ፈልግ

ካርዲናል ዙፒ በዩክሬን ስላለው ስቃይ ለመወያየት ከአሜርካ ፕሬዝዳንት ባይደን ጋር ተገናኙ! ካርዲናል ዙፒ በዩክሬን ስላለው ስቃይ ለመወያየት ከአሜርካ ፕሬዝዳንት ባይደን ጋር ተገናኙ! 

ካርዲናል ዙፒ በዩክሬን ስላለው ስቃይ ለመወያየት ከአሜርካ ፕሬዝዳንት ባይደን ጋር ተገናኙ!

በዩክሬን ሰላምን ለመሻት የጳጳሱ ልዩ መልዕክተኛ ብፁዕ ካርዲናል ማትዮ ዙፒ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር ተገናኝተው ቫቲካን ወደ ሩሲያ የተወሰዱትን የዩክሬን ልጆችን ለመመለስ በምታደርገው ጥረት ላይ ተወያይተዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ልዩ መልዕክተኛ በመሆን ለዩክሬን ባደረጉት የሰላም ተልዕኮ አካል ብፁዕ ካርዲናል ማትዮ ማሪያ ዙፒ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በዋይት ሀውስ ተወያይተዋል።

ስብሰባው የተካሄደው ማክሰኞ ሐምሌ 11/2015 ዓ.ም ሲሆን ለሁለት ሰአት ተኩል ያህል የፈጀ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

ለቅድስት መንበር ሰብአዊ ጥረት አድናቆት

በዋይት ሀውስ የተለቀቀው መግለጫ ፕሬዝደንት ባይደን "ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ቀጣይ አገልግሎት እና ለዓለም አቀፋዊ አመራር ያላቸውን የሰላም ምኞት በመጋራት በቅርቡ የአሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ሆነው መሾማቸውን በደስታ ተቀብለዋል" ብሏል።

ፕሬዚዳንቱ እና ካርዲናል ስለ "ሩሲያ በዩክሬን ቀጣይነት ባለው ጥቃት ምክንያት የተስፋፋውን ስቃይ ለመቅረፍ የቅድስት መንበር ሰብአዊ እርዳታን ለማቅረብ የምታደርገውን ጥረት" በተመለከተም ተናግረዋል።

ልጆችን ወክሎ ጥብቅና መቆም

የዩክሬን መንግስት በሩስያ ውስጥ ትክክለኛው የዩክሬን ልጆች ቁጥር በጣም ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ተናግሯል። የቦሎኛ ሊቀ ጳጳስ እና የኢጣሊያ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ዙፒ ቀደም ሲል ወደ ኪየቭ (እ.አ.አ ከሰኔ 5-6/2023) እና ሞስኮ (እ.አ.አ ከሰኔ 28-30) ባደረጓቸው ተልዕኮዎች ውስጥ ርዕሱን አንስተዋል ።

በሩሲያ ውስጥ የጣሊያን ተወላጅ ካርዲናል ስለ ጉዳዩ ከቭላድሚር ፑቲን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ እና ከሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የህፃናት መብት ኮሚሽነር ማሪያ ሎቮቫ-ቤሎቫ ጋር ተነጋግረዋል ።

የኮሚሽነሩ ድረ-ገጽ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ መወያየቱን አረጋግጧል እናም ስለ "ወታደራዊ ኦፕሬሽን" እና የህጻናት መብት ጥበቃን በተመለከተ ስለ ሰብአዊ ጉዳዮች መነጋገራቸውን የሚገልጽ የካርዲናል ጉብኝት ፎቶ በድረ ገጹ ላይ ይፋ ማደርጉ ይታወቃል።

"በዩክሬን ውስጥ ሰላምን ማሳደግ"

ብፁዕ ካርዲናል ዙፒ ከቫቲካን ዋና ጸሐፊ ከሆኑት ባለሥልጣን ጋር እ.አ.አ. በሐምሌ 17/2023 ወደ ዋሽንግተን ተጉዘዋል፣ ጉብኝታቸውም እሮብ ይጠናቀቃል።

ካርዲናል ከፕሬዝዳንት ባይደን ጋር ከመገናኘታቸው በፊት ከበርካታ የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ጋር በካፒቶል ሂል ተገናኝተዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ዙፒ "በዩክሬን ያለውን ሰላም ለማስፈን" ዋሽንግተንን እንደሚጎበኙ የቅድስት መንበር የፕሬስ ቢሮ ሰኞ ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም ማስታወቁ ይታወሳል።

የካርዲናሉም ተልእኮ እንደ ጋዜጣዊ መግለጫው “ወቅታዊውን አሳዛኝ ሁኔታ በሚመለከት የሃሳቦችን እና አስተያየቶችን መለዋወጥ ለማመቻቸት እንዲሁም በጣም ተጋላጭ የሆኑትን በተለይም የህፃናትን ስቃይ ለመቅረፍ የታለሙ ሰብአዊ እርምጃዎች ድጋፍ ለማድረግ ይፈልጋል” በማለት መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።

ስለ ካርዲናል ዙፒ ተልዕኮ የተሰጠ አስተያየት

ማክሰኞ ሐምሌ 11/2015 ዓ.ም ላይ ለበርካታ የጣሊያን ሚዲያዎች ቅድስት መንበርን በመወከል የዩናይትድ ስቴትስ ሐዋርያዊ እንደራሴ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ዙፒ ተልእኮ “ውይይት መክፈት፡ ማዳመጥና መደመጥ ነው” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ለሰላም የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንደሚያበረክቱ እና በተለይም በሰብአዊ ጉዳዮች ላይ በተለይም ሕፃናትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ለመሳተፍ” ተስፋ እንዳላቸው ተመራጩ ካርዲናል ክሪስቶፍ ፒየር ተናግረዋል።

"ሐሳቡ ውስብስብ በሆነው አውድ ውስጥ ሰላምን ግምት ውስጥ ማስገባት ነው" ብለዋል። "ካርዲናሉ በጣም እውነታዊ ናቸው እና የምንችለውን ለማድረግ እንሞክራለን" ሲሉ አስተያየታቸው ሰጥተዋል።

19 July 2023, 12:39