ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የሐይማኖት ተቋማት ለዓለም ሰላምና መግባባት ቁልፍ ሚና አላቸው ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በካዛኪስታን ዋና ከተማ ኑር-ሱልጣን በተካሄደው 7ኛው የዓለም እና የባህላዊ ሃይማኖቶች መሪዎች ጉባኤ ባደረጉት ንግግር ሃይማኖቶች ለዓለም ሰላም ጥማት እና በእያንዳንዱ ልብ ውስጥ ለሚኖረው ወሰን የለሽ ጥያቄ እንዴት በወዳጅነት ማደግ እና ሰላምን መፍጠር እንደሚችሉ እንዲሁም ሊያበረክቱት የሚችሉትን ሚና ላይ አስምረው ተናግረዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በካዛክስታን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የሚያደርጉ ጉብኝት መርሐ ግብር ላይ የመጀመሪያው ትልቅ ዝግጅት የተካሄደው ረቡዕ ጠዋት በሀገሪቱ ዋና ከተማ ኑር-ሱልጣን በ 7 ኛው የዓለም እና ባህላዊ ሃይማኖቶች መሪዎች ጉባኤ ላይ ለተሳታፊዎች ንግግር ማደረግ ነበር።

በየሦስት ዓመቱ የሚካሄደው የሁለት ቀናት ስብሰባ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተውጣጡ የሀይማኖት አባቶችን በማሰባሰብ በዚህ ወቅት የሃይማኖት መሪዎች በድህረ-ወረርሽኝ አለም መንፈሳዊ እና ማህበራዊ እድገትን ማጎልበት በሚችሉበት ጉዳይ ላይ አትኩረው ይነጋገራሉ። ከ100 የሚበልጡ ከ50 ሀገራት የተውጣጡ ልዑካን በሸንጎ ላይ እየተሳተፉ ሲሆን የሀይማኖት፣ የባህል፣ የሲቪል፣ የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ይገኙበታል።

በወሰን አልባነት የተሳሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የሀገሪቱ ማለትም የካዛክስታን ፕሬዝዳንት ካሲም-ጆማርት ቶካዬቭ ባደረጉላቸው ግብዣ መሰረት በዚህ ስብሰባ ላይ በግል ለመሳተፍ ወደ ካዛኪስታን ተጉዘዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለሸንጎው ባደረጉት ንግግር ሁሉንም ሰው "ወንድሞች እና እህቶች ... የአንድ ሰማይ  ልጆች እንድንሆን በሚያደርገን ወንድማማችነት ስም" በማለት ጀመሩ። “የምያሻግረንና የሚማርከን ከማያልቀው ምስጢር በፊት ሃይማኖቶች ፍጡራን መሆናችንን ያስታውሱናል...ሁሉን ቻይ እንዳልሆንን... ወደ አንድ ሰማያዊ ግብ የምንጓዝ” ሰዎች መሆናችንን ሐይማኖት ያስታውሰናል በማለት ተናግሯል።

ይህ የጋራ ተፈጥሮ በተፈጥሮው “የጋራ ትስስር፣ እውነተኛ ወንድማማችነት” ይፈጥራል ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በታሪክ ዘመናት ሁሉ የካዛክስታን የመካከለኛው እስያ ሀገር እንዴት እንደ ጥንቱ የሐር መንገድ ሀሳቦችን፣ እምነቶችን እና ንግድን ያካተተ የግጭት ምድር እንደነበረች አስታውሰዋል።

የሃይማኖቶች ገጠመኝ ሁሌም በሰዎች ግንኙነት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን "በመከባበር፣ በቅንነት መወያየት፣ የእያንዳንዱን ሰው የማይደፈር ክብር ማክበር እና መተባበር" የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ትክክለኛ ሃይማኖታዊነት

በንግግራቸው ሁሉ የካዛኪስታንን በጣም ታዋቂ ገጣሚ እና የዘመናችን ሥነ ጽሑፍ አባት አባይ (1845-1904) (ኢብራሂም (አባይ) ኩናንባይዩሊ) የካዛኪስታን ገጣሚ፣ አቀናባሪ እና የሃይማኖት ምሁር እንዲሁም ፈላስፋ ነበር። በብሩህ እስልምና መሰረት ወደ አውሮፓ እና ሩሲያ ባህሎች የባህል ለውጥ አራማጅም ነበር። በካዛኪስታን ሕዝቦች መካከል በቀላሉ አባይ በመባል ይታወቃል) ጽሑፎቹ ጥልቅ ሃይማኖታዊ ቁርጠኝነትን እና “የዚህን ሕዝብ ክቡር ነፍስ” የሚያንፀባርቁ መሆናቸውን ጠቅሷል።

አባይ መንፈሳዊነትን ለማዳበር ስለ ሕይወት እና ትርጉም ያላቸውን የመጨረሻ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ እንዴት እንደተናገረ ያስታወሱት እና እርሱን በመጥቀስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህ "ነፍስ ሕያው እና አእምሮን ንጹሕ ያደርገዋል" ብለዋል እናም ሰዎች በእምነት ሰዎች ላይ "የነፍስ ምሳሌ" እንደሆኑ ተናግረዋል ። ሕያው እና አእምሮዎች ግልጽ" እንዲሁም "ትክክለኛ ሃይማኖታዊነት" የሚያንፀባርቁ ናቸው በማለት ተናግረዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሐይማኖት አክራሪነት "እያንዳንዱን የእምነት መገለጫ ያረክሳል እና ያበላሻል" እናም "ክፍት እና ሩህሩህ ልብ ሊኖረን ይገባል" ሲሉ አስታውሰዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል . . .

“የወንድማማችነት ልዕልና እና የተቀደሰ እሴት ማሳደድ በመልካ ምድራዊ ፖለቲካ፣ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚ፣ በሥነ-ምህዳር፣ ነገር ግን በመሠረታዊ መንፈሳዊ ቀውሶች መካከል መወሰድ ያለባቸውን ውሳኔዎች ዲሞክራሲን ጨምሮ ብዙ ዘመናዊ ተቋማት በአሁኑ ጊዜ እያጋጠሟቸው ያሉትን ውሳኔዎች ሊያነሳሳ እና ሊያበራ የሚችሉ ቢሆንም ነገር ግን በህዝቦች መካከል ደህንነትን እና ስምምነትን መጉዳት የለበትም። ለዓለም ሰላም ጥማት እና በእያንዳንዱ ወንድና ሴት ልብ ውስጥ ለሚኖረው ወሰን የለሽ ጥማት ምላሽ ለመስጠት ሃይማኖት እንፈልጋለን”።

የሃይማኖት ነፃነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመቀጠል የሀይማኖት ነፃነት አስፈላጊነት "ለእውነተኛ ሰብአዊ እና አጠቃላይ እድገት አስፈላጊ ሁኔታ" ነው ሲሉ ገልጸዋል። በነጻነት የተፈጠረ፣ ማንኛውም ሰው “ለእምነቱ ወይም ለሷ እምነት ማንም ሳያስገድድ በአደባባይ ምስክርነቱን የመስጠት” መብት አለው በማለት አክለው ገልጸዋል።

በድህረ-ወረርሽኝ ዓለም ውስጥ መንፈሳዊ እና ማህበራዊ ድጋፍን እንዴት መስጠት እንዳለብን በዚህ ሸንጎ መሪ ሃሳብ ላይ በማንፀባረቅ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሁላችንም የሚያጋጥሙንን አራት ፈተናዎች ላይ ያተኮሩ ሲሆን በልዩ ሁኔታ ሃይማኖቶች ወደ ታላቅ የዓላማ አንድነት እንድንመጣ እንዲሰሩ አሳስበዋል።

ተጋላጭነት እና ኃላፊነት

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሁሉንም ሰው “በተመሳሳይ ጀልባ ውስጥ አስቀመጠ” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የጋራ ተጋላጭነታችንን እና የእርዳታ ፍላጎታችንን እንዴት እንዳጋለጠ ተናግረዋል ።

ወረርሽኙ ያስከተለውን “ኃይለኛ የአብሮነት ስሜት” አወድሰዋል፣ ነገር ግን ይህን ስሜት ማባከን እንደሌለብን አስጠንቅቀዋል። እዚህ ላይ ሀይማኖቶች "ሰብዓዊ ቤተሰባችንን የበለጠ ሊከፋፍሉ በሚችሉ ከባድ ፈተናዎች ውስጥ የአንድነት አራማጆች በመሆን ግንባር ላይ እንዲገኙ ተጠርተዋል" ብሏል።

"በአሁኑ ጊዜ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የእኛን ተጋላጭነት እንዳይረሱ መርዳት የእኛ በመለኮት የምናምን ሰዎች ኃላፊነት ነው...በአንድ ቃል ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት የተፈጠረው የጋራ የተጋላጭነት ስሜት ወደ ፊት እንድንሄድ ሊያነሳሳን ይገባል" እንደቀድሞው ሳይሆን አሁን በትህትናና አርቆ አስተዋይነት መጓዝ ይኖርብናል”።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠልም አማኞች የሰው ልጆችን "እንዲንከባከቡ ተጠርተዋል" እናም "የኅብረት ጥበብ ባለሙያዎች፣ ከማህበረሰባችን፣ ከጎሳ፣ ከሀገራዊ እና ከሃይማኖታዊ ግንኙነቶች ወሰን በላይ የሆነ ትብብር ምስክሮች" ይሆናሉ ያሉ ሲሆን “በዝምታ እና በአጠቃላይ ግድየለሽነት” እየተሰቃዩ የሚገኙትን ድሆችን፣ ችላ የተባሉትን እና ረዳት የሌላቸውን ሰዎች መርዳት በማዳመጥ ይጀምራል ብለዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል . . .

እኔ የማቀርበው ለላቀ ትኩረት እና ትብብር ብቻ ሳይሆን ለህብረተሰባችን የፈውስ መንገድም ነው። በድህነት እና በእኩልነት ላይ የሚንፀባረቁትን ወረርሽኞች እና ሌሎች ታላላቅ ክፋቶች እንዲስፋፉ የሚረዳው ድህነት ነውና።

የሰላም ተግዳሮት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ያጎሉት ሁለተኛው ዓለም አቀፍ ፈተና የሰላም ተግዳሮት ነው።

በተለይ ከቅርብ አሥርተ ዓመታት ወዲህ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች  የተወያዩበት ቢሆንም የጦርነትና የግጭት መቅሰፍት አሁንም ዓለምን እያስጨነቀ መሆኑን ተመልክቷል። ይህም በዘመናችን ያሉ ሰዎች በአክብሮት እና ኃላፊነት የተሞላበት ውይይት ለማድረግ እንዲነሳሱ ከተፈለገ በታላላቅ ሀይማኖቶች ውስጥ በንቃት ለመሰባሰብ እና ለሰላም ቅድሚያ በመሰጠት "ወደ ፊት መዝለል" ይጠይቃል ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ። አክለውም . . .

"እግዚአብሔር ሰላም ነው። እሱ ሁል ጊዜ በሰላም መንገድ ይመራናል እንጂ በጦርነት መንገድ አይመራንም። እንግዲያውስ፣ ግጭቶችን በኃይልና በማያዳግም መንገድ፣ በትጥቅና ዛቻ ሳይሆን፣ በሰማይ በተባረከና ለሰው በተገባ ብቸኛ መንገድ፣ መገናኘት፣ መነጋገር እና በትዕግስት ድርድር መፍታት እንደሚያስፈልግ አምነን ራሳችንን እንስጥ። በተለይም ወጣቱን እና መጪውን ትውልድ ከግምት ውስጥ በማስገባት እድገትን የሚያቀላጥፉ ተግባራትን እንደግፍ... በዚህ ላይ መዋለ ነዋይ እናፍሥሥ ፣ እማጸናችኋለሁ፣ በዚህ ላይ ብዙ የጦር መሳሪያ ሳይሆን ብዙ ትምህርት መስጠት አስፈላጊ ነው!”

በወንድማማችነት መንፈስ መቀባበል

ሦስተኛው ፈተና የሚገጥመን “በወንድማማችነትን መንፈስ መቀባበል ነው” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በየእለቱ “ልጆች፣ የተወለዱና ያልተወለዱ፣ ስደተኞችና አረጋውያን እንዴት እንደሚጣሉ እና እንደ ሚገለሉ እንመለከታለን...ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው የተቀደሰ ነው” በማለት አስረድተዋል።

በተለይም በጦርነት፣ በድህነት እና በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የብዙ ሰዎችን ስደት በማስታወስ ይህንን ዓለም ማስታወስ የሃይማኖቶች ተግባር ነው ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ። “እያንዳንዱን ፍጡራኑን የሚከታተል ፈጣሪ ሌሎችን እንደ እርሱ እንድንመለከት እና በእነርሱም ውስጥ የወንድም ወይም የእህት ፊት እንድናይ እንደሚመክረን ልብ ልንል ይገባል” ብሏል።

“የእንግዳ ተቀባይነት፣ የመቀበል፣ የመተሳሰብ ጥበብን እንደገና መልሰን እንቀናጅ። እናም ማፈርንም እንማር፡ አዎን፣ ለሚሰቃዩት ርህራሄ፣ ምሕረት እና ለሁኔታቸው እና እጣ ፈንታቸው በመጨነቅ የተወለደውን ጤናማ ሀፍረት መለማመድ ያስፈልጋል፣ እኛም የምንካፈለውን እንገነዘባለን። የሰው ልጆች የተሻልን አማኞች እንድንሆን የሚያደርገን ይህ የርህራሄ መንገድ ነው”።

የጋራ የመኖሪያ ቤታችንን እንከባከብ

ሁላችንም የሚያጋጥመን የመጨረሻው ፈተና "ለጋራ ቤታችን እንክብካቤ" እና የተፈጥሮ አካባቢን ከብክለት፣ ብዝበዛ እና ውድመት ከመጉዳት እንጠብቅ” የሚለው እንደ ሆነ በመግለጽ የተገሩት ቅዱስነታቸው “የብዝበዛ አስተሳሰብ” የጋራ ቤታችንን እያፈራረሰ “ፈጣሪ የፈቀደውን የዓለምን የተከበረና ሃይማኖታዊ ራዕይ ወደ ግርዶሽ ውስጥ እየከተተው ነው” ብለዋል።

14 September 2022, 15:48