የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
ቅዱስነታቸው የቀዶ ጥገና ሕክምና አገልግሎት ከተደረገላቸው በኋላ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ፣ የሚቀርብላቸውን ቀለል ያሉ ምግቦችን መውሰድ መጀመራቸውን እና የምርመራ ውጤቶችም መልካም መሆናቸውን አቶ ማቴዎ ብሩኒ አስታውቀዋል።
ቅዱስነታቸው ትናንት ሌሊት እና ዛሬ ጥሩ ዕረፍት አድርገው መዋላቸውን እና ጥቂት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ መጀመራቸውን የቫቲካን ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍሉ ዳይሬክተር አቶ ማቴዎ ብሩኒ አስታውቀዋል።