ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የገና በዓል እርዳታ እና ደስታን ለሌሎች እንድንሰጥ ይጋብዘናል ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እርሳቸው በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው የሚያደርጉትን አስተንትኖ ለመከታተል በስፍራው ለሚገኙ ምዕመናን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው የጎሮጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ትላንት በተጀመረው 4ኛ የስብከተ ገና ሳምንት ላይ ከሉቃስ ወንጌል 1፡39-45 ላይ ተስወስዶ በተነበበውና “ማርያምም በዚያው ሰሞን በፍጥነት ተነሥታ ወደ ደጋው አገር፣ ወደ አንድ የይሁዳ ከተማ ሄደች፤ ወደ ዘካርያስ ቤትም ገብታ ለኤልሳቤጥ ሰላምታ አቀረበች። ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ፣ ፅንሱ በማሕፀኗ ውስጥ ዘለለ፤ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች፤ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፤ “አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ለመሆኑ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እኔ ማን ነኝ? እነሆ፤ የሰላምታሽ ድምፅ ጆሮዬ እንደ ገባ፣ በማሕፀኔ ያለው ፅንስ በደስታ ዘሎአልና። ጌታ ይፈጸማል ብሎ የነገራትን ያመነች እርሷ የተባረከች ናት!” በሚለው ማርያም ኤልሳቤጥን ጥየቃ የሄደችበትን ሁኔታ በሚገልጸው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን የገና በዓል እርዳታ እና ደስታን ለሌሎች እንድንሰጥ ይጋብዘናል ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

 የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው 4ኛው የስብከተ ገና ሳምንት በእሑድ ስርዐተ አምልኮ ላይ የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል ማርያም ወደ ኤልሳቤጥ ስላደረገችው ጉብኝት ይናገራል (ሉቃ. 1፡39-45)። የመልአኩን ብስራት ከተቀበች በኋላ ድንግል ምን እንደተፈጠረ በማሰብ፣ ችግሮችን እና እንቅፋቶችን በማሰብ በቤት ውስጥ መቀመጥ አልፈለገችም፣ እነዚህም በእርግጠኝነት የሚቀሩ ጉዳዮች አይደሉም፣ ምክንያቱም ምስኪን ልጃገረድ በዚህ የብስራት ዜና ምን ማድረግ እንዳለባት አላወቀችም ነበር፣ በዛ ዘመን ባሕል…መሰረት ምን ማድረ እንደሚገባት አልተረዳችም… በተቃራኒው፣ መጀመሪያ የተቸገረን ሰው ታስባለች፤ በራሷ ችግር ከመጠመድ ይልቅ ስለ ተቸገረ ሰው ታስባለች፣ ስለ ዘመዷ ኤልዛቤት ምንም እንኳን በእድሜ የገፋች እና  ልጅ የሌላት ሴት ብትሆንም በሕይወቷ አሁን ስለተከሰተው እንግዳና ድንቅ ነገር ታስባለች። ማርያም በጉዞው ውስጥ በሚያጋጥማት ምቾት ሳትሰናከል በልግስና ተነሳች፣ እንድትቀርብ እና እንድትረዳው ለሚጠራት ውስጣዊ ግፊት ምላሽ ሰጠች። ረጅም ኪሎ ሜትር የሚያክል መንገድ ርቀት በእግሯ ተጉዛ ሄደች፣ መክንያቱም በወቅቱ ወደዚያ የሚሄድ አውቶቡስ አልነበረም፡ በእግሯ ሄደች። ለመርዳት ወጣች። እንዴት? ደስታዋን በማካፈል። ማርያም በልቧ እና በማህፀኗ የተሸከመችውን ደስታ የኢየሱስን ደስታ ለኤልሳቤጥ ሰጠቻት። ወደ እርሷ ሄዳ ስሜቷን ተናገረች እናም ይህ የስሜቶች አዋጅ ሁላችንም የምናውቀው ጸሎት ማለትም “ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፣ መንፈሴ በአምላኬ በመድኅኔቴ ትደሰታለች” የሚለው ጸሎት እንዲወለድ አደረገ። እመቤታችንም “በፍጥነት ተነስታ ሄደች” (ቁ. 39) እንዳለ ጽሑፉ ይናገራል።

ተነስታ ሄደች። በመጨረሻው 4ኛው የስብከተ ገና ሳምንት ጉዞ፣ በእነዚህ ሁለት ግሦች እንመራ። ለመነሳትና በችኮላ ለመሄድ፡- እነዚህ ሁለት እንቅስቃሴዎች ማርያም ያደረገቻቸው እና የገና በዓል ሲቃረብ እንድናደርግ የጋበዘችን ግሦስች ናቸው። በመጀመሪያ ደረጃ ተነሱ። ከመልአኩ ብስራት በኋላ ለድንግል አስቸጋሪ ጊዜ ከፊቷ ተደቅኗል፣ ያልተጠበቀ እርግዝናዋ በጊዜው ባሕል ውስጥ አለመግባባቶችን አልፎ ተርፎም ከባድ ቅጣትን አልፎ ተርፎም በድንጋይ ተወግሮ እስከ መሞት ድረስ አጋልጧታል። ምን ያህል ጭንቀትና ተስፋ መቁረጥ እንዳጋጠማት እናስብ! ቢሆንም ተስፋ አልቆረጠችም ነበር፣ ተስፋ አልቆረጠችም፤ ተነሳች። ወደ እግዚአብሔር እንጂ ወደ ችግሮቿ አልተመለከተችም። እናም ለማን እርዳታ ማድረግ እንደ ሚገባት እንጂ ከማን እርዳታ እንደምትጠይቅ አላሰበችም። ሁልጊዜ ስለሌሎች ታስባለች፡ ማርያም ማለት ነው፡ ሁልጊዜ የሌሎችን ፍላጎት ታስባለች። በቃና ዘገሊላ ሰርግ ላይ የወይን ጠጅ እንደሌለ ስታውቅ እሷም እንዲሁ አደረገች። የሌሎች ሰዎች ችግር ቢሆንም ቅሉ እርሷ ግን ስለዚህ ጉዳይ ታስባለች እና መፍትሄ ትፈልጋለች። ማርያም ሁልጊዜ ስለሌሎች ታስባለች። እኛንም ታስባለች።

በተለይ ችግሮች ሊያደቁን በሚነሱበት ሰዓት እና በሚያስፈራሩበት ጊዜ መነሳትን ከእመቤታችን እንማር። ለመነሳት፣ በችግሮች ውስጥ እንዳንዘናጋ፣ ለራስ ርኅራኄ እንዳንሰጥ ወይም በሚያሳዝን ሀዘን ውስጥ ላለመውደቅ ከእርሷ እንማር። ግን ለምንድነው የምንነሳው? ምክንያቱም እግዚአብሔር ታላቅ ነው ወደ እርሱ ከደረስን ሊያነሳን ዝግጁ ነው። ስለዚህ እያንዳንዱን ግፊት የሚከለክሉ እና ወደ ፊት እንዳንሄድ የሚከለክሉን አሉታዊ አስተሳሰቦችን እናስወግድ። ከዚያም እንደ ማርያም እናድርግ፡ ዙሪያችንን እንይ እና የምንረዳውን ሰው እንፈልግ! ትንሽ እገዛ የምሰጠው አንድ የማውቃቸው አዛውንት አሉ፣ ከእርሳቸው ጋር ለጥቂት ጊዜ መቆየት እችላለሁ ወይ? ሁላችሁም አስቡበት። ወይም ለአንድ ሰው አገልግሎት፣ ደግነት፣ የስልክ ጥሪ ለማቅረብ እንዘጋጅ? ግን ማንን ልረዳ እችላለሁ? ተነስቼ እረዳለሁ። ሌሎችን በመርዳት፣ ከችግሮች እንድንነሳ እራሳችንን እንረዳለን።

ሁለተኛው እንቅስቃሴ በችኮላ መሄድ ነው። ይህ ማለት በሁከት መንቀሳቀስ ማለት አይደለም፣ በችኮላ መሄድ ማለት አይደለም፣ ይህ ማለት አይደለም። ይልቁንም ዘመናችንን በደስታ እርምጃ መምራት፣ በልበ ሙሉነት እግሮቻችንን ሳንጎትት፣ የቅሬታ ባሪያዎች አለመሆናችንን በማሰብ መጓዝ ማለት እንደ ሆነ ያሳያል - እነዚህ ቅሬታዎች የብዙዎችን ህይወት ያበላሻሉ፣ ምክንያቱም አንድ ሰው ማጉረምረም እና ማጉረምረም ስለሚጀምር እና ህይወቱ በዚህ መልኩ ስለሚበላሽ ነው። ማጉረምረም ሁል ጊዜ የሚወቅሰውን ሰው እንዲፈልጉ ይመራዎታል። ወደ ኤልሳቤጥ ቤት ስትሄድ፣ ማርያም ልቧ እና ህይወቷ በእግዚአብሔር የተሞላ፣ በደስታ የተሞላውን ፈጣን እርምጃ አደረገች። ስለዚህ ለራሳችን ጥቅም ስንል እራሳችንን እንጠይቅ፡ “እርምጃዬ” እንዴት ነው? ንቁ ነኝ ወይስ በጭንቀት ፣ በሀዘን ውስጥ ሆኜ ነው የምጓዘው? በተስፋ ወደ ፊት እጓዛለሁ ወይንስ ቆሜ በራሴ አዝኛለሁ? በሰለቸን የማጉረምረምና የመነጋገር አካሄድ ከቀጠልን እግዚአብሔርን ለማንም ማምጣት አንችልም፣ ይልቁንስ ምሬትና ጨለማን ብቻ እናመጣለን። ይልቁንስ ጤናማ የሆነ የጫዋታ ለዛ ማዳበር በጣም ጥሩ ነው፣ ለምሳሌ ቅዱስ ቶማስ ሞር ወይም ቅዱስ ፊሊፕ ኔሪን እንመልከት። እኛ ደግሞ ይህን ጸጋ መጠየቅ እንችላለን፣ ይህ ጤናማ የጫዋታ ለዛ ስሜት ጸጋ በጣም ብዙ መልካም ነገር ያደርጋል። ለባልንጀራችን ልንሰራው የምንችለው የመጀመሪያው የበጎ አድራጎት ተግባር ረጋ ያለ እና ፈገግታ የተሞላ ፊት ማቅረብ መሆኑን አንዘንጋ። ማርያም ለኤልሳቤጥ እንዳደረገችው የኢየሱስን ደስታ ለሰዎች ማምጣት ይኖርብናል።

ወላዲተ አምላክ እጇን ይዘን እንድንነሳ እና ወደ ገና በችኮላ እንድንሄድ በአማላጅነቷ ትርዳን።

19 December 2021, 10:48

የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >