ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት   (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዩክሬን ውስጥ ጦርነት እንዲቆም ልዩ ጸሎት አቅረቡ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ በመካሄድ ላይ ለሚገኙ ጦርነቶች በተለይም በዩክሬን እየተከሰተ የሚገኘው ጦርነት ማስቆም ባለመችላችን ይቅር እንዲለን አምላክን የመማጸኛ ልዩ ጸሎት ማቅረባቸው ተገለጸ።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ረቡዕ መጋቢት 7/2014 ዓ.ም ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባጠናቀቁበት ወቅት እንደ ገለጹት በዩክሬን ያለውን ጦርነት እንዲቆም ልዩ ጸሎት አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሰው ልጅ ጭካኔ የተነሳ በዓለም ዙሪያ እየተከሰቱ የሚገኙት ጦርነቶች ሁሉ ይቅር እንዲለን እግዚአብሔርን የተማጸኑ ሲሆን እርሱም ምድርን ለመንከባከብ እና ለመጠበቅ የተፈጠሩት  እጆቻችን ወደ ሞት መሣሪያነት በመቀየራቸው የተነሳ እግዚአብሔር ይቅር ይለን ዘንድ ጸሎት ማደረጋቸው ተገልጿል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጸሎቱን ከማቅረባቸው በፊት ክርስቲያኖች በዩክሬን ጦርነት የተነሳ በተከሰቱት ሥቃዮች ውስጥ "እግዚአብሔርን ይቅርታ እንዲጠይቁ እና ሰላምን እንዲማጸኑ" ጋብዘው ነበር።

የጳጳሱ ኦፊሴላዊ ያልሆነ ጸሎት ትርጉም ከዚህ በታች እንደ ሚከተለው ቀርቧል።

አቤቱ ጦርነትን ስላካሄድን ይቅር በለን!

የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እኛን ኃጢአተኞችን ማረን!

በኪየቭ ላይ በተጣሉ ቦምቦች ጥላ ውስጥ የተወለድከው ጌታ ኢየሱስ ሆይ ማረን!

በካርኪቭ በድንጋይ ውስጥ በእናት እቅፍ ውስጥ የሞተከው ጌታ ኢየሱስ ሆይ ማረን!

ወደ ጦር ግንባር የተላከው የ20 አመት ወጣት ጌታ ኢየሱስ ሆይ ማረን!

አሁንም የታጠቁ እጆችን በመስቀልህ ጥላ የምታይ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ማረን!

አቤቱ ይቅር በለን ።

በጦር መሳሪያ በተጨፈጨፉ ሰዎች ደም ጥማችንን ሳይረካ በጉዳዩ ላይ የምናደርገውን ጉዞ እየቀጠልን በመሆኑ የተነሳ እጆችህን የሰቀልንበት ችንካር ይቅር በለን።

እነዚህ ሊታደጓቸው የፈጠርሃቸው እጆች ወደ ሞት መሣሪያነት ስለተቀየሩ ይቅር በለን።

አቤቱ ወንድማችንን ስለገደለን ይቅር በለን!

አቤልን ለመግደል ከመረት ላይ ድንጋይ እንዳነሳው ቃየል ስለሆንን ይቅር በለን።

ጭካኔያችንን በተግባራችን ስላሳየን ራሳችንን ስላመጻደቅን፣ ተግባራችንን በአረመኔነታችን እና በህመማችን ሕጋዊ ስላደረግን ይቅር በለን።

አቤቱ ጦርነትን ስላካሄድን ይቅር በለን፣

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ እንለምንሃለን!

የቃየንን እጅ አጥብቀህ ያዝልን!

ህሊናችንን አብራል፣

ፈቃዳችን አይፈጸም!

የእኛ ፍላጎት እንዳይፈጸም አድርግልን!

አቤቱ አቤቱ አስቁመን!

የቃየንንም እጅ መልሰህ ስታጥፍ እርሱንም ቢሆን መንከባከብህን አታቁም። እርሱም ወንድማችን ነውና።

አቤቱ ግፍን ሁሉ አስቁም!

አቤቱ እንማጽንሃለን!

አሜን።

16 March 2022, 11:45

በቅርብ ጊዜ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የተደረገው ግንኙነት

ሁሉንም ያንብቡ >