ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የኢትዮጲያ ጠ/ ሚኒስትር ከሆኑት ከዶ/ር አብይ ጋር በቫቲካን ተገናኙ። ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የኢትዮጲያ ጠ/ ሚኒስትር ከሆኑት ከዶ/ር አብይ ጋር በቫቲካን ተገናኙ። 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከኢትዮጲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ጋር በቫቲካን ተገናኙ

“በኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ ውስጥ የክርስትና እምነት የተጫወተውን ከፍተኛ የሆነ ሚና በመዘርዘር እና በኢትዮጲያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ተቋማት በትምህርት እና የጤና ዘርፍ እያበረከቱ የሚገኙትን አስተዋጾ” አንስተው መነጋገራቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብልክ ጠቅላይ ሚንስትር የሆኑት ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ በቫቲካን እምብርት ውስጥ የሚገኘውን የኢትዮጲያ ኮሌጅ ከጎበኙ በኋላ በዚያው በቫቲካን ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸሶስ ጋር መገናኘታቸውን እና በግል መወያየታቸው ተገለጸ። በግንኙነታቸው ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ያደርጉት ውይይት ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በኢትዮጲያ እና በኤርትራ መካከል በቅርቡ ተደርጎ ስለነበረው የሰላም ስምምነት እና በአጠቅላይ የአፍሪካን እድገት በተመለከተ መወያየታቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና የሚያስረዳ ሲሆን ኢትዮጲያ በጠቅላይ ሚንስትር በዶክተር አብይ መሪነት በሁለቱ አገራት መካከል ሰላም እንዲፈጠር፣ ብሎም በጠቅላላው በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ሰላም እንዲረጋገጥ ጠቅላይ ሚንስትሩ እያበረከቱት ለሚገኘው አስተዋጾ ቅዱስነታቸው ምስጋና ማቅረባቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
የኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚንስተር የሆኑት ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ በበኩላቸው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጲያ በትህምርት እና በጤና ዘርፍ እያበረከተች የምትገኘውን ከፍተኛ አስተዋጾ ማድነቃቸውን ለመረዳት ተችሎዋል።
በመቀጠል የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክ ጠቅላይ ሚንስትር የሆኑት ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ ውይይት ትኩረቱን አድርጎ የነበረው “ኢትዮጲያ በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ሰላም ይረጋገጥ ዘንድ ልታበረክተው ስለምትችለው አስተዋጾ” አንስተው መነጋገራቸው በተለይ ለቫቲካን ዜና ከደረሰው መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በአጠቅላይ ደግሞ በአፍሪካ አህጉር ሰላምን በማረጋገጥ፣ ግጭቶችን በሰላማዊ መልኩ በመፍታት ኢኮኖሚያዊ እድገትን እንዴት ማረጋገጥ እንደ ሚቻል ጨመረው መነጋገራቸውን ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።
የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክ ጠቅላይ ሚንስትር የሆኑት ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ በተገናኙበት ወቅት በተጨማሪም "በኢትዮጲያ ብሔራዊ እርቅ ይፈጠር ዘንድና እንዲሁም በሀገሪቱ ሁለንተናዊ የሆነ ዕድገት ለማምጣት አስፈላጊ የሆኑ ቀጣይ እርምጃዎች ላይ” ጠቅለል ባለ ሁኔታ ውይይት ማደርጋቸው የተገለጸ ሲሆን “በኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ ውስጥ የክርስትና እምነት የተጫወተውን ከፍተኛ የሆነ ሚና በመዘርዘር እና በኢትዮጲያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ተቋማት በትምህርት እና የጤና ዘርፍ እያበረከቱ የሚገኙትን አስተዋጾ” አንስተው መነጋገራቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክ ጠቅላይ ሚንስትር የሆኑት ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ በውይይታቸው ማብቂያ ላይ ስጦታዎችን መቀያየራቸው የታወቀ ሲሆን በዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው ለጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያቀረቡት ስጦታ ያቅረቡትም ስጦታ ባለፈው ምዕተ አመት አንድ ሰዓሊ በበረሃ ውስጥ የወይን ተክል ስያብብ የሚያሳይ ስዕል ቅዱስነታቸው ማበርከታቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ትርጉሙም “ በረሃው አንድ ቀን ለምለም ይሆናል” ከሚለው ከነቢዩ ኢሳያስ ታሪክ ጋር እንደ ሚገናኝ በማውሳት ቅዱስነታቸው በወቅቱ ማብራሪያ መስጠታቸው ተገሉጹዋል። ቅዱስነታቸው በመቀጠል ለጠቅላይ ሚንስትሩ ያቀረቡት ስጦታ እርሳቸው በርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው ከጻፏዋቸው በርካት ሐዋሪያዊ መልእክቶች እና ቃለ ምዕዳኖች መካከል እንደ ነበረ በወቅቱ የተገለጸ ሲሆን በዚህም መሰረት በላቲን ቋንቋ “Evangelii Gaudium” አማሪኛው በግርዱ ሲተረጎም በቅዱስ ወንጌል የሚገኝ ደስታ “ Laudato si” ውዳሴ ላንተ ይሁን በሚል አርእስት የተጻፈ እና የጋራ መኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን እንዴት መንከባከብ እንደ ሚገባን የሚያወሳም “Gaudete et Exultate” ደስ ይባላችሁ ሐሴትም አድርጉ በሚል አርእስት የተጻፈ እና እለት በእለት በምንፈጻማቸው ጥቃቅን ተግባራት ለምሳሌም እባክህን፣ ይቅርታ እና አመስግናለሁ የሚሉትን እለታዊ የሆኑ ቀለል ያሉ ቅላትን በመጠቀም ወደ ቅድስና የሚወስደውን መንገድ መጀመር እንደ ሚቻል የሚገልጸው ቃለ ምዕዳን፣ Amoris Laetitia በፍቅር የሚገኝ ሐሴት በሚል አርእስት የተጻፈ እና በቤተሰብ ውስጥ ፍቅር ከፈተኛ የሆነ ሚና እንደ ሚጫወት፣ በቤተሰብ ውስጥ ችግር ሲፈጠር የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች በችኮላ ውሳኔ ከማድረጋቸው በፊት ሁኔታውን በጥንቃቄ በመገምገም ለችግሮች ሁሉ በመለኮታዊ ምሕረት የተሞላ ውሳኔ ማድረግ እንደ ሚገባ፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ትዳርን በተመለከተ በቂ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ ተመጣጣኝ የሆነ እውቀት መገብየት የሚያስችላችው ሁኔታዎች እንዲመቻቹ የሚያሳስብ መልእክት እንደ ሚገኙበት ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል። በመጨረሻም የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ ማኅበርሰቦች ዘንድ ባላፈው ጥር 1/2019 ዓ.ም የተጀመረውን አዲስ አመት ምክንያት በማድረግ ለተከበረው 52ኛው ዓለማቀፍ የሰላም ቀን ይሆን ዘንድ ቅዱስነታቸው “መልካም ፖለቲካ ለሰላም” በሚል አርእስት ያስተላለፉትን መልእክት ጨምሮ ለክቡር ጠቅላይ ሚንስተር ዶክተር አብይ አመድ በስጦታ መልክ መስጠኣቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
ጠቅላይ ሚንስተር ክቡር ዶክተር አብይ አመድ በበኩላቸው ለቅዱስነታቸው ያቀረቡት ስጦታ የኢትዮጲያን ባሕል መገለጫ የባሕል ልብስ ጋቢ በስጦታ ለቅዱስነታቸው ማቀረባቸውን ለመረዳት ተችሎዋል።
ጠቅላይ ሚንስተር ክቡር ዶክተር አብይ አመድ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር ከነበራቸው ቆያታ በመቀጠል በቫቲካን የቅድስት መነበር ዋና ጸሐፊ ከሆኑት ከካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ጋር ቆያት ማድረጋቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በወቅቱ ባደረጉት ውይይት የጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 2018 ዓ.ም ማብቂያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለዲፕሎማቶች ባደረጉት ንግግራቸው ስለ ሰላምና ስላምን ስለመገንባት ቅዱስነታቸው ተናግረው እንደ ነበረ ያስታወሱት ካርዲናል ጴትሮ ፓሮሊን ባለፈው ዓመት (2018) በአንዳንድ አገሮች ዘንድ የሰላም ምልክቶች መታየቱን አስታውሰው በኢትዮጵያና በኤርትራ መንግሥታት እንዲሁም በደቡብ ሱዳን መሪዎች መካከል የተፈራረሙትን የሰላም ስምምነቶችን እንደ ምሳሌ ጠቅሰው በሁለቱ ኮሪያዎች መካከልም መልካም የሰላም ምልክት መታየቱን ተናግረው እንደ ነበረ በማስታወስ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስተር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ በቫቲካን ስለነበራቸው ቆያት መደሰታቸውን ገለጸው እና አመስግነው የቫቲካን ጉብኝታቸውን ማጠናቀቃቸው ታውቁዋል።


 

Photogallery

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የኢትዮጲያ ጠ/ ሚኒስትር ከሆኑት ከዶ/ር አብይ ጋር በቫቲካን ተገናኙ።
22 January 2019, 16:02