ፈልግ

Vatican News

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የክርስቶስ ንግሥና እውነትን፣ አገልግሎትን፣ ሕይወትን ያመለክታል ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በኅዳር 12/2014 ዓ.ም የተከበረውን ክርስቶስ የዓለም ንጉሥ በዓል አስመልክተው በቫቲካን ከሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባደረጉት አስተንትኖ በክርስቶስን ንግሥና ላይ ያተኮረ አስተንትኖ ያደረጉ ሲሆን ኢየሱስ የመጣው የበላይ ለመሆን ሳይሆን ሌሎችን ለማገልገል መሆኑን ጠቁመዋል። ክርስቲያኖችም እንዲሁ እንዲያደርጉ ተጠርተዋል፣ ከድካማችን ነፃ የሚያወጣውን የኢየሱስን ወሰን የለሽ ፍቅር እውነት መፈለግ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አስተንትኖዋቸውን ሲቀጥሉ በዛሬው ክርስቶስ የዓለም ንጉሥ በዓል ንግሥ ላይ  በተነበበው ንባብ ላይ በማሰላሰል፣ ኢየሱስ ጲላጦስ ጥያቄ ባቀረበለት ወቅት፣ “እኔ ንጉሥ ነኝ” በማለት በግልጽ የተናገረው እንዴት እንደሆነ ቀደም ሲል በተነበበው ቅዱስ ወንጌል (ዮሐንስ 6 ) ውስጥ ኢየሱስ ሰዎች እርሱን እንደ ንጉሥ አድርገው እንዲያመሰግኑት እንደ ፈለገ ያሳየናል ብለዋል። ምክንያቱም “ንግሥና”ን እንደ ዓለማዊ መመዘኛዎች መረዳቱ እርሱ ካሰበው በእጅጉ የተለየ እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ወደ ዓለም የመጣው ሊገዛ ሳይሆን “ሊያገለግል ነው” ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ይህንንም ያደረገው “በኃይል ምልክቶች” ሳይሆን “በምልክቶች ኃይል” ነው ብለዋል። ንግሥናው በመስቀል ላይ እስከ ተቸነከረበት ደረጃ ድረስ ያለውን አገልግሎት የሚያመለክት ሲሆን ይህም ንግሥና በሌሎች ላይ ኩራትን፣ ዝናን፣ ክብርን እና ሥልጣንን የሚገልጥ ሳይሆን "በእውነት ከሰው መለኪያ በላይ የሆነ" ነገር ነው ብለዋል።

ኢየሱስ የሆሉም ንጉሥ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ክርስቶስ ሕዝቡ ከእርሱ ተቃራኒ ሆነው በቆሙበት ወቅት ንጉሥ ነኝ እንዳለ የተናገሩት ሲሆን ነገር ግን ሕዝቡ ከዚህ ቀደም ሲያደንቁት፣ ግን ርቆ መሄድ እንደ ፈለገ እና እርቀቱን እንደጠበቀ አመልከተዋል። ይህ የሚያሳየው ኢየሱስ ምድራዊ ዝናንና ክብርን ለማግኘት ካለው ምድራዊ ፍላጎት “በተቃራኒ እንደ ቆመ” ያሳያል ያሉት ቅዱስነታቸው ሁሉም ክርስቲያኖችም ይህን ሌሎችን የማገልገል ተልእኮ በመኮረጅ ፈቃድ፣ ክብርና ጭብጨባ ከመጠየቅ ይልቅ ራሳቸውን መጠየቅ እንደሚያስፈልግ ተናግሯል።

ተከታዮች ነፃ እና ሉዓላዊ መሆን ይኖርባቸዋል

ኢየሱስ ከምድራዊ ታላቅነት በሸሸ ጊዜ፣ እርሱን የተከተሉትን ሰዎች ልብ ነፃ እና ሉዓላዊ ያደርጋል፣ በማለት ጳጳሱ ጠቁመው፣ ኢየሱስ ከኃጢአት ባርነት ነፃ አውጥቶናል ብለዋል። “መንግሥቱ ነጻ ታወጣለች” በማለት እያንዳንዱ ደቀ መዝሙር እንደ ወዳጅ የሚቆጠርበት እንጂ እንደ ርዕሰ ጉዳይ የማይታይበት፣ ምንም እንኳን እሱ ከሉዓላዊ ገዢዎች ሁሉ በላይ ቢሆንም ሁላችንም ነፃ እንድንወጣ የሚፈልገውን ክርስቶስን በመከተል “ክብርን እናገኛለን” በማለት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

ለእውነት መመስከር

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የኢየሱስ ነፃነት ከእውነት የመነጨ መሆኑን፣ ኢየሱስ በውስጣችን ያለውን ውሸት “በውስጣችን ያለው እውነት” እንዳደረገው አስረድተዋል። ኢየሱስ በልባችን ሲነግሥ ከግብዝነት፣ ከሽንገላ እና ከንትርክ ነፃ ወጥተናል ማለት ነው ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የገለጹ ሲሆን “ከኢየሱስ ጋር በመሆናችን እውነተኛ እንሆናለን” ብለዋል። በተመሳሳይም የአቅም ገደቦችን እና ድክመቶቻችንን ልንቋቋም ይገባናል፣ ነገር ግን በኢየሱስ ጌትነት ሥር ስንኖር ከምግባረ ብልሹነት ወይም ማባበያዎችን ከመከተል እንቆጠባለን ያሉ ሲሆን  በማጠቃለያም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ማርያም በየዕለቱ ከምድራዊ የኃጢአት ባርነት ነፃ የሚያወጣንና በሕይወታችን ወደ ተግሣጽ የሚመራንን “የዓለም ንጉሥ የሆነውን የኢየሱስን እውነት” እንድንፈልግ እንድትረዳን አማላጅነቷን ልንማጸን ይገባል ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው አስተንትኖዋቸውን አጠናቀዋል።

21 November 2021, 12:11

የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >