ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ሆዳምነት እግዚአብሔር የሚሰጠንን ‘የዕለት እንጀራችንን’ ያዛባል ማለታቸው ተገለ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት ከቫቲካን ሆነው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደሚያደርጉ ይታወቃል። በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በጥር 1/2016 ዓ.ም ያደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከእዚህ ቀደም በአዲስ መልክ እኩይ እና ሰናይ ምግባር በሚል ዓብይ አርዕስት ጀምረውት ከነበረው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እና ሆዳምነት በሚል አርዕስት ባደረጉት የክፍል 3 የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሆዳምነት እግዚአብሔር የሚሰጠንን ‘የዕለት እንጀራችንን’ ያዛባል ማለታቸው ተገልጿል!

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በእለቱ ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

እኩይ እና ሰናይ ምግባር በሚል ዓብይ አርዕስት  ጀምረነው የነበረውን የጠቃላላ የትምህርተ ክርስቶስ ዛሬም በመቀጠል፣ ዛሬ ደግሞ ሆዳምነት የሚለውን አርዕስት እንመለከታለን።

ወንጌል ስለዚህ ጉዳይ ምን ይነግረናል? ኢየሱስን እንመልከት። በቃና ሰርግ ላይ ያደረገው የመጀመሪያ ተአምር ለሰው ደስታ ያለውን ርኅራኄ ገልጿል፡ በዓሉ በመልካም እንዲጠናቀቅ አስቦ ለሙሽሪትና ለሙሽራው ብዙ ጥሩ የወይን ጠጅ ይሰጣቸዋል። በአገልግሎቱ ሁሉ፣ ኢየሱስ ከመጥምቁ ዮሐንስ የተለየ ነቢይ ሆኖ ይገለጣል፡- ዮሐንስ በብትውና ሕይወቱ ሲታወስ - በምድረ በዳ ያገኘውን ነገር ሁሉ በልቷል - በምትኩ ኢየሱስ ብዙ ጊዜ በማዕድ የምናየው መሲህ ነው። በእዚህ ባህሪው በእርሱ ላይ የአሉባልታ ወሬ ያስከትላል፣ ምክንያቱም እሱ ለኃጢአተኞች ቸር ብቻ ሳይሆን ከእነሱ ጋር ይበላልና ይጠጣ ነበር ይህ ምልክት ሁሉም ሰው ከተቃወማቸው ሰዎች ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ መሆኑን አሳይቷል።

ነገር ግን ከእዚህ የበለጠ ነገር አለ። ኢየሱስ ለአይሁድ ትእዛዛት ያለው አመለካከት ለህግ ሙሉ በሙሉ መገዛቱን ሲገልጽ፣ ነገር ግን ለደቀ መዛሙርቱ እንደሚራራላቸው ያሳያል፡ በሰንበት ቀን በስንዴ ማሳ በኩል በምያልፉበት ወቅት የስንዴ እሸት ቀጥፈው በሚበሉበት ወቅት “ዳዊት በተራበና የምግብ ፍላጎት በጸናበት ጊዜ አብረውት ከነበሩት ሰዎች ጋር ያደረገውን አላነበባችሁምን? በማለት ከትእዛዛቱ ውስጥ አንዱን ጥሰው እንደነበር (ማር. 2፡23-26) በመጥቀስ ለደቀመዛሙርቱ ጥብቅና ይቆምላቸዋል። ከሁሉ በላይ ግን ኢየሱስ በሚያምር ምሳሌ አዲስ መርሕ አረጋግጧል፡ ሙሽራው ከእነርሱ ጋር በሚሆንበት ጊዜ የሠርጉ እንግዶች መጾም አይችሉም፣ ሙሽራው ከእነርሱ ተለይቶ ሲሄድ ግን ይጾማሉ። አሁን ሁሉም ነገር ከኢየሱስ ጋር አንጻራዊ ነው። እርሱ በመካከላችን ሲሆን እኛ ማዘን አንችልም፣ ነገር ግን በሕማማቱ ሰዓት አዎን፣ እንጾማለን (ማር. 2፡18-20)። ኢየሱስ ከእሱ ጋር ደስተኞች እንድንሆን ይፈልጋል፣ ነገር ግን እርሱ ደግሞ በእርሱ መከራ እንድንካፈል ይፈልጋል እርሱም ደግሞ የታናናሾችና የድሆች መከራ ነው።

ሌላው አስፈላጊ ገጽታ! ኢየሱስ በጥንታዊው ዓለም ለአንዳንድ ባሕሎች የማዕዘን ድንጋይ በሆነው በንጹሕና ንጹህ ባልሆኑ ምግቦች መካከል ያለውን ልዩነት አስቀርቷል። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ኢየሱስ ያስተምራል፣ ሰውን የሚያረክሰው ወደ ሰው የሚገባው ሳይሆን ከልቡ የሚወጣው ነው ይላል። “እንዲሁም ምግብ ሁሉ ንጹሕ መሆኑን ተናገረ” (ማር 7፡19)። ለዚህ ነው ክርስትና ንጹህ ያልሆኑ ምግቦችን የማይመለከተው። ነገር ግን ሊኖረን የሚገባው ትኩረት ውስጣዊ ነው፣ ስለዚህ በራሱ በምግብ ላይ ሳይሆን ከእሱ ጋር ባለን ግንኙነት ላይ ማተኮር ይኖርብናል።

ኢየሱስ ከምግብ ጋር በተያያዘ የመሰረተው ይህ የተረጋጋ ግንኙነት በተለይም ምቹ ናቸው በሚባሉት ማህበረሰቦች ውስጥ ብዙ አለመመጣጠን እና በሽታ አምጪ ተህዋሲያን በሚገለጡበት ጊዜ እንደገና መታየት እና ዋጋ ሊሰጠው ይገባል። አንድ ሰው በጣም ብዙ ወይም በጣም ትንሽ ይበላል። ብዙውን ጊዜ አንድ ሰው ብቻውን ይበላል። የአመጋገብ ችግሮች - የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ጤናማ ያልሆነ ተከታታይ የረሃብ ስሜት፣ ከመጠን በላይ ውፍረት ወዘተ እየተስፋፋ ነው። እናም መድሃኒት እና ስነ ልቦና ከምግብ ጋር ያለንን ደካማ ግንኙነት ለመቋቋም እየሞከሩ ናቸው።

በአብዛኛው ከሥነ-አእምሮ እና ከነፍስ ስቃይ ጋር የተቆራኙ በሽታዎች፣ ብዙ ጊዜ በጣም የሚያሠቃዩ ናቸው። ኢየሱስ እንዳስተማረው የተሳሳተው ምግብ በራሱ ሳይሆን ከምግብ ጋር ያለን ግንኙነት ነው። የምንበላበት መንገድ የውስጠኛው ነገር መገለጫ ነው፡- ለማመጣጠን ወይም ከመጠን በላይ የመጠቀም ዝንባሌ፣ የማመስገን ችሎታ ወይም ራስን በራስ የማስተዳደር እብሪተኝነት፣ ለችግረኞች ምግብ የምያካፍሉ ሰዎች ርኅራኄ ወይም ሁሉንም ነገር ለራሳቸው የሚያከማቹ ራስ ወዳድነት። እንዴት እንደምትበላ ንገረኝ እና ምን አይነት ነፍስ እንዳለህ እነግርሃለሁ።

የጥንት አባቶች የሆዳምነትን እኩይ ባሕሪ ተመልክተው በእንግሊዘኛው ቋንቋ "gastrimargy" የሚል ስም ሰጡት፤ ይህ ቃል "የሆድ ጅልነት" ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። እንደ መብላት ካሉት አስፈላጊ ፍላጎቶቻችን ውስጥ አንዱን የሚይዘው መጥፎ ተግባር ነው።

ከማህበራዊ እይታ አንፃር ከተረጎምነው ሆዳምነት ምናልባትም ፕላኔቷን እየገደለ ያለው በጣም አደገኛው መጥፎ ተግባር ነው። ምክንያቱም ሁሉም ነገር ግምት ውስጥ በማስገባት በስግብግብነት የተሸነፉ ሰዎች ኃጢአት ብዙ ጉዳት አያደርስም በሚል ግምት የፕላኔታችንን ትንሽ ኬክ የሚቀራመቱ ሰዎች የፕላኔቷን ሸቀጦች እየዘረፍ ላለፉት ምዕተ-አመታት የኖረው የስግብግብነት መንፈስ የሁሉንም የወደፊት እጣ ፈንታ ይጎዳል። ሁሉም ነገር በእጃችን ተወስኖ ሳለ የሁሉም ነገር ገዢ እንደሆንን አድርገን ሁሉንም ነገር በእጃችን ያዝን። የሆድ ቁጣ ትልቅ ኃጢአት የሆነው ለዚህ ነው፡ የሰውን ስም ጠልተናል፣ ሌላውን “ሸማቾች” ብለን እንገምታለን። አንድ ሰው ይህን ስም ሊሰጠን ሲጀምር አላስተዋልንም። የተፈጠርነው ወንድ እና ሴት ሆነን እንደ “ቅዱስ ቁርባን” እንድንሆን፣ ማመስገን እንድንችል፣ በምድሪቱ አጠቃቀም ረገድ አስተዋይ እንድንሆን ነው፣ ይልቁንም ወደ አዳኝነት ተለውጠን እና አሁን ይህ “ሆዳምነት” እንዳደረገ እየተገነዘብን ነው። በእኛ እና በምንኖርበት አካባቢ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረስን እንገኛለን። ከግል ሆዳምነታችን እና ከማህበራዊ ሆዳምነታችን ወንጌሉ እንድንፈውስ ያድርግልን።

10 January 2024, 12:31

በቅርብ ጊዜ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የተደረገው ግንኙነት

ሁሉንም ያንብቡ >