጉም በተመለከተ ታሪክ ይሰጠናል። ሙሽራውን ለመቀበል እንዲወጡ የተጠሩት የአሥሩ ደናግል ምሳሌ ነው (ማቴ. 25፡1-13)። መኖር ይህ ነው፤ ወደ ኢየሱስ እንድንሄድ ለተጠራንበት ቀን ታላቅ ዝግጅት ማደረግ ነው! ነገር ግን በአስሩ ደናግል ምሳሌ አምስቱ ጥበበኞች አምስቱም ደግሞ ሞኞች ናቸው። ጥበብና ሞኝነት ምን እንደሆነ እስቲ እንመልከት። ጥበብ በህይወት ውስጥ እና ሞኝነት በህይወት ውስጥ።

እነዚያ ሁሉ የሙሽራው አጃቢዎች ሙሽራውን ለመቀበል እዚያ ሥፍራ ተገኝተዋል፣ ማለትም እሱን ለመገናኘት ይፈልጋሉ ፣ ልክ እኛ እንዲሁ የህይወት አስደሳች ፍፃሜ እንደምንመኝ ማለት ነው፣ በጥበብ እና በሞኝነት መካከል ያለው ልዩነት በመልካም ፈቃድ የሚፈጸም አይደለም ። በሰርጉ ግብዣ ላይ በሰዓቱ መገኘትንም አያመለክትም፣ ሁሉም እዚያ ነበሩ። የጠቢባንና የሞኞች ልዩነት ሌላ ነው፤ ዝግጅት። ጽሑፉ እንዲህ ይላል፡- አስተዋዮቹ “ግን ከመብራታቸው ጋር መጠባበቂያ ዘይት በማሰሮ ይዘው ነበር” (ማቴ 25፡ 4)፤ በሌላ በኩል ዝንጉዎቹ ግን ትርፍ ዘይት አለነበራቸውም ነበር።  ልዩነቱ ይህ ነው፤ የዘይቱም አንዱ ባሕርይ ምንድን ነው? አይታይም: በመብራቶቹ ውስጥ ነው ያለው፣ አይታይም፣ ነገር ግን ያለሱ መብራቶች ብርሃን የላቸው።

እራሳችንን እንመልከትና ህይወታችን ተመሳሳይ አደጋ እንዳለው እናያለን: ብዙ ጊዜ ስለ ቁመናችን በጣም እንጠነቀቃለን - ዋናው ነገር የራስን ምስል በጥንቃቄ መንከባከብ፣ በሌሎች ፊት ጥሩ ስሜት እንዲሰማን ማድረግ ነው። ነገር ግን ኢየሱስ የህይወት ጥበብ ሌላ ቦታ ላይ እንዳለ ተናግሯል፡- የማይታየውን በመንከባከብ ነገር ግን ከሁሉም በላይ አስፈላጊ የሆነው ልብን መንከባከብ ነው። ውስጣዊ ሕይወትን ማዳበር። ይህ ማለት አንዴ ቆም ማለት እና ልብን ማዳመጥ፣ የራሳችንን ሀሳቦች እና ስሜቶች ለመጠበቅ ለማወቅ ጊዜ መስጠት ማለት ነው። በልባችን ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር ምን መሆኑን ለማወቅ ይረዳናል። ጥበብ ማለት እራሳችንን እና ሌሎችን ለመስማት እንድንችል ለዝምታ ቦታ መስጠትን ማወቅ ማለት ነው። ይህም ማለት በስልካችን ስክሪ ፊት ለፊት የምናሳልፈውን አንዳንድ ጊዜዎች ትተን በሌሎች ዓይን፣ በራስ ልብ፣ በእግዚአብሔር እይታ ውስጥ ያለውን ብርሃን ለመመልከት እንዴት እንደሚቻል ማወቅ ማለት ነው። በእንቅስቃሴ ወጥመድ ውስጥ መውደቅ ሳይሆን ለጌታ ጊዜ መስጠት፣ ቃሉን ለማዳመጥ ማለት ነው።

እናም ቅዱስ ወንጌል የውስጣዊውን ህይወት ዘይት "የነፍስ ዘይት" ችላ እንዳንል ትክክለኛውን ምክር ይሰጠናል፣ እሱን ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን ይነግረናል። በእዚህ ታሪክ ውስጥ በእውነት፣ ደናግል መብራቶቻቸውን እንደያዙ እናያለን፣ ነገር ግን ዘይቱን ማዘጋጀትም አለባቸው፣ ወደ ሻጮች ሄደው ይግዙት፣ በመብራት ውስጥ ያኑሩት… (ማቴዎስ 25፡ 7-9) )። ለእኛም እንደዚሁ ነው፡ የውስጣዊው ሕይወት ሊሻሻል ይችላል ነገር ግን የአንድ አፍታ ጉዳይ አይደለም፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊፈታ የሚችል ነገር አይደለም፣ አንድ ሰው ለእያንዳንዱ አስፈላጊ ነገር እንደሚያደርገው ያለማቋረጥ በየቀኑ ጥቂት ጊዜ በመመደብ የውስጥ ሕይወት መዘጋጀት አለበት።

ስለዚህ እራሳችንን መጠየቅ እንችላለን - በዚህ ጊዜ በህይወት ውስጥ ምን እያዘጋጀሁ ነው? በራሴ ውስጥ፣ ምን እያዘጋጀሁ ነው? ምናልባት አንዳንድ ቁጠባዎችን ለማደረግ እየሞከርኩኝ ነው? ስለ ቤት ወይም አዲስ መኪና እያሰብኩ ነው፣ ተጨባጭ እቅዶች… ጥሩ ነገሮች ናቸው፣ እነሱ መጥፎ ነገሮች አይደሉም። ጥሩ ነገሮች ናቸው። ነገር ግን ጊዜን ለልብ እንክብካቤ፣ ለጸሎት፣ ሌሎችን ለማገልገል የሕይወት መድረሻ ለሆነው ጌታ ጊዜ ለመስጠት እያሰብኩ ነው ወይ? ባጭሩ የነፍሴ ዘይት እንዴት ነው? እያንዳንዳችን እራሳችንን እንዲህ ብለን እንጠይቅ፡ የነፍሴ ዘይት እንዴት ነው? እኔ ነፍሴን እመግባለሁኝ ወይ? ነፍሴን በደንብ እጠባበቃለሁኝ ወይ?

የውስጣችንን ዘይት እንድንከባከብ እመቤታችን ማርያም በአማላጅነቷ ትርዳን።

13 November 2023, 10:55

የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >