ፈልግ

ረቡዕ ሰኔ 23/1963 ዓ. ም. በመሰብሰቢያው አዳራሽ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ረቡዕ ሰኔ 23/1963 ዓ. ም. በመሰብሰቢያው አዳራሽ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት 

በቫቲካን ውስጥ የሚገኘው ጳውሎስ 6ኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከታነጸ 50 ዓመት ሞልቶታል

በቫቲካን ውስጥ የሚገኘው እና በቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ ስም የሚጠራው ሰፊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከዓለማችን ክፍሎች የሚመጡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ምዕመናንን፣ መንፈሳዊ ተጓዦችን እና አገር ጎብኚዎችን ሲያስተናግድ ቆይቷል። የግንባታ ሥራው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ሲደርስ አዳራሹን ሰኔ 23/1963 ዓ. ም. መርቀው ለአገልግሎት ያበቁት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ መሆናቸው ይታወቃል። ስለዚህም የመሰብሰቢያ አዳራሹ ጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ በመባል ይታወቃል። የምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳት ሳምንታዊ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮአቸውን በሚያቀርቡበት ርቡዕ ዕለት መፈጸሙ ይታወሳል።
ር. ሊ. ጳ ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ ረቡዕ ሰኔ 23/1963 ዓ. ም. የመሰብሰቢያ አዳራሹን በመረቁበት ዕለት
ር. ሊ. ጳ ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ ረቡዕ ሰኔ 23/1963 ዓ. ም. የመሰብሰቢያ አዳራሹን በመረቁበት ዕለት

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ለዚህ እጅግ ሰፊ እና ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የግንባታ ንድፍ አዘጋጅተው ያቀረቡት ታዋቂው ጣሊያናዊ አርክቴክ አቶ ፔር ሉዊጂ ስለነበሩ አልፎ አልፎ "Aula Nervi" ወይም ነርቪ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እየተባለ ሲጠራ ይሰማል። አዳራሹ ባለፉት 50 ዓመታት ታሪኩ አምስት ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳት የተገለገሉበት፣ በቁጥር በርካታ ምዕመናንን፣ መንፈሳዊ ተጓዦችን እና አገር ጎብኝዎችን ወደ አዳራሹ በመጋበዝ ሳምንታዊ የጠቅላላ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምሮአቸውን ያቀረቡበት፣ መንፈሳዊ ስብሰባዎችን እና ሌሎች ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን የመሩበት ምቹ ሥፍራ ነው።

ር. ሊ. ጳ ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ ረቡዕ ሰኔ 23/1963 ዓ. ም. የመሰብሰቢያ አዳራሹን በመረቁበት ዕለት
ር. ሊ. ጳ ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ ረቡዕ ሰኔ 23/1963 ዓ. ም. የመሰብሰቢያ አዳራሹን በመረቁበት ዕለት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ ረቡዕ ሰኔ 23/1963 ዓ. ም. በመሰብሰቢያው አዳራሽ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ለተገኙት በርካታ ምዕመናን ባሰሙት ንግግር አዳራሹ የተገነባው ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳት ከሐዋርያዊ ተልዕኮዋቸው አንዱ የሆነውን ሳምንታዊ የረቡዕ ዕለት የጠቅላላ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮአቸውን ከዓለም ዙሪያ ለሚመጡት እንግዶች የሚያቀርቡበትን ምቹ ሥፍራን ለማዘጋጀት መሆኑን አስረድተዋል።

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ሳምንታዊ የረቡዕ ዕለት የጠቅላላ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮን ሲያቀርቡ
ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ሳምንታዊ የረቡዕ ዕለት የጠቅላላ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮን ሲያቀርቡ

በቫቲካን ውስጥ የሚገኘው ጳውሎስ 6ኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ከመላው የዓለማችን ክፍሎች የሚመጡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ምዕመናንን፣ መንፈሳዊ ተጓዦችን እና አገር ጎብኚዎችን ተቀብሎ ሲያስተናግድ መቆየቱ ይታወቃል። ከዚህም በላይ ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳት በሮም ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ድሃ እና መጠለያ አልባ ከሆኑ ሰዎች ጋር ማዕድ የሚካፈሉበት ሥፍራ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል። ባለፉት ቅርብ ወራትም በሮም ከተማ እና በቫቲካን ዙሪያ ለሚገኙ አቅመ ደካማ ተረጂዎች እና ለቫቲካን ተቀጣሪዎች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት ማዕከል ሆኖ ማገልገሉ ይታወሳል። የጳውሎስ 6ኛ መሰብሰቢያ አዳራሽ ሌላው አገልግሎት የመላዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የሚሰበሰብበት ቦታ መሆኑ ይታወቃል።       

06 July 2021, 14:45