ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ኢየሱስ በዕርገቱ ወደ ሰማይ መንገድ ይመራናል አሉ።
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!
ዛሬ በጣሊያን እና በሌሎች በርካታ አገሮች የጌታ ዕርገት በዓል እየተከበረ ይገኛል። እኛ ሁላችን በደንብ የምናውቀው በዓል ነው ፣ ነገር ግን ብዙ ጥያቄዎችን ሊያመጣ ይችላል - ቢያንስ ሁለት። የመጀመሪያው የኢየሱስን ከምድር ተለይቶ ወደ ሰማይ መውጣቱን የምናከብረው ለምንድን ነው? የሱ ወደ ሰማይ መውጣት የሚያሳዝን እንጂ የሚያስደስት ነገር አይመስልም! ሁለተኛው ጥያቄ፡- ኢየሱስ አሁን በሰማይ ምን እያደረገ ነው… እዚያ መገኘቱ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? ለምን እያከበርን ነው እና ኢየሱስ አሁን ምን እያደረገ ነው፡ እነዚህ ሁለት ጥያቄዎች ናቸው የምናከብረውን በዓል በሚገባ እንድንረዳ የሚያደርጉን።
የሰው ልጅ በሰማይ
ለምን እያከበርን ነው። ምክንያቱም ከእርገቱ ጋር አንድ አዲስ እና የሚያምር ነገር ተከስቷል፡ ኢየሱስ ሰባዊነታችንን ወደ ሰማይ ማለትም ወደ እግዚአብሔር እንዲወጣ አድርጓል። ያ በምድር ላይ ያሰበው የሰው ልጅ እዚህ አልቀረም። ወደ እግዚአብሔር ዐረገ በዚያም ለዘላለም ይኖራል። ከዕርገቱ ቀን ጀምሮ፣ እግዚአብሔር ራሱ፣ “ተቀየረ” ማለት እንችላለን – ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እርሱ መንፈስ ብቻ ሳይሆን፣ የራሳችንን ሥጋ፣ ሰውነታችንን የሚሸከም ለእኛ ያለው ፍቅር እንዲህ መሆኑን አሳይቷል! የሚጠብቀን ቦታ በዚህ መንገድ ተጠቁሟል፣ እጣ ፈንታችን ይህ ነው። ስለዚህ አንድ የእምነት ጥንታዊ አባት “እንዴት ያለ አስደሳች ዜና ነው! እኛን ወንድሞቹ ሊያደርገን ስለ እኛ ሰው የሆነው እርሱ ከእርሱ ጋር አብረው ያሉትን ሁሉ ከራሱ ጋር ሊሸከም በአብ ፊት እንደ ሰው አቀረበ። ዛሬ "የሰማይን ድል" እናከብራለን፣ ዛሬ በታላቅ ደስታ ሁል ጊዜ እንደምንለው “ሰማይን በገዛ ጣታችን መንካት” ብቻ ሳይሆን ከሥጋችን ሁሉ ጋር መንካት ችለናል። መንግሥተ ሰማያት ሩቅ አይደለም፣ ቤታችን ነው፣ ኢየሱስ ለእኛ ለማዘጋጀት የሄደበት ቦታ ነው። በአብ ልጆች ሆነን በገነት ለዘላለም እንድንኖር መንገዱን ከፍቶልን እሱን መከተል እንችላለን።
ሁሌም ከኛ ጋር ነው
ሁለተኛው ጥያቄ፡- ኢየሱስ በሰማይ ምን እየሰራ ይገኛል? የሚለው ነው። እርሱ በአብ ፊት ለእኛ አለ፣ ያለማቋረጥ ሰብአዊነታችንን ለእርሱ ያሳያል - ለእኛ ሲል የተቀበለውን ቁስሎች ለእርሱ ያሳያል። እሱ “ይሰራል”፣ ማለትም በአብ ፊት ጠበቃችን ሆኖ (1ዮሐ. 2፡1) ይሠራል። ስለዚህ ብቻችንን አልተወንም። እንዲያውም ከማረጉ በፊት የዛሬ ቅዱስ ወንጌል እንደሚለው “እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” (ማቴ 28፡20) ብሎ ነግሯል። እርሱ ሁል ጊዜ ከእኛ ጋር ነው፣ እናም ስለ እኛ "ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል" (ዕብ 7፡25)። በአንድ ቃል ስለዚህ ያማልዳል ማለት እንችላለን። እርሱ ስለ እኛ ሊማልድ በአባቱ እና በእኛ ፊት በተሻለ “ቦታ” አለ። ስለዚህ እኛን ከሁኔታዎች፣ ከችግሮች፣ ከሰዎች እና ከመከራዎቻችን እና ከኃጢአቶቻችን ጋር እንድናቀርብ እየጠበቀን ነው፣ ስለዚህም ለእኛ ይቅርታን እና ምህረትን እንዲያስገኝልን፣ እናም በእሱ እና በአብ ፍቅር ላይ - መንፈስ ቅዱስን እንዲያፈስልን መጠየቅ ይኖርብናል።
ምልጃ መሰረታዊ ነገር ነው። ስለዚህ በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ፣ ኢየሱስ እንድንጠመድ፣ ወደ ሥራ እንድንገባ፣ “በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እንድንጠመቅ” ጠይቆናል (ማቴ. 28፡19)። ቃል በቃል መጠመቅ ማለት ነው። መጠመቅ ከምስጢራዊ ትርጉሙ በተጨማሪ፣ ሁሉንም ነገር በእግዚአብሔር ውስጥ “ለመዝፈቅ” በተጠራንበት መንገድ ልናስበው እንችላለን - ያጋጠመንን እና የምናገኘውን ሁሉ ማለት ነው። ስለዚህ እራሳችንን እንጠይቅ፡ ይህንን ጥያቄ ራሳችንን እንጠይቅ-እማልዳለሁ ወይ? የማውቃቸውን ሰዎች፣ ችግሮቻቸውን የሚናገሩልኝን፣ በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ያሉትን በእግዚአብሔር ውስጥ “እንዲዘፈቅ” አደርጋለሁ ወይ?” ጸሎቴን ከሚጠብቀው ለኢየሱስ ራሴን አማላጅ አደርጋለውን? መንፈሱን ለእኔ ለሚያቀርብልኝ ለእርሱ ለጌታ ችግሬን አቀርባለሁ ወይ? የቤተክርስቲያን እና የአለምንም ጭምር ችግሮች ለጌታ አቀርባለሁ ወይ? የሰማይ ንግሥት በጸሎት ኃይል እንድናማልድ ትርዳን።