ር.ሊ.ጳ. ፍራንችስኮስ መንፈስ ቅዱስ ከፍርሃት ነፃ ያወጣናል እና በሮችን ይከፍታል ማለታቸው ተገለጸ።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በእለቱ በሚነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ እንደምያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በግንቦት 20/2015 ዓ.ም መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ የወረደበት የበዓለ 50 ወይም የጴራቅሊጦስ በዓል ላይ መሰረቱን ያደረገ አስተንትኖ እንደነበረ የተገለጸ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ከፍርሃት ነፃ ያወጣናል እና በሮችን ይከፍታል ማለታቸው ተገልጿል።
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ክቡራን እና ክቡራት ይዘግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እሕቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!
ዛሬ የጴንጤቆስጤ በዓል አከባበር ላይ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል ከኢየሱስ ሞት በኋላ ሐዋርያት ወደ ተሸሸጉበት ወደ ላይኛው ክፍል ይወስደናል (ዮሐ. 20፡19-23)። የተነሣው፣ በፋሲካ ምሽት፣ በዚያ የፍርሃትና የጭንቀት ሁኔታ ውስጥ ራሱን አቅርቧል፣ እናም በእነሱ ላይ በመተንፈስ፣ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ” (ዮሐንስ 20. 22) ይላል። በዚህ መንገድ፣ በመንፈስ ስጦታ፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ከፍርሃት፣ በቤት ውስጥ ተዘግተው እንዲኖሩ ካደርገው ከዚህ ፍርሃት ነፃ ሊያወጣቸው ፈልጎ ነፃ አውጥቷቸው ወጥተው የወንጌል ምስክርና አዋጅ ነጋሪዎች እንዲሆኑ ነው። መንፈስ ቅዱስ በሚሠራው ሥራ ላይ ጥቂት እናሰላስል፡ ከፍርሃት ነጻ የሚያወጣ ነው።
ደቀ መዛሙርቱ በሮችን ዘግተው ነበር፣ ቅዱስ ወንጌል እንዲህ ይላል፣ “በፍርሃት” (ዮሐንስ 20፡19)። የኢየሱስ ሞት አስደነገጣቸው፣ ሕልማቸው ፈርሷል፣ ተስፋቸው ጠፋ። እናም ውስጣቸውን ዘጉ። በዚያ ክፍል ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውስጥም በልብ ውስጥ ሳይቀር። ይህንን ማስመር እወዳለሁ፡ ውስጣቸው ተዘግቷል። እኛስ ምን ያህል ጊዜ ራሳችንን እንዘጋለን? ለምን ያህል ጊዜ፣ በአንዳንድ አስቸጋሪ ሁኔታዎች፣ በአንዳንድ የግል ወይም የቤተሰብ ችግሮች ምክንያት፣ እኛን በሚጠቁመን ሰዎች ምክንያት በሚፈጠረው መከራ ወይም በዙሪያችን በምንተነፍሰው ክፋት የተነሳ ቀስ በቀስ ወደ ተስፋ ማጣት እና ወደ ፊት ለመቀጠል ድፍረት ማጣት አለብን ወይ? ይህ ብዙ ጊዜ ይከሰታል። እናም እንደ ሐዋርያት ራሳችንን ዘግተን በጭንቀት ቤተ ሙከራ ውስጥ ራሳችንን እንዘጋለን።
ወንድሞች እና እህቶች፣ ይህ “እራሳችንን መዝጋት” የሚሆነው በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ፣ ፍርሃት እንዲቆጣጠር ስንፈቅድ እና ከፍተኛ ድምፅ ውስጣችንን እንዲቆጣጠር ስንፈቅድ ነው። ስለዚህ መንስኤው ፍርሃትን አለመቋቋም፣ አለመቻልን መፍራት፣ የዕለት ተዕለት ውጊያዎችን ብቻችንን መጋፈጥ፣ አደጋ ላይ መጣል እና ከዚያም ተስፋ መቁረጥ፣ የተሳሳቱ ውሳኔዎችን ማድረግ ያካትታል። ወንድሞች፣ እህቶች፣ ፍርሀት የገድበናል፣ ፍራቻ ሽባ ያደረገናል። እናም ደግሞ እንድንገለል ያደርጋል፣ የሌሎችን ፍርሃት፣ የውጭ አገር ሰዎች የሆኑትን፣ የተለዩትን፣ በሌላ መንገድ የሚያስቡትን አስቡ። እናም እግዚአብሔርን መፍራት እንኳን ሊኖር ይችላል፡ ይቀጣኛል፣ ይቆጣኛል… ለእነዚህ የውሸት ፍርሃቶች ቦታ ከሰጠን በሮች ይዘጋሉ፡ የልብ በሮች፣ የህብረተሰብ በሮች እና እንዲያውም የቤተክርስቲያን በሮች! ፍርሃት ባለበት መዘጋት አለ። እና ይሄ መሆን የለበትም።
ነገር ግን ወንጌል ከሙታን የተነሣው መድኃኒት መንፈስ ቅዱስን ይሰጠናል። ከፍርሀት እስር ቤቶች ነፃ ያወጣናል። መንፈሱን ሲቀበሉ ሐዋርያት - ዛሬ ይህን እናከብራለን - ከሰገነት ወጥተው ወደ ዓለም በመሄድ ኃጢአትን ይቅር ለማለት እና ወንጌልን ለመስበክ ይወጣሉ። ለእሱ ምስጋና ይግባው ፍርሃቶች ይሸነፋሉ እና በሮች ይከፈታሉ። ምክንያቱም መንፈሱ የሚያደርገው ይህንኑ ነው፡ የእግዚአብሔር ቅርበት እንዲሰማን ያደርጋል፣ እናም ስለዚህ ፍቅሩ ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል፣ መንገዱን ያበራል፣ ያጽናናል፣ በመከራ ውስጥ ይደግፋል። ከፍርሀት እና መዘጋት ጋር ፊት ለፊት እንድንጋፈጥ ያደርገናል፣ እንግዲያውስ፣ መንፈስ ቅዱስን ስለእኛ፣ ለቤተክርስቲያኑ እና ለመላው አለም እንለምነው፡ አዲስ ጴንጤቆስጤ እኛን የሚያጠቁን ፍርሃቶችን አውጥተን የእግዚአብሔርን ፍቅር ነበልባል እናነቃቃ።
ቅድስተ ቅዱሳን የሆነችው እና በመጀመሪያ ደረጃ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላችው ማርያም አማላጃችን ትሁንልን።