ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እምነት የሃሳብ ጥቅል ሳይሆን ልንጓዝበት የሚገባ መንገድ ነው ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የአገር ጎብኝዎች በእለቱ በሚነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ተንተርሰው የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ እንድሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በሚያዝያ 29/2015 ዓ.ም ባደረጉት አስተንትኖ እምነት የሃሳብ ጥቅል ሳይሆን ልንጓዝበት የሚገባ መንገድ ነው ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰንድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው ሥርዓተ አምልኮ ላይ (ዮሐ 14፡1-12) ላይ ተወስዶ የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት ከነበረው የመጨረሻ ንግግር የተወሰደ ነው። የደቀ መዛሙርቱ ልብ ታወከ፣ ነገር ግን ጌታ የሚያጽናና ቃል ነግሯቸዋል፣ አትፍሩ፣ አትጨነቁ በማለት ይናገራቸዋል፣ እንዲያውም ብቻችውን አልተዋችሁም፣ ነገር ግን ቦታ ሊያዘጋጅላቸውና ሊመራቸው እንደ ሚሄድ ይናገራል። ስለዚህ ዛሬ ጌታ ለሁላችንም የምንሄድበትን አስደናቂ ቦታ ይጠቁመናል፣ እናም በተመሳሳይ ጊዜ ወደዚያ እንዴት መሄድ እንዳለብን ይነግረናል፣ የምንሄድበትን መንገድ ያሳየናል። የት መሄድ እንዳለብን እና እንዴት ወደዚያ መሄድ እንዳለብን ይነግረናል።

በመጀመሪያ የት መሄድ እንዳለበት። ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን ጭንቀት አይቷል፣ ከምንወደው ሰው ራሳችንን እንድንለይ ስንገደድ በእኛ ላይ እንደሚደርስ ሁሉ ትቷቸው ሊሄድ ሲል የደረሰባቸውን  ፍርሃታቸውንም ተመልክቷል። ከዚያም እንዲህ ይላል፡- “እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ [...]እሄድለሁ” (ዩሐንስ 14. 2-3) ይላቸዋል። ኢየሱስ የሚያውቀውን የቤት ምስል፣ የግንኙነቶች እና መቀራረብ ቦታን ይጠቀማል። በአብ ቤት ውስጥ - ለጓደኞቹ እና ለእያንዳንዳችን - ለእናንተም ጭምር ቦታ አለን፣ እንኳን ደህና መጡ በማለት በእቅፍ ሙቀት ለዘላለም ይቀበለናል እና እኔ ለእናንተ ቦታ ለማዘጋጀት በሰማይ ነኝ ይላቸዋል! ያ ከአብ ጋር መተቃቀፍ ለዘለአለም ቦታ የሆነውን ያዘጋጅልናል።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ይህ ቃል የመጽናኛ ምንጭ ነው፣ ለእኛም የተስፋ ምንጭ ነው። ኢየሱስ ከኛ አልተለየም ነገር ግን የመጨረሻውን መድረሻችንን እየገመተ መንገዱን ከፍቶልናል፣ ይህም በልቡ ውስጥ ለእያንዳንዳችን ቦታ ካለ ከእግዚአብሔር አብ ጋር መገናኘት ነው። ከዚያም ድካም፣ ግራ መጋባት እና ውድቀት ሲያጋጥመን ህይወታችን ወዴት እያመራ እንዳለ እናስታውሳለን። ዛሬ ግቡን የመርሳት፣የመጨረሻውን ጥያቄ የመርሳት፣አስፈላጊ የሆኑትን፡ወዴት እየሄድን ነው? የት ነው የምንሄደው? መኖር ምን ዋጋ አለው? ያለ እነዚህ ጥያቄዎች ህይወትን የምንጨፈጭፈው አሁን ባለንበት ጊዜ ብቻ ነው፣ በተቻለ መጠን መደሰት እንዳለብን እያሰብን ያለ ግብ፣ ያለ ዓላማ ከእለት ወደ እለት እንኖራለን። በአንጻሩ የትውልድ አገራችን በሰማይ ነው (ፊል 3፡20 ተመልከት) የመዳረሻውን ታላቅነትና ውበት አንርሳ!

መድረሻውን ካወቅን በኋላ፣ እኛም በዛሬው ወንጌል እንደ ተጠቀሰው እንደ ሐዋርያው ​​ቶማስ፣ እራሳችንን እንጠይቃለን፡ ወደዚያ እንዴት መሄድ እንዳለብን፣ መንገዱ ምንድን ነው ብለን ልንጠይቅ እንችላለን። አንዳንድ ጊዜ በተለይም ትልቅ ችግሮች ሲያጋጥመን እና ክፋት የበለጠ ጠንካራ እንደሆነ ስሜት ሲሰማ እና አንድ ሰው ምን ማድረግ አለብኝ፣ የትኛውን መንገድ መከተል አለብኝ ብሎ ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል። የኢየሱስን መልስ እንስማ፡- “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ” (ዮሐ 14፡6)። "መንገዱ እኔ ነኝ" በእውነት ለመኖር እና የተትረፈረፈ ሕይወት ለማግኘት ኢየሱስ ራሱን መከተል ያለብን መንገድ ነው። እርሱ መንገድ ነው፣ ስለዚህም በእርሱ ማመን "የሃሳብ ጥቅል" ሳይሆን የመጓዣ መንገድ፣ ልንጓዘው የሚገባን መንገድ፣ ከእርሱ ጋር ነው። ኢየሱስን መከተል ነው፣ ምክንያቱም እርሱ ወደ እርሱ የሚወስደው መንገድ ነውና። ኢየሱስን ተከተሉ እና እርሱን ምሰሉ፣ በተለይም ለሌሎች በመቅረብ እና በምሕረት ምልክቶች። መንግሥተ ሰማያት ለመድረስ የሚያስችለን አቅጣጫ መጠቆሚያ መሣሪያ ይኸውና፡ ኢየሱስን መውደድ፣ በእርሱ መንገድ መጓ፣ በምድር ላይ የፍቅሩ ምልክቶች ይሆናሉ።

ወንድሞቼ እና እህቶቼ አሁን ያለንበትን ወቅት እና ሁኔታ እንኑር፣ ስጦታውን በእጃችን እንውሰድ ነገር ግን እራሳችንን እንዳናስጨንቅ፣ ወደ ላይ እንመልከት፣ ወደ መንግሥተ ሰማያት እንመልከት፣ ግባችንን እናስታውስ፣ ምን እንደሆንን እናስብ። ተጠርተናል ለዘላለም ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ከሰማይም እስከ ልብ ድረስ የኢየሱስን ምርጫ ዛሬ እናድስ እርሱን የመውደድ እና የመከተል ምርጫን እናድስ።ኢየሱስን በመከተል አስቀድማ ግቧ ላይ የደረሰች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተስፋችን ስንቅ ትሁነን።

07 May 2023, 10:10

What is the Regina Coeli?

The antiphon Regina Coeli (“Queen of Heaven”) is one of four traditional Marian antiphons, the others being Alma Redemptoris Mater, Ave Regina Coelorum, and Salve Regina.

It was Pope Benedict XIV who, in 1742, enjoined the recitation of the Regina Coeli in place of the Angelus during Eastertide, that is, from Easter Sunday to the end of Pentecost. It is recited standing as a sign of Christ’s victory over death.

Like the Angelus, the Regina Coeli is said three times a day, at dawn, at noon, and at dusk, in order to consecrate the day to God and the Virgin Mary.

This ancient antiphon arose, according to a pious tradition, in the 6th century; it is attested in documentary sources from the first half of the 13th century, when it was inserted in the Franciscan breviary. It is composed of four short verses, each ending with an “alleluia.” With the Regina Coeli, the faithful turn to Mary, the Queen of Heaven, to rejoice with her at the Resurrection of Christ.

At the Regina Coeli on Easter Monday of 2015, Pope Francis spoke about the spiritual dispositions that should animate the faithful as they recite this Marian prayer:

“In this prayer, expressed by the Alleluia, we turn to Mary inviting her to rejoice, because the One whom she carried in her womb is Risen as He promised, and we entrust ourselves to her intercession. In fact, our joy is a reflection of Mary’s joy, for it is she who guarded and guards with faith the events of Jesus. Let us therefore recite this prayer with the emotion of children who are happy because their mother is happy.”

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >