ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በ16ኛው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሲንዶስ ላይ ሲሳተፉ የሚያሳይ ምስል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በ16ኛው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሲንዶስ ላይ ሲሳተፉ የሚያሳይ ምስል  (Vatican Media)

ካርዲናል ሆለሪች የክፍል B2 የሲኖዶስ መጀመሪያ ጉባሄ ላይ ያደረጉት የመግቢያ ንግግር

በሲኖዶሱ ስምንተኛው ቀን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሲኖዶሱ ዋና አስተዳዳሪ ብፁዕ ካርዲናል ዣን ክላውድ ሆሌሪች “በተልዕኮ ውስጥ የጋራ ኃላፊነት” በሚል ርዕስ በላቲን ቋንቋ Instrumentum Laboris የሥራ መርዓ ግብር ክፍል B2 አስተዋውቀዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በብፁዕ ካርዲናል ዣን ክላውድ ሆለሪች

ሁላችሁም እንደምን አደራችሁ፣ እናም እንደገና አብረን መሄድ ለመጀመር ዝግጁ በሆን ወደ አዳራሻችን እንኳን በደህና መጣችሁ። ቀኑን ሙሉ እንድንቀመጥ ስለሚያደርገን ጉዟችን እንግዳ ነው። ሆኖም ወደ ኋላ መለስ ብለን ብናስብ፣ በማኅበረ ቅዱሳን የተገናኘንበትን ቀን እያሰብን - ሁለት ሳምንታት እንኳን አላለፉም! - እንደማስበው ሁላችንም አንድ ላይ እንደተራመድን እና ረጅም መንገድ እንደሄድን የምንስማማ ይመስለኛል።

በአካል ትላንት በሃይማኖታችን አንድ ላይ ተጉዘናል ይህም ከቀደምት ማህበረሰብ ክርስቲያኖች እና በተለይም ከሰማዕታቱ ጋር እንድንገናኝ አስችሎናል እናም እምነት እንዲኖረን ነፍሳቸውን ከሰጡን ቅዱሳን ጋር ማለት ነው። በአንድ ጌታ ላይ ያለው ይህ እምነት ከእነሱ ጋር አንድ ያደርገናል፣ እኛ የአንድ ቤተ ክርስቲያን አካል ነን፣ እናም አንድ አይነት ተልእኮ እንካፈላለን፡ የወንጌልን መልካም ዜና፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር እና ምሕረት ለሰው ልጆች እና ለፍጥረት ሁሉ ለዓለም እናውጅ። በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ መስዋተ ቅዳሴን በቅዱስ ቁርባን እንደተካፈልነው ከእኛ በፊት የሄዱት ሰማዕታትና ምእመናን ከእኛ ጋር ናቸው። ጸሎታቸው ይደግፈናል፣ እና ከእኛ ጋር ሲራመዱ ይሰማናል፡ ሲኖዶሱ መላውን ቤተክርስቲያን ያካትታል፣ ይህም በሁሉም ቦታ እና ጊዜ በክርስቶስ የምያምኑትን አማኞችን ያካትታል። ቤተ ክርስቲያን በዘመናት ሁሉ የእግዚአብሔር ሕዝብ እንደመሆኗ መጠን እንደ እስራኤል ሕዝብ በምድረ በዳ መና ያስፈልጋታል። እኛ ግን ከመና የሚበልጥ ነገር አለን: ተሰቅለናል ተነሥተናል ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት ፈጥረናል።

ከመላው ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር፣ ለቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ወደ ተዘጋጀው ስራ አሁን እንገባለን፣ ሦስተኛው የሥራ ክፍል በላቲን ቋንቋ Instrumentum laboris ክፍል B2 (የሥራ መርሃ ግብር) ጀምረናል። አስቀድመን እንደተማርነው እያንዳንዱ ክፍል እና ስለዚህ እያንዳንዱ ምዕራፍ ርዕስ አለው፣ ከጥያቄ ጋር ተያይዞ ከመባከን ለመዳን ትኩረታችንን የት ማድረግ እንዳለብን ያሳየናል። በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የሚመራን ርዕስ እና ጥያቄ፡- “በተልእኮ ውስጥ የጋራ ኃላፊነት፡ በወንጌል አገልግሎት ውስጥ ስጦታዎችን እና ተግባሮችን እንዴት በተሻለ መንገድ ማካፈል እንችላለን?” የሚሉት ናቸው።

የእኛ ጭብጥ ስለዚህ ተልዕኮ ነው። በሲኖዶሳዊው ሂደት በሁሉም እርከኖች “ሲኖዶሳዊ ቤተ ክርስቲያን በተልእኮ ላይ ያላች ቤተ ክርስቲያን ናት” ተብሎ በግልጽ ተነግሯል።

በጉዞአችን የተልእኮውን ጭብጥ ስንገናኝ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በተቃራኒው በሁለተኛው መዕራፍ ወይም ክፍል ሥራ ውስጥ ያለማቋረጥ ብቅ አለ፣ ሕብረት በራሱ አልተዘጋም ነገር ግን ወደ ተልእኮ ይገፋፋል፣ በተመሳሳይ ጊዜ፣ የተልእኮ ዓላማ የኅብረት ወሰንን ለማራዘም፣ ብዙ ሰዎች ጌታን እንዲገናኙ እና የሕዝቡ አካል እንዲሆኑ ጥሪውን እንዲቀበሉ ማስቻል ነው።

ካለፉት ጥቂት ቀናት ሥራ፣ በተልእኮ ላይ የምናሰላስልበትን አመለካከት ለማጉላት አንድ ምሳሌ መውሰድ እንችላለን። ብዙ ተናጋሪዎች ስለ "ዲጂታል አህጉር" ተናግረዋል። ብዙዎቻችን ኢንተርኔትን በቀላሉ ለወንጌል መስበኪያ መሳሪያ አድርገን እናያለን። ከዚህም በላይ ነው። አኗኗራችንን፣ እውነታውን የማወቅ እና የኑሮ ግንኙነቶችን ይለውጣል። ስለዚህ አዲስ የተልእኮ ክልል ይሆናል።

ፍራንችስኮስ ዣቪየር ወደ አዲስ አገሮች እንደሄደ፣ ወደዚያ አዲስ አህጉር በመርከብ ለመጓዝ ፍቃደኛ እና ዝግጁ ነን? አብዛኞቻችን በእነዚህ አዲስ የተልእኮ አውዶች መመሪያ መሆን አንችልም ... በዲጂታል አህጉር በሚኖሩ ሰዎች መመራት አለብን? በአብዛኛው እኛ ኤጲስ ቆጶሳት የዚህ ተልእኮ ፈር ቀዳጆች አይደለንም፣ ነገር ግን በታናናሾቹ የእግዚአብሔር ሕዝብ አባላት በተከፈተው መንገድ የምንማራቸው ነገሮች ናቸው። ስለዚህ ጉዳይ ሌላ ጊዜ እንሰማለን። ያም ሆነ ይህ፣ ይህ ምሳሌ ርዕሳችን ለምን ስለ ተልእኮ የጋራ ኃላፊነት እንደሚናገር እንድንገነዘብ ይረዳናል፡ ሁሉም የተጠመቁ ሰዎች ተጠርተዋል እናም በቤተክርስቲያኗ ተልዕኮ ውስጥ የመሳተፍ መብት አላቸው፣ ሁሉም የማይተካ አስተዋፅኦ አላቸው። ለዲጂታል አህጉር እውነት የሆነው ለሌሎች የቤተክርስቲያኑ ተልእኮ ገፅታዎችም እውነት ነው።

ይህ ለክፍል B2 አምስቱ የስራ ሉሆች የተቀመጡበት አድማስ ነው። እያንዳንዱ ቡድን ከመካከላቸው አንዱን ብቻ ያነጋግራል፣ በሌሎች በላቲን ቋንቋ ቺርኮሊስ ሚኖሪስ (በአናሳ የጠረጴዛ ዚሪያ የተሰበሰቡ ቡድኖች) ስራ በሌሎች የስራ ሉሆች ላይ እምነት፣ ፍሬዎቹ በምልአተ ጉባኤው የምንካፈልባቸው ናቸው። የመጀመሪያው ሉህ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ በብዙ ቋንቋዎች እና ምስሎች የሚተላለፈውን የተልእኮውን ትርጉም እና ይዘት በጥልቀት የመመልከት አስፈላጊነትን ይመለከታል። በስጦታ እንድንቀበል የተጠራንበት ተጨማሪ ልዩነት ነው ሀብታም የሚያደርገን። የቤተክርስቲያን ተልእኮ በክሪክ ቋንቋ ከኬሪግማ (መስበክ) ጀምሮ ወንጌልን ማወጅ ነው። ይህ ተልእኮ በከንፈሮቻችን ብቻ የተገደበ ሳይሆን በእለት ተእለት ህይወታችን ልዩ ልዩ ገጽታዎች ውስጥ መታየት አለበት። የቤተክርስቲያኒቱ ተልእኮ የአጠቃላይ ሥነ-ምህዳር፣ ለፍትህ እና ለሰላም የሚደረግ ትግል፣ ለድሆች እና ለዳርቻው ተመራጭ አማራጭ እና ከሁሉም ጋር ለመገናኘት ክፍት መሆን ቁርጠኝነት ነው።

ሁለተኛው ሉህ የሚያተኩረው በቤተክርስቲያን ውስጥ ባለው አገልግሎት ላይ ነው። አሁንም አንዳንድ ምስክርነቶችን እንሰማለን። በሌሎቹ ሶስት የስራ ሉሆች ላይ ትንሽ ልቆይ እፈልጋለሁ፣ ምክንያቱም እንደ እኛ ያለ ጉባኤ ከእነሱ ጋር ሲገናኝ በጣም መጠንቀቅ አለበት። እንደ እግዚአብሔር ሕዝብ አባላት፣ ሁሉም በላቲን ቋንቋ የInstrumentum laboris (የሥራ መርሃ ግብር) ጭብጦች እኛን በቅርበት ያሳስበናል እናም ይነካናል። ነገር ግን እነዚህ ሦስቱ በተለየ መንገድ ይሠራሉ። እንደ እውነቱ ከሆነ እነዚህን ሦስት ጭብጦች በተመለከተ፣ እያንዳንዳችን አስፈላጊ የሆነውን የአመለካከት ተሸካሚዎች ነን፣ ነገር ግን ጭብጡን በብቃት ለመፍታት፣ የራሳችንን አድልዎ እንድንገነዘብም ተጠርተናል። ይህን ስል ምን ማለቴ እንደሆነ ለመረዳት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ሶስቱን የስራ ሉሆች መከለስ ነው።

አብዛኞቻችን ወንዶች ነን። ነገር ግን ወንዶች እና ሴቶች አንድ ጥምቀት እና አንድ መንፈስ ይቀበላሉ። የሴቶች ጥምቀት ከወንዶች ጥምቀት ያነሰ አይደለም። ሴቶች የዚህ ሚስዮናዊት ቤተክርስቲያን ዋነኛ አካል እንደሆኑ እንዲሰማቸው እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? እኛ ወንዶቹ መንፈስ ቅዱስ ለሴቶች የሰጣቸውን የጸጋ ስጦታዎች ልዩነት እና ብልጽግና እናስተውላለን? ወይም የምናደርጋቸው መንገዶች በአብዛኛው የተመካው ባለፈው ትምህርታችን፣ በቤተሰባችን አስተዳደግ እና ልምድ ወይም በባህላችን ጭፍን ጥላቻ እና ሰዎች ለአንድ ነገር ያላቸው ቋሚ አመልካከትና ዕውነታው ግን ሌላ የሆነ ጭፍን ጥላቻ ላይ ነው? የጋራ ተልእኮአችንን ስንካፈል እና ሴቶች በቤተክርስቲያን ተልእኮ ውስጥ በጋራ ኃላፊነት ሲወጡ በጋራ ጥምቀታችን ጸጋ ላይ እንደበለፀጉ ወይም ስጋት ይሰማናል?

ወንዶች ከመሆናችን በተጨማሪ አብዛኞቻችን አገልጋይ ነን። በእግዚአብሔር ሕዝብ ውስጥ ሌሎች አካላት፣ ሌሎች መክሊቶች፣ ሌሎች ጥሪዎች እና ሌሎች አገልግሎቶችም አሉ። በተቀባ አገልግሎት እና በሌሎች የጥምቀት አገልግሎቶች መካከል ያለው ግንኙነት ምን ይመስላል? ቅዱስ ጳውሎስ የሚጠቀምበትን የሰውነት መልክ ሁላችንም እናውቃለን። ሁሉም የሰውነት ክፍሎች አስፈላጊ መሆናቸውን ለመቀበል ዝግጁ ነን? ክርስቶስ የአካል ራስ እንደሆነ እና እያንዳንዱ ክፍል ከራስ እና ከሌሎች ክፍሎች ጋር የሚዛመድ ከሆነ አካል ብቻ እንደሚሰራ ለመቀበል ዝግጁ ነን? የቤተክርስቲያናችን አካል ተስማምቶ መስራት ይችላል ወይንስ ክፍሎቹ በሁሉም አቅጣጫ እየተጣመሙ ነው?

የመጨረሻው ሉህ ጳጳሳትን ይመለከታል፣ በጌታ ፈቃድ አገልግሎታቸው የቤተክርስቲያኗን ህብረት ያዋቅራል። ለሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያን ተስማሚ በሆነ መንገድ እንዲተገበር እንዴት መታደስ እና ማስተዋወቅ አለበት? እዚህ ብዙዎቻችን ጳጳሳት ነን። ይህ ጥያቄ እኛን በተለየ መንገድ ሊፈታተን አይችልም፣ ምክንያቱም መልሱ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ይኖረዋል፣ ጊዜያችንን በምንመራበት መንገድ፣ በአጀንዳችን ቅድሚያዎች ላይ፣ የእግዚአብሔር ህዝብ ከእኛ በሚጠብቀው ነገር ላይ እና ተልእኳችንን እንዴት እንደምንፀነስ ማወቅ ይኖርብናል።

የተሳትፎን መጠን እና ጥንካሬ ጠንቅቀን ማወቅ አለብን። እናም በአንድ የተወሰነ ጥያቄ ወይም እውነታ ውስጥ በጣም ስንሳተፍ፣ ሌሎችን በእውነት ለመስማት፣ ለቃላቸው በራሳችን ውስጥ ቦታ ለመስጠት እና መንፈስ ምን እንደሚጠቁመን ለመጠየቅ የበለጠ ድፍረት እንፈልጋለን። ይህ ጳጳሳት ያልሆኑትን እና ስለዚህ የተለየ አመለካከት ያላቸውን ሰዎች የምንሰማበትን መንገድ ይመለከታል፣ ነገር ግን ሌሎች ጳጳሳትንም ጭምር ነው ምክንያቱም በመጨረሻ እያንዳንዳችን ጳጳስ የምንሆንበት የራሱ መንገድ ስላለን። የራሳችንን የጵጵስና ልምድ እና ይህ በጊዜ ሂደት እንዴት እንደተለወጠ ማካፈላችን ትልቅ እገዛ ሊሆን ይችላል።

በመንፈስ ውስጥ ያለው የንግግር ዘዴ ለእኛ ይበልጥ እየለመን ሲሄድ ለእያንዳንዳችን ቃላት ክፍተት መፍጠር በእነዚህ ቀናት ማሳደግ የምንቀጥልበት ትኩረት ነው። አስተባባሪዎች በሁለተኛው ዙር በአማካይ በአናሳ የጠረጴዛ ዙሪያዎች የበለጠ አስቸጋሪ ጊዜ እንዳላቸው ይገልጻሉ። ይህ በትክክል እያንዳንዱ ሰው የራሱን አመለካከት፣ የራሱን አስተሳሰብ ወደ ጎን በመተው ሌሎችን ማዳመጥ በውስጣቸው የሚቀሰቅሰውን ድምጽ ትኩረት ለመስጠት ለአፍታ የተጠራበት ወቅት ነው። የመጀመሪያው ዙር ማራዘሚያ ሳይሆን አዲስ ነገር ለመክፈት እድል ነው፣ በዚህ መልኩ አስበንበት የማናውቀው ነገር ነው። ይህ መንፈስ ለእያንዳንዳችን ያዘጋጀው ስጦታ ነው። ለማዳመጥም ተመሳሳይ ትኩረት በጠቅላላ ጉባኤው መቀጠል አለበት፡ ባለፉት ጥቂት ቀናት እንደምናስታውሰው፣ ነፃ ጣልቃገብነቶች ከዚህ በፊት ቡድኖቹ የሚጋሩትን ግንዛቤዎች መግለፅ አለባቸው። በዚህ ምክንያት በትናንሽ የጠረጴዛ ዙሪያዎች በሚሰባሰቡ ቡድኖች ሪፖርቶች እና የሪፖርተሮች ጣልቃገብነት የመሰብሰቢያ እና የመለያየት ነጥቦችን እየጨመረ መምጣቱ አስፈላጊ ነው ፣ ግን ከሁሉም በላይ ሊመረመሩ የሚገቡ ጥያቄዎች እና በመጪው ጊዜ የሚወሰዱ ተጨባጭ እርምጃዎች ሀሳቦች ለመጪው አመት ሲኖዶስ ግባቶች ይሆናሉ።

ከላይ እንዳየነው በዚህ ክፍል የተወሰኑትን የሲኖዶሳችንን ቁልፍ ነጥቦች እንዳስሳለን። የእነዚህን አስቸጋሪ ጥያቄዎች ገጽታ ያላገናዘበ የችኮላ መልስ አንስጥ። ልናማክራቸው የምንችላቸው የሃይማኖት ምሁራን አሉን፣ እናም እ.አ.አ በጥቅምት 2024 ሁለተኛ ክፍለ ጊዜ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ አሁን የምንለይባቸውን ጥያቄዎች ለመጸለይ እና ለመመርመር ጊዜ አለን።

ስለእያንዳንዳችን ጌታን አመሰግነዋለሁ፣ ስለግል ልምዳችን፣ አገልግሎታችንን ስለኖርን፣ የእኛ በሆነው ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ስለሄድን። ይህን አስተንትኖ እንድንቀጥል የሚረዱንንም አመሰግናለሁ፡ እናት ኢግናዚያ አንጀሊኒ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ግንዛቤዎቿ ጋር፣ ፕሮፌሰር ካርሎስ ጋሊ ከሥነ መለኮት ግንዛቤዎች ጋር፣ እናም ከነሱ በኋላ ምስክርነታቸውን ለሚሰጡ። ወደ ጭብጦች እና ጥያቄዎች በጥልቀት እንድንገባ እና ከሁሉም በላይ እነሱን ለመቅረጽ ይረዱናል። በዚህ የመግቢያ ክፍለ ጊዜ ከምንሰማው አንጻር ሁሉም ሰው ዛሬ ከሰአት በኋላ ለመጀመሪያው በትናንሽ የጠረጴዛ ዙሪያዎች በሚሰበሰቡ ቡድኖች ለሚከናው ውይይት ያዘጋጀውን ንግግር ማሻሻል ይችላል።

ለእያንዳንዳችን እና ለሁላችንም እንደ ጉባኤ መንፈስን የምንሰማበት ፍሬያማ ጊዜ እንዲሆንልን እመኛለሁ።

13 October 2023, 16:58