ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራችስኮስ ወንጌልን ለማብሰር "በዛሬው መስቀለኛ መንገድ ላይ መገኘት አለብን" ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት ከቫቲካን ሆነው የጠቅላላ የተምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደሚያደርጉ ይታወቃል። ቅዱስነታቸው በኅዳር 19/2016 ዓ.ም ይህንን ሳምንታዊውን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እርሳቸው በአሁኑ ወቅት በደረሰባቸው የሳንባ እብጠት በሽታ ምክንያት አስተምህሮውን ልያቀርቡ አልቻሉም፣ ነገር ግን እርሳቸው ያሰናዱትን አስተምህሮ የእኔታ አባ ፊሊፖ ካምፓኔሊ ቅዱስነታቸው በተገኙበት በምንባብ መልክ ማቅረባቸው ተገልጿል። በወቅቱ ቅዱስነታቸው ያሰናዱት እና በየኔታ አባ ፊሊፖ የቀረበው አስተምህሮ ከእዚህ ቀደም ቅዱስነታቸው በተከታታይ ሲያቀርቡት ከነበረው አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን  ክርስቲያናዊ መልእክት የምንኖርበት እና የምንሰራበት፣ የምንሰቃይበት እና የምንማርበት ነው፣ ቤተክርስቲያን “የመነጋገሪያ እና የመገኛ” ቦታ መሆን አለባት ሲሉ ተናግረዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ከጠቅላላው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በፊት ቅዱስነታቸው በወቅቱ ወደ ጳውሎስ 6ኛ የመሰብሰቢያ አዳርሽ ሲገቡ ሕዝቡ ሞቅ ያለ አቀባበል እና ጭብጨባ እንዳደርጉላቸው የተገለጸ ሲሆን "ሊቀ ጳጳሳችን ረጅም እድሜ ይኑርዎት" በሚሉ ጩኸቶች ቅዱስነታቸውን ተቀብለዋል፣ ይህም በቅርብ ቀናት ውስጥ የእርሳቸውን ስሜት የሚያውቁ ምዕመናን ለቅዱስነታቸው ያላቸውን ፍቅር እንዲመሰክሩ እንደሚያስችላቸው ተገልጿል።  ትናንት ምሽት የቫቲካን ፕሬስ ጽ/ቤት በሐኪሞች ጥያቄ መሰረት ቅዱስነታቸው በ COP28 ለመሳተፍ በሚቀጥለው አርብ ወደ ዱባይ የሚደረገው ሐዋርያዊ ጉዞ እንዲሰረዝ የሕክምና ባለሙያዎች ያቀረቡት ጥሪ ተግባራዊ እንደ ሆነም ይታወሳል። በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ውስጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተቀምጠው ሁሉንም ሰው በመመልከት አሁንም ጥሩ ስሜት ስላልተሰምኝ "በዚህ ጉንፋን እና ድምፁ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባደርግ አያምርም፣ በእኔ ፈንታ የእኔታ አባ ፊሊፖ የእኔን አስተምህሮ በጹሑፍ ወደ እናንተ ያቀርባሉ” ሲሉ ቅዱስነታቸው መናገራቸው ተገልጿል።

የክርስቲያን መልእክት ለዛሬ ጊዜ ነው።

የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከዚህ ቀደም “ለስብከተ ወንጌል ያለው ፍቅር፡- የምእመናን ሐዋርያዊ ቅንዓት” በሚል ዓብይ አርዕስት ሥር ሲያቀርቡት የነበረው አስተምህሮ ቀጣይና የክፍል 28 አስተምህሮ  እንደነበር ታውቋል። በእዚህ መሰረት በላቲን ቋንቋ “Evangelii gaudium” (የወንጌል ደስታ) በሚል አርዕስት ቅዱስነታቸው ከእዚህ ቀደም ይፋ ባደረጉት ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ ላይ ትኩረቱን ያደርገ ነበር።  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በእዚህ ጊዜ ለማስመር የሚፈልጉት ገጽታ የአሁኑ ጊዜ ዋጋ ላይ ነው። የቅዱስ ወንጌል አዋጁ ለዛሬ ነው በማለት ቅዱስነታቸው በአስተምህሮዋቸው የገለጹ ሲሆን ዛሬ ብዙዎች ጦርነትን፣ የአየር ንብረት ለውጥን፣ አለማቀፋዊ ኢፍትሃዊነትን እና ቀጣይነት ያለው ስደትን፣ የወቅቱን "የቤተሰብ እና የተስፋ ቀውስ" ሲመለከቱ ቅሬታ ያሰማሉ ሲሉ ገልጸዋል።

"እነሆ፤ ትክክለኛው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳንም ቀን አሁን ነው!” (2ኛ ቆሮ 6፡2) በየእኔታ አባ ፊሊፖ አማካኝነት በተነበበው የቅዱስነታቸው አስተምህሮ ውስጥ የተገለጸ ሲሆን የዛሬውን ባህል በግለሰብ እና በቴክኖሎጂ ቀዳሚነት ላይ የተመሰረተ ባህል አድርጎ ገልጸው የነፃነት ፅንሰ ሀሳብ ላይ ሁሉንም ገደቦች የማይቀበል እና ለአቅመ ደካሞች ደንታ የለውም ሲሉ የገለጹ ሲሆን ስለዚህም ትልቅ የሰው ልጅ ምኞቶችን ወደ ተለመደው የኢኮኖሚ አመክንዮ ያደርሳል፣ በጤና እና በእርጅና ምክንያት የማያመርቱትን እና የቀን ገቢ ለማግኘት የሚታትሩትን ሰዎች የሚጥላቸው የህይወት ራዕይ አለው። እኛ እራሳችንን የምናገኘው በታሪክ የመጀመሪያው ስልጣኔ ውስጥ ነው ማለት እንችላለን” ሲሉ ቅዱስነታቸው አስተምህሮዋቸውን አስፍረዋል።

ነጠላ አስተሳሰብ እና ስልጣንን ማሳደድ አደገኛ ፈተናዎች ናቸው።

አንድ ወጥነት እና ሁሉን ቻይነት ውዥንብር የባቢሎን ግንብ ታሪክ ያስታውሳል። የሰው ልጅ አንድ ቋንቋ ይናገራል እና ወደ ሰማይ መድረስ ይፈልጋል፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ካርዶቹን አበላሽቶ ልዩነቶቹን እንደገና ያዘጋጃል “ነጠላ አስተሳሰብ” እየተባለ የሚጠራው እና የስልጣን ፍለጋ አደገኛ ፈተናዎች ናቸው ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአስተምህሮዋቸው ውስጥ አስምረውበታል፣ ስለዚህ ጌታ በእሱ ጣልቃ ገብነት አደጋን ይከላከላል ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

ይህ ታሪክ በእውነት ወቅታዊ ይመስላል፡ ዛሬም ቢሆን ከወንድማማችነት እና ከሰላም ይልቅ መተሳሰር ብዙውን ጊዜ በምኞት፣ በብሔርተኝነት፣ በደረጃ ላይ የተመሰረተ፣ በቴክኒካል-ኢኮኖሚያዊ መዋቅር ላይ የተመሰረተ ነው፣ ይህም እግዚአብሔር እዚህ ግባ የማይባል እና የማይጠቅም ነው የሚለውን እምነት የሚያጎለብት ነው፡ ብዙም አይደለም ምክንያቱም የበለጠ እውቀትን እንፈልጋለን ነገር ግን ከሁሉም በላይ ለበለጠ ኃይል እንዘጋጃለን ይህ ደግሞ እምነትን የምያንጽ ነገር አይደለም ብለዋል።

ያለፈውን አንመልከት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በላቲን ቋንቋ “Evangelii gaudium” (የወንጌል ደስታ) በተሰኘው ሐዋርያዊ ማሰሰቢያቸው ውስጥ በሰዎች እና ከአካባቢው ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያንፀባርቅ እና ህይወት ወደ ሚገኝበት “የከተማ ነፍስ ጥልቅ እምብርት” የሚደርስ የወንጌል አዋጅ እንዲታወጅ ጥሪ ማቅረባቸውን በአስተምህሮዋቸው ቅዱስነታቸው የገለጹ ሲሆን ያለፈውን ጊዜ ከመናፈቅ እና ከማንኛውም ግትርነት የጸዳ ስብከተ ወንጌል እንደሚያስፈልግ ቅዱስነታቸው በአባ ፊሊፖ በኩል ባስተላለፉት አስተምህሮ ገልጸዋል።

“ስለዚህ አማራጭ ራዕዮችን ካለፈው እና ከዛሬ ጋር ማነፃፀር አያስፈልግም። ወይም እውነት ቢሆንም፣ ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ረቂቅ የሆኑትን ሃይማኖታዊ እምነቶችን ብቻ መድገሙ ብቻ በቂ አይደለም። እውነት የበለጠ ተዓማኒነት ያለው የሚሆነው አንድ ሰው ሲናገር ድምፁን ስለሚያሰማ ሳይሆን በህይወቱ ስለመሰከረ ነው”።

ዛሬ መስቀለኛ መንገድ ላይ መቆየት አለብን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአባ ፊሊፖ በኩል ባስተላለፉት አስተምህሮ ቤተክርስቲያን ለመገናኘት እና ለአንድነት ማነቃቂያ መሆን አለባት እና በአለም ላይ ያለው እይታ እንግዳ ተቀባይ እንጂ የተለየ ፍርድ መሆን የለበትም” ያሉ ሲሆን በመቀጠል ኢየሱስን ወደ ሌሎች ለማምጣት "በመንገድ ላይ መሄድ፣ አንድ ሰው ወደሚኖርበት ቦታ መሄድ፣ የሚሰቃይበትን፣ የሚሰራበት፣ የሚያጠናበት እና የሚያሰላስልበትን ቦታ መድረስ" አለበት ብለዋል። ንግግርን መፍራት የለብንም ሲሉ በአስተምህሮዋቸው ያሰፈሩት ቅዱስነታቸው  በእርግጥ ንፅፅር እና ትችት ሊረዳን ይችላል ብለዋል።

“ዛሬ መስቀለኛ መንገድ ላይ መቆየት አለብን። እነሱን መተው ማለት ወንጌልን ማደህየት እና ቤተክርስቲያንን ወደ ኑፋቄ መቀነስ ማለት ነው። በእነሱ ላይ መገኘታችን ግን እኛ ክርስቲያኖች የተስፋችንን ምክንያቶች በአዲስ መንገድ እንድንገነዘብ፣ “አዲስና አሮጌውን” ከእምነት ውድ ነገር ነቅለን እንድናካፍል ይረዳናል” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው በየእኔታ አባ ፊሊፖ በኩል ያስተላለፉትን አስተምህሮ አጠናቀዋል።

30 November 2023, 13:38

በቅርብ ጊዜ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የተደረገው ግንኙነት

ሁሉንም ያንብቡ >