ፈልግ

ፋይል፡ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እና የታላቁ የአል-አዝሃር ኢማም አህመድ ኤል-ታይብ እ.ኤ.አ. በ 2019  “ሰብዓዊ ወንድማማችነት ለአለም ሰላም እና አብሮ መኖር” በሚለው ሰነድ ፊርማ ከፈረሙ በኋላ ስጨባበጡ የሚያሳይ ምስል ። ፋይል፡ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እና የታላቁ የአል-አዝሃር ኢማም አህመድ ኤል-ታይብ እ.ኤ.አ. በ 2019 “ሰብዓዊ ወንድማማችነት ለአለም ሰላም እና አብሮ መኖር” በሚለው ሰነድ ፊርማ ከፈረሙ በኋላ ስጨባበጡ የሚያሳይ ምስል ።  (ANSA)

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጥላቻን ሰንኮፍ ለመንቀል ‘ሰብዓዊ ወንድማማችነት’ ወሳኝ ነው አሉ!

በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ እና በታላቁ ኢማም አህመድ አል ታዬብ የተደረገው “የሰብዓዊ ወንድማማችነት ለዓለም ሠላም እና አብሮ መኖር” የሚለው የስምምነት ሰነድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥላቻ በተስፋፋበት በአሁኑ ጊዜ የርኅራኄ እና ሰብዓዊ ትብብር አርአያ ነው ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተናገሩ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ረቡዕ ሰኔ 7/2015 ዓ.ም. ለፀጥታው ምክር ቤት ንግግር ሲያደርጉ ፥ የውጪ ሃገር ሰዎችን ጥላቻ ፣ ዘረኝነት ፣ አለመቻቻል ፣ የጥላቻ እና የሀይማኖት ስደት ምክንያት በዓለም ዙሪያ ግጭቶችን እና አስከፊ ወንጀሎችን እያስከተለ ነው ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት መሪው ጥላቻን እንደ የግጭቱ መንስኤ እና ማባባሻ መንገድ ነው ብለው ፥ የሰው ልጅ ስሜት ላይ እንደ መጥፎ ማቀጣጠያ ነዳጅ ሆኖም ይሰራል በማለት ጠቁመዋል። በመቀጠልም የማህበራዊ ሚዲያ የጥላቻ ንግግሮችን እና የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት ላይ ያለውን ሚና ጎላ አድርገው ገልጸዋል ፤ ይህም “ጥላቻን ለሚቀሰቅሱ ሰዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ መሳሪያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል” ብለዋል።

ጉቴሬዝ በጥላቻ የተሞሉ አስተሳሰቦች ወደ ዋና ዋና የተባሉ ሚድያዎች ላይ እየቀረቡ እውነተኛው የሰው ልጅ ህይወት ላይ ብጥብጥ እየቀሰቀሱ በመሆናቸው ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፐብሊክ ፣ በምያንማር እና በኢራቅ ያሉ ጉዳዮችን በመጥቀስ የጥላቻ ንግግር “አናሳዎችን ለመሳደብ” ጥቅም ላይ ውለዋል ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት ዋና ኃላፊ የበለጠ አካታች እና ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ዓለም ለመፍጠር ፥ እንዲሁም በትምህርት ፣ በሰላም ግንባታ እና በዓለም አቀፍ ትብብር ላይ ተጨማሪ ኢንቨስትመንቶችን በማድረግ ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አሳስበዋል። የርህራሄ፣ የመከባበር እና የሰዋዊ ወንድማማችነት እሴቶች የአለመግባባት እና የመለያየት መርዝ ምርጡ መድሀኒቶች መሆናቸውን አፅንዖት ሰጥተውበታል።

ሰብአዊ ወንድማማችነት የተሻለ ዓለም ለመገንባት

ጉቴሬዝ የእምነት መሪዎች በተከታዮቻቸው መካከል ጥላቻን በመዋጋት ረገድ ያላቸውን ጠቀሜታ አጉልተዋል። ሌሎች ተናጋሪዎችም ሰብአዊ ወንድማማችነት ‘የተሻለ ዓለምን ለመገንባት እና ሠላምን ለማራመድ’ እንደሚረዳ አፅንዖት ሰጥተውበታል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መሪ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ እና የአል-አዝሃር ታላቁ ኢማም የሆኑት አህመድ ኤል ጣይብ በጋራ የፃፉትን “የሰብዓዊ ወንድማማችነት ለዓለም ሠላም እና አብሮ መኖር” የሚለውን ሰነድ የርህራሄ እና የሰዋዊ አጋርነት አርአያ መሆኑን አረጋግጠዋል። ሰነዱም የሃይማኖት እና የፖለቲካ መሪዎች “ጦርነትን፣ ግጭቶችንና የአካባቢ ውድመትን እንዲያስቆሙ አጥብቆ ያስገነዝባል።

የጳጳሱ መልእክት

የቅድስት መንበር የፀጥታው ምክር ቤት ተወካይ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥላቻ እየተስፋፋ በመምጣቱ ማዘናቸውን ገልጸው ፥ ዓለም ‘በወንድማማችነት ረሃብ’ እየተሰቃየች መሆኑን እና ይህም ወዳልተገባ የጦር መሣሪያ ግጭት እና ጦርነት እንደሚመራን ጠቁመዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን ወክለው የተናገሩት ሊቀ ጳጳስ ጋላገር ሠላምን እውን ለማድረግ ዓለም ‘ከጦርነት ሕጋዊነት አመክንዮ መራቅ አለበት’ ብለዋል። በተጨማሪም “በታሪክ ውስጥ አዲስ የሠላም ምዕራፍ ለመጻፍ አሁንም ጊዜ እንዳለ እና ጦርነት የወደፊቱ ሳይሆን ያለፈው ነው” በማለት ተናግሯል።

በኒውዮርክ የተካሄደው ስብሰባ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና እንግሊዝ የቀረበው የጥላቻ ንግግር ፣ ዘረኝነት እና ጽንፈኝነት በግጭት ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ የውሳኔ ሃሳብ ላይም ውይይት ተደርጓል። የውሳኔ ሃሳቡም በእነዚህ ከፋፋይ አስተሳሰቦች የሚነሱ ስጋቶችን ለመዋጋት ያለመ ነው።

የትጥቅ ግጭቶች ፣ ጽንፈኝነት እና የጥላቻ ንግግሮች የሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች ቢኖሩም ተናጋሪዎቹ በማኅበረሰቦች መካከል ሠላምና መግባባትን ለመፍጠር ውይይት፣ የመከላከያ እርምጃዎች እንዲሁም በሃይማኖቶች እና በባህሎች መካከል ውይይቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል ።

 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስለ ሰብአዊ ወንድማማችነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ከዚህን በፊትም ደጋገመው የሰብአዊ ወንድማማችነትን አስፈላጊነት አጽንዖት ሰጥተውበታል። እ.አ.አ. በ 2019 “የሰብአዊ ወንድማማችነት ለዓለም ሠላም እና አብሮ መኖር” የሚለውን ሰነድ “በእግዚአብሔር የሚያምኑ እና በሰው ልጆች ወንድማማችነት ላይ እምነት ያላቸው ሰዎች ሁሉ እንዲተባበሩ እና አብረው እንዲሰሩ እና የሰው ልጆችን ሁሉ ወንድማማች እና እህትማማች የሚያደርግ መለኮታዊ ጸጋ እንዲኖራቸው የሚጋብዝ ሰነድ ጽፈው ነበር። 

እ.አ.አ. በ2020 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የተሻለ ፣ የበለጠ ፍትሃዊ እና ሠላማዊ ዓለምን ለመገንባት የወንድማማችነትን ፍቅር እና የማህበራዊ ወዳጅነት መልእክት ለማሰራጨት ‘ኢንሳይክሊካል ፍራቴሊ ቱቲ’ (ሁላችንም ወንድማማቾች ነን) የሚል ደብዳቤ ጽፈዋል።

በቅርቡም ሰኔ 3 2015 ዓ.ም. 30 የሚጠጉ የኖቤል የሠላም ተሸላሚዎች በቫቲካን ተሰብስበው በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ለሁሉም እኩል ክብር የሚሰጠውን “የወንድማማችነት ጥያቄያችንን እንዲቀበሉ” የሚናገረውን የሰብአዊ ወንድማማችነት ሰነድ ለማዘጋጀት እና ለማቅረብ እንደ ነበር ይታወቃ።

 

16 June 2023, 15:52