ፈልግ

ካርዲናል ዙፒ ካርዲናል ዙፒ 

ካርዲናል ዙፒ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የላኩትን ደብዳቤ ለፕሬዚዳንት ባይደን መስጠታቸው ተገለጸ!

የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት ብፁዕ ካርዲናል ዙፒ በዋሽንግተን ዲሲ ባደረጉት የ3 ቀናት ጉብኝት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው፣ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር ያደረጉትን ውይይት፣ እንዲሁም ከሄልሲንኪ ኮሚሽን እና ከበርካታ የኮንግረስ አባላት ጋር ያደረጉትን ውይይት ጨምሮ ዝርዝር ጉዳዮችን ይፋ አድጓል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

እ.ኤ.አ ከሐምሌ 17-19/2023 የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ልዩ መልዕክተኛ ብፁዕ ካርዲናል ማትዮ ዙፒ ዋሽንግተን ዲሲን ጎብኝተው በጦርነት የተጎዳውን የዩክሬን ሕዝብ ስቃይ ለማቃለል እና ወደ ሰላም ጎዳና ለመምጣት ባደረጉት ጥረት የመጨረሻውን ደረጃ አሳይተዋል።

ጉብኝቱ እውን የሆነው ካርዲናሉ በኪየቭ ካደረጉት ጉብኝት በኋላ ሲሆን ብፁዕ ካርዲናል ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ተገናኝተው ከእዚያም በመቀጠል በሞስኮ ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ኪሪል እና ከሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ካደርጉት ግንኙነት በኋላ እውን የሆነ ጉብኝት ነው።

የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት በትላንትናው እለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው ብፁዕ ካርዲናል ዙፒ ከቫቲካን ዋና ጸሐፊ ጋር በመሆን በአሜሪካ ካፒቶል ሂል ጉብኝት ባደርጉበት ወቅት "በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማስቀጠል እና ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ባይደን ጋር ለመገናኘት" በማቀድ ነበር ወደ እዚያው ያቀኑት።

ዲፕሎማሲያዊ ጥረት

እ.ኤ.አ. ሐምሌ 17 ምሽት ላይ በአሜርካ በሚገኘው የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ እንደራሴ ጽሕፈት ቤት ሲደርሱ ካርዲናል ዙፒ ከዩኤስ ካቶሊካዊ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሊቀ ጳጳስ ቲሞቲ ብሮሊዮ ጋር ተወያይተዋል። በዚያ ስብሰባ ላይ ቀሳውስቱ በዩክሬን ስላለው ጦርነት እና የቅድስት መንበር ተጎጂዎችን እና ሰላምን ለማስፈን ባደረገው እንቅስቃሴ ላይ ሀሳባቸውን ተለዋውጠዋል።

በማግስቱ ጠዋት፣ የቫቲካን ልኡካን፣ በአሜሪካ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ጽሕፈት ቤት እንደራሴ እጩ ካርዲናል ክሪስቶፍ ፒየር እና የእኔታ ፓትሪክ ሆርጋን፣ የዩናይትድ ስቴትስ የመጀመርያው የቅድስት መንበር የሐዋርያዊ እንደራሴ ምክር ቤት አባል፣ ከዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የደኅንነት እና ትብብር ኮሚሽን (ሄልሲንኪ ኮሚሽን) (“ሄልሲንኪ ስምምነት ወይም የሄልሲንኪ ሰነድ” በመባል የሚታወቀው ሰነድ እ.አ.አ በነሐሴ 30 እና በሐምሌ 1/1975 መካከል በሄልሲንኪ፣ ፊንላንድ ውስጥ በአውሮፓ የደህንነት እና ትብብር ኮንፈረንስ (CSCE) የመዝጊያ ስብሰባ ላይ የተፈረመ ሰነድ ነው። ሰነዱ በአራት ዋና ዋና ክፍሎች የተከፈለ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ሉዓላዊ እኩልነት፣ በሉዓላዊነት ውስጥ ያሉ መብቶችን ማክበር፣ ከአደጋው ወይም ኃይል መጠቀም መቆጠብ፣ የድንበሮች የማይጣሱ የግዛቶች ግዛታዊ አንድነት ማክበር፣ አለመግባባቶችን በሰላም መፍታት፣ በውስጣዊ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ አለመግባት፣ የአስተሳሰብ፣ የህሊና፣ የሃይማኖት ወይም የእምነት ነፃነትን ጨምሮ የሰብአዊ መብቶች እና መሰረታዊ ነጻነቶችን ማክበር፣ የህዝቦች እኩል መብት እና ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ማክበር፣ በክልሎች እና በአገራት መካከል ትብብር እንዲፈጠር ማድረግ፣ በአለም አቀፍ ህግ ውስጥ ያሉ ግዴታዎችን በቅን ልቦና መፈፀም የሚለው የመጀመሪያው የሰነዱ አካል ነው) ከአውሮፓ አባላት ጋር ተገናኝተዋል።

በዚያ ስብሰባ ላይ ብፁዕ ካርዲናል በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት አደራ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ምንነትና እድገቶች በሥዕላዊ መግለጫዎች የገለጹ ሲሆን ተሰብሳቢዎቹም የበለጠ ውጤታማ መሆን በሚቻልበት መንገድ ላይ ተወያይተዋል።

በዚሁ ቀን ከሰአት በኋላ፣ የጳጳሱ ልኡካን እና ሌሎች የልዑካን ቡድን አባላትን ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ባይደን በዋይት ሀውስ ተቀበሉ። ብፁዕ ካርዲናሉ በጦርነቱ ምክንያት ለደረሰው ስቃይ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ማዘናቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለፕሬዝዳንት ባይደን የላኩትን ደብዳቤ አስረክበዋል።

በዋሽንግተን ዲ ሲ የሰዓት አቆጣጠር “ከሰዓት ቡኋላ 5 ሰአት ላይ የጀመረው እና ከአንድ ሰአት በላይ የፈጀው ስብሰባው በታላቅ መተሳሰብ እና መደማመጥ በተሞላበት ድባብ ተካሂዷል” ያለው መግለጫው “በስብሰባው ወቅት በተለይ ለህፃናት እና በጣም ደካማ ለሆኑት ሰብአዊ እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናችንን በማረጋገጥ ለዚህ አጣዳፊ ምላሽ ለመስጠት እና የሰላም መንገዶችን ለመፍጠር በማቀድ” ሰፋ ያለ ውይይት አድርጓል።  

መግለጫው ሲያበቃ እ.ኤ.አ ሀምሌ 19 ማለዳ የቫቲካን ልኡካን በኮንግረስ ቁርስ ላይ ተገኝተው ነበር ፣በዚህም ወቅት ብፁዕ ካርዲናል ዙፒ “በሰላማዊ ተልእኮው የተለያዩ ደረጃዎች ባደረጓቸው ስብሰባዎች ላይ አጭር ሐሳባቸውን” የመግለጽ እድል አግኝተዋል።

በዚያ ወቅት፣ “የቅድስት መንበር ጥረት አድናቆቱን ገልጿል፤ እያንዳንዱ ግለሰብ ለሰላም የመሥራት ኃላፊነት አለበት” ብሏል።

የሐዋርያዊው እንደራሴ በጥንቃቄ የተሞላ ብሩህ ተስፋ

ከቫቲካን ዜና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በዋሽንግተን የሚገኙት የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ እንደራሴ ብፁዕ ካርዲናል ዙፒ በሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ በተለይም “ከዩክሬን ወደ ሩሲያ የተጓጓዙ ሕፃናትን” በሚመለከት ተስፋቸውን ገልጸዋል ሲሉ ተናግሯል።

በሊቀ ጳጳሱ ልዑካን ስብሰባ ላይ የተገኙት እጩ ካርዲናል ክሪስቶፍ ፒዬር “ፕሬዝዳንቱ ብዙ ያዳምጡ ነበር፣ እናም በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተነሳሽነት ያላቸውን እርካታ ገልጸዋል፣ እናም በዚህ ጉዳይ ላይ የፕሬዚዳንቱን አመለካከት እና የቅዱስ አባታችንን አመለካከት በተመለከተ ረጅም ጊዜ ወስደን ሐሳብ ተለዋውጠናል። ሁሉንም ችግሮች ወዲያውኑ የመፍታት አቅም ባይኖረንም ብፁዕ ካርዲናል የራሳቸውን አዎንታዊ አስተዋጾ ማድረግ እና የተለያዩ ሐሳቦችን ማመንጨት እንደምንፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል። ውስብስብነታቸውን እናውቃቸዋለን” ሲሉ ካርዲናል ፒየር ተናግረዋል።

ጳጳሱ አክለውም ለጊዜው ተጨባጭ ውጤቶች ባይኖሩም በተቸገሩት ሰዎች ምትክ ሁሉንም ጥረት ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል ። "እኔ እንደማስበው እዚህ በሁሉም ቦታ፣ ካርዲናል ዛሬ ባደረጓቸው የተለያዩ ግንኙነቶች፣ ሰዎች ለዚያ ልኬት በጣም ስሜታዊ እንደሆኑ እና ለመርዳት ዝግጁ መሆናቸውን አሳይተዋል ብሏል።

የቅድስት መንበር ሚና

በዲፕሎማሲያዊ ደረጃ እጩ ካርዲናል ክሪስቶፍ ፒየር እንደ ተናገሩት ከሆነ፣ ቤተክርስቲያን በዓለም ሕይወት ውስጥ የምታበረክተው አስተዋጽኦ ወሳኝ ነው፣ “ቅድስት መንበር የዓለም አካል ናት፣ እናም ጦርነቱ የሚያስከትላቸው ውጤቶች ለሰዎች አስከፊ ናቸው። ስለስደተኞቹ፣ ስለሞቱት ሰዎች፣ ስለደረሰባቸው ጉዳት በተለይም ስለ ህጻናት ጉዳይ መናገራችንን አናቆምም” ብሏል።

እናም እንደ ዲፕሎማት “ደረጃ በደረጃ መስራት አለብን። በሚቻልበት ጊዜ የመጀመሪያውን እርምጃ እንወስዳለን ፣ እና ከእነዚህ እርምጃዎች ውስጥ አንዱ ካርዲናል እያደረጉ ያሉት ነገር ነው ፣ ሁሉንም ነገር መፍታት እችላለሁ ብለው ሳይናገሩ ፣ እና ለወደፊቱ ብዙ ተስፋ እያዩ የበኩላቸውን አስተዋጾ እያደርጉ ይገኛሉ ሲሉ ተናግሯል።

 

20 July 2023, 10:46