ፈልግ

ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አመድ በቫቲካን የሚገኘውን የኢትዮጲያ ኮሌጅ በጎበኙበት ወቅት ከብጹዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ የክብር አቀባበል ሲደረግላቸው ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አመድ በቫቲካን የሚገኘውን የኢትዮጲያ ኮሌጅ በጎበኙበት ወቅት ከብጹዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ የክብር አቀባበል ሲደረግላቸው  

ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በቫቲካን የሚገኘውን የኢትዮጲያ ኮሌጅ ጎበኙ

ይህ ኮሌጅ በዚህ ስፍራ መገኘቱ የአገራችንን ታላቅነት እና የሕዝቦቹዋን እምነት መግለጫ ነው። ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር እንዲሁም ደግሞ ከቅድስት መንበር ጋር ያለንን ቅርበትና ግንኙነት ማሳያ ነው።

የኢትዮጲያው ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክር አብይ አህምድ በጥር 13/2011 ዓ.ም በጣሊያን ይፋዊ ጉብኝት አድርገው እንደ ነበረ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ከጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ከጁሴፔ ኮንቴ ጋር ከነበራቸው ቆይታ በመቀጠል በቫቲካን እንብር ውስጥ የሚገኘውን የኢትዮጲያ ኮሌጅ (የቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም) መጎብኘታቸው ታውቁዋል።
የዚህ ዘገባ አዘጋጅ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በሮም ሰዓት አቆጣጥ ከሰዓት በኋላ 3፡30 አከባቢ ከኢትዮጲያ የመጡ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጽዕን ጳጳሳት ብጽዕ ካርዲና ብርሃነየሱስ ሊቃነ ጳጳስት ዘካቶሊካዊያን የኢትዮጲያ ካቶሊካዊያን ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዚዳንት፣ የአዲግራት ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ ተስፋስላሴ መድኅን፣ የመቂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡን አብርሃ ደስታ፣ የጅማ ቦንጋ አገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ ማርቆስ ገብረመድኅን፣ የሆሳህና አገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ ስዩም፣ የኢትዮጲያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ ጽሕፈት ቤት የሐዋሪያዊ ሥራ አገልግሎት መምሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ክቡር አባ ተሾመ፣ የአዲስ አገረ ስብከት ሐዋሪያዊ አገልግሎት መምሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ክቡር አባ ጴጥሮስ በርጋ እና በርካታ የኢትዮጲያ ኮሌጅ ኢትዮጲያዊያን እና ኤርትራዊያን ካህናት እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አመድ እና ከእርሳቸው ጋር አብረው ለነበሩ ለኢትዮጲያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የሆኑት ክቡር አቶ ወርቅነህ ገበየውን ጨምሮ ከስድስት የማያንሱ በተለያየ የስልጣን እርከን ላይ የሚገኙ ባለስልጣናትን ጨምሮ በጉብኝቱ መሳተፋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
ቫቲካንን በመወከል በጉብኝቱ የአቀባበል ስነ-ስረዓት ላይ የተገኙት በቅድስት መንበር የምስራቃዊያን አብያተ ክርስቲያናትን ጉዳይ በበላይነት የሚከታተለው ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ሌዎናርዶ ሳንዲሪ ጨምሮ የቀድሞ በኢትዮጲያ የቫቲካን አንባሳደር የነበሩ የእኔታ ቶማሲ ዚልቫኖ መገኘታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
በግንኙነቱ ወቅት በቅድሚያ የእንኳን ደኽና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት ብጽዕ ካርዲና ብርሃነየሱስ ሊቃነ ጳጳስት ዘካቶሊካዊያን የኢትዮጲያ ካቶሊካዊያን ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዚዳንት በወቅቱ እንደ ገለጹት “ዛሬ በዚህ ታሪካዊ ቦታ፣ አጋጣሚ እና ቀን አገናኝቶን እርሶን በክብር ለመቀበል በመታደላችን ታላቅ ደስታ ይሰማናል። እንዲሁም እርሶ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በዚህ ታሪካዊ ቦታ በቅድስት መንበር ሥር በቫቲካን እብርት ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጲያ ኮሌጅ እና ገዳም (ደብረ ቅዱስ እስጢፋኖስ) ለመጎብኘት የቀረበሎትን ጥሪ አክብረው በመምጣቶ በኢትዮጲያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እና በኢትዮጲያ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የጳጳስት ጉባሄ፣ እንዲሁም ከኢትዮጲያ እና ከኤርትራ የተውጣጡ በኮሌጁ ካህናት እና በራሴ ስም እንኳን ደህና መጡ ለማለት እወዳለሁ” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል። በወቅቱ ብጽዕ ካርዲና ብርሃነየሱስ ሊቃነ ጳጳስት ዘካቶሊካዊያን የኢትዮጲያ ካቶሊካዊያን ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዚዳንት ያስተላለፉን መመልእክት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

ክቡር የኢትዮጲያ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ
ዛሬ በዚህ ታሪካዊ ቦታ፣ አጋጣሚ እና ቀን አገናኝቶን እርሶን በክብር ለመቀበል በመታደላችን ታላቅ ደስታ ይሰማናል። እንዲሁም እርሶ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በዚህ ታሪካዊ ቦታ በቅድስት መንበር ሥር በቫቲካን እብርት ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጲያ ኮሌጅ እና ገዳም (ደብረ ቅዱስ እስጢፋኖስ) ለመጎብኘት የቀረበሎትን ጥሪ አክብረው በመምጣቶ በኢትዮጲያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እና በኢትዮጲያ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የጳጳስት ጉባሄ፣ እንዲሁም ከኢትዮጲያ እና ከኤርትራ የተውጣጡ በኮሌጁ ካህናት እና በራሴ ስም እንኳን ደህና መጡ ለማለት እወዳለሁ።
ዛሬ የዚህን የኢትዮጲያ ኮሌጅ ታሪክ በሰፊው ለመተንተን ጊዜ እና ሰዓት ስለማይፈቅድልን የዚህን የኢትዮጲያ ኮሌጅ ታሪክ በአጭሩ ለመግለጽ ይህ በቫቲካን እንብርት ውስጥ የሚገኘው ብቸኛው የኢትዮጲያ ኮሌጅ እንደ ሆነና በታሪክ ውጣ ውረድ ውስጥ ሥራውን ሳያቋርጥ ይሄው እስከ ዛሬ ድረስ ተግባሩን በማከናወን ላይ ይገኛል። ከእርሶ በፊት በተለያዩ ወቅቶች የነበሩ የኢትዮጲያ የአገር መሪዎች እና የሃይማኖት አባቶች ይህንን ታሪካዊ የኢትዮጲያ ኮሌጅ ጎብኝተዋል።
ይህ ኮሌጅ በዚህ ስፍራ መገኘቱ የአገራችንን ታላቅነት እና የሕዝቦቹዋን እምነት መግለጫ ነው። ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር እንዲሁም ደግሞ ከቅድስት መንበር ጋር ያለንን ቅርበትና ግንኙነት ማሳያ ነው።
ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ በመካከላችን ተገኝተው በክብር ልንቀበሎት ከፊቶ የሚታዩት ካህናት ኢትዮጲያዊያን እና ኤርትራዊያን ናቸው። ያለፈው ታሪካችን እንዳለ ሆኖ እስከ ዛሬ ድረስ እነዚህ ካህናት ያለምንም ልዩነት በአንድነት መንፈስ ለሁለቱ አገራት እና ሕዝቦች ሲጸልዩ እና ሲቀድሱ ቆይተው ይኸው አሁን ሁለቱም አገራት ወደ ሰላም መድረክ ተመልሰዋል። ይህንን ብርታት እና የአንድነት መንፈስ የሰጠን እግዚኣብሔር ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን። እርሶም በዚህ ጉዳይ ላይ የአንበሳውን ድርሻ እንደ ተጫወቱ ይታወቃል፣ ለዚህ ልፋቶ እግዚብሔር ይስጥልን እያልኩኝ ለተገኘው ስኬት ደግሞ እንኳን ድስ አሎት ለማለት እፈልጋለሁ።
በዚህ አጋጣሚ በሁለቱ አገራት እና ሕዝቦች መካከል የተጀመረው ግንኙነት በበለጠ ዳብሮ ወደ ቀድሞ ሰላምና ፍቅር ተመልሰን ያለፈውን በይቅርታ አልፈን፣ አዲስ ታሪክ እንድንጀምር መንገድ ስለከፈቱልን እናደንቆታለን እናመስግኖታለንም።
በአገር ውስጥ እና ከጎረቤቶቻችን ጋር ሁሉ ለአገራችን እንድገት ለሕዝቦቿ ብልጽግና ሰላም እጅግ ወሳኝ በመሆኑ እንደ ጀመሩት ሁሉ ኃይል ከመጠቀም ይልቅ “ይቅርታ እና ፍቅር ያሸንፋል” የሚለውን አቋሞን መሰረት በማድረግ ኢትዮጲያ እና ሕዝቦቿን ወደ ልማትና እድገት ከፍታ እንደ ሚመሩዋት እንተማመናለን።
እግዚኣብሔር ኢትዮጲያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ብጽዕ ካርዲና ብርሃነየሱስ
ሊቃነ ጳጳስት ዘካቶሊካዊያን
የኢትዮጲያ ካቶሊካዊያን ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዚዳንት
ጥር 13/2011 ዓ.ም
የኢትዮጲያ ኮሌጅ
ቫቲካን

 

Photogallery

ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በቫቲካን የሚገኘውን የኢትዮጲያ ኮሌጅ ጎበኙ
22 January 2019, 11:21