ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በእግዚአብሔር ፀጋ በጎ ስነ-ምግባርን መጎናጸፍ እንችላለን ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት ከቫቲካን ሆነው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደሚያደርጉ ይታወቃል። በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በመጋቢት 04/2016 ዓ.ም ያደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከእዚህ ቀደም በአዲስ መልክ ክፉ እና መልካም ስነ-ምግባር በሚል ዐብይ አርዕስት ጀምረውት ከነበረው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቀጣይ ክፍልና “በጎ ተግባር” በሚል ንዑስ አርዕስት ባደረጉት የክፍል 11 የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በእግዚአብሔር ፀጋ በጎ ስነ-ምግባርን መጎናጸፍ እንችላለን ማለታቸ ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ- ቫቲካን

በእለቱ የተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል

በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ፤ እውነት የሆነውን ሁሉ፣ ክቡር የሆነውን ሁሉ፣ ትክክል የሆነውን ሁሉ፣ ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፣ ተወዳጅ የሆነውን ሁሉ፣ መልካም የሆነውን ሁሉ፣ በጎነት ቢሆን ወይም ምስጋና እንደ እነዚህ ስላሉት ነገሮች አስቡ። ከእኔ የተማራችሁትን ወይም የተቀበላችሁትን፣ የሰማችሁትን ወይም ያያችሁትን ማናቸውንም ነገር አድርጉ፤ የሰላም አምላክም ከእናንተ ጋር ይሆናል (ፊሊጵስዮስ 4፡8-9)።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉ።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በክፉ እና መልካም ስነ-ምግባር ዙሪያ ስናደርገው የነበረውን አጠቃላይ እይታችንን ከጨረስን በኋላ፣ የመጥፎ ተግባርን  ልምድን የሚቃረን የመስታወት ምስል ለመመልከት ጊዜው አሁን ነው። የሰው ልብ ክፉ ምኞትን ሊፈጽም ይችላል፣ የሚያባብል ልብስ ለብሰው ለሚያስጎመጁ ፈተናዎች ትኩረት መስጠት ይችላል፣ ነገር ግን ይህን ሁሉ መቃወም ይችላል። ይህ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ የሰው ልጅ የተፈጠረው ለበጎነት ነው፣ እሱም በእውነት እሱን ያሟላል፣ እና ይህን ጥበብ በተግባር ላይ ማዋል ይችላል፣ ይህም አንዳንድ ዝንባሌዎች በእሱ ውስጥ ቋሚ እንዲሆኑ ያደርጋል። በዚህ አስደናቂ የኛ ዕድል ላይ ማሰላሰል በሥነ ምግባር ፍልስፍና ውስጥ ዓይነተኛ ምዕራፍ ይመሰርታል።

የሮማውያን ፈላስፋዎች በጎነትን ግሪኮች ‘aretè’ ብለው ይጠሩታል። የላቲን ቃል ከሁሉም በላይ በጎ ሰው ጠንካራ፣ ደፋር፣ ተግሣጽ እና ግላዊ የስነ-ምግባር ችሎታ ያለው መሆኑን ያጎላል፣ ስለዚህ በጎነትን መለማመድ ጥረትን አልፎ ተርፎም መከራን የሚጠይቅ በረጅም ጊዜ እንደሚበቅል ፍሬ ነው። “አሬቴ” የሚለው የግሪክ ቃል በምትኩ የሚያመለክተው የላቀ፣ ብቅ ያለ፣ አድናቆትን የሚፈጥር ነገር የሚያመለክት ነው። ስለዚህ ጨዋ ሰው በተዛባ ነገር አይናወጥም፣ ነገር ግን ለራሱ ጥሪ ታማኝ ሆኖ ይኖራል፣ ራሱን ሙሉ በሙሉ ይገነዘባል።

ቅዱሳን ከሰው ልጆች የተለዩ ናቸው ብለን ብናስብ ከዝርያዎቻችን ወሰን በላይ የሚኖሩ ተወዳዳሪ የሌላቸው ለየት ባለ ሥፍራ ተከልለው የሚቀመጡ ዓይነት ናቸው ብለን ብናስብ ከትምህርታችን ውጪ እንሆናለን። ቅዱሳን አሁን ከስነ ምግባራት ጋር በተያያዘ ካስተዋወቅነው አንጻር፣ ይልቁንም ራሳቸው ሙሉ በሙሉ የሆኑ፣ ለእያንዳንዱ ወንድ ወይም ሴት ተገቢውን ጥሪ የሚፈጽሙ ናቸው። ፍትህ፣ መከባበር፣ መረዳዳት፣ አንዱ ለአንዱ መልካም ነገር ማድረግ፣ መተሳሰብ እና ተስፋ የጋራ መደበኛ የሆኑ ነገሮች ተደርገው ቢቆጠሩ እና በምትኩ ያልተለመደ እንግዳ ነገር ባይሆኑ ኖሮ ምንኛ ደስተኛ አለም በሆነ ነበር! ለዚህም ነው በዚህ በዘመናችን ከክፉው የሰው ልጅ ጋር መስማማት በሚኖርብን በአስደናቂ ሁኔታ ውስጥ ስለ በጎ ተግባር የሚናገረው ምዕራፍ በሁሉም ሰው እንደገና ሊገለጥ እና ሊተገበር የሚገባው። በተዛባ ዓለም ውስጥ፣ የተፈጠርንበትን መልክ፣ በላያችን ላይ ለዘላለም ታትሞ የሚገኘውን የእግዚአብሔር መልክ ማስታወስ አለብን።

ግን የበጎስ ስነ-ምግባርን ጽንሰ-ሀሳብ እንዴት መግለፅ እንችላለን? የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ትክክለኛ እና አጭር ፍቺ ይሰጠናል፡- “በጎነት መልካሙን ለማድረግ የተለመደ እና ጽኑ ዝንባሌ ነው” (ቁጥር 1803)። ስለዚህ አልፎ አልፎ ከሰማይ የሚወርደው የተሻሻለ ወይም በተወሰነ የዘፈቀደ መልካም ነገር አይደለም። ታሪክ እንደሚያሳየን ወንጀለኞች እንኳን በቅጽበት ጥሩ ስራዎችን ሲሰሩ ነበር፣ በእርግጥ እነዚህ ተግባራት "በእግዚአብሔር መጽሐፍ" ውስጥ ተጽፈዋል፣ ነገር ግን በጎነት ሌላ ነገር ነው። ከሰውየው ቀስ በቀስ ብስለት ጀምሮ ውስጣዊ ባህሪ እስከመሆን ድረስ የሚመነጭ መልካምነት ነው። በጎነት የነጻነት ልማድ ነው። በማንኛውም ተግባር ነፃ ከሆንን እና በክፉ እና በደጉ መካከል እንድንመርጥ በተፈለገን ቁጥር በጎነት ወደ ትክክለኛው ምርጫ የመምረጥ ዝንባሌ እንዲኖረን የሚያስችለን ነው።

በጎነት እንደዚህ ዓይነት ቆንጆ ስጦታ ከሆነ፣ አንድ ጥያቄ ወዲያውኑ ይነሳል-እንዴት በጎነትን ማግኘት ይቻላል? የዚህ ጥያቄ መልስ ቀላል አይደለም ውስብስብ ነው።

ለክርስቲያን የመጀመሪያ እርዳታ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። በእርግጥም መንፈስ ቅዱስ በተጠመቅን በእኛ በውስጣችን ይሰራል፣ ወደ በጎ ህይወት ለመምራት በነፍሳችን ውስጥ ሁሌም ይሠራል። አንዳንድ ድክመቶቻቸውን ማሸነፍ እንደማይቻል በማሰብ ስንት ክርስቲያኖች በእንባ ወደ ቅድስና ደረጃ የደረሱት! ነገር ግን እግዚአብሔር ለእነርሱ ነድፎ የነበረውን መልካም ሥራ እንዳጠናቀቀ ተለማመዱ። ከሥነ ምግባራዊ ቁርጠኝነት በፊት ጸጋ ይቀድማል።

ከዚህም በላይ በጎነት እንደሚያድግና ሊዳብር እንደሚችል ከሚነግረን ከጥንቶቹ ጥበብ የተገኘውን እጅግ የበለጸገ ትምህርት ፈጽሞ መርሳት የለብንም። እናም ይህ እንዲሆን፣ መንፈስን ለመጠየቅ የመጀመሪያው ስጦታ በትክክል ጥበብ ነው። የሰው ልጅ በእነዚህ ኃይሎች ላይ ምንም ነገር ማድረግ ሳይችል፣ አንዳንድ ጊዜ ምስቅልቅል፣ በውስጥም የሚኖረውን ደስታን፣ ስሜትን፣ ድመነፍስን፣ ፍላጎትን ለማሸነፍ ነፃ ክልል አይደለም። በዋጋ ሊተመን የማይችል ስጦታ ያለን አእምሮ ክፍት ነው፣ ህይወትን በጥሩ ሁኔታ ለመምራት ከስህተቶች የሚማር ጥበብ ነው። ከዚያም በጎ ፈቃድን ይጠይቃል፣ መልካሙን የመምረጥ አቅም፣ እራሳችንን በባሕታዊ ሕይወት ልምድ ማንቀሳቀስ፣  ከግል ፍላጎቶቻችን ከመጠን በላይ መራቅ ይኖርብናል።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ በዚህ ሰላማዊ ፍጥረተ አለም ውስጥ፣ ፈታኝ በሆነው፣ ነገር ግን ለደስታችን ወሳኝ በሆነው በመልካም ምግባሮች ውስጥ ጉዟችንን የምንጀምረው በዚህ መንገድ ነው።

13 March 2024, 13:44

በቅርብ ጊዜ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የተደረገው ግንኙነት

ሁሉንም ያንብቡ >