ፈልግ

የኢራቅ ክርስቲያኖች የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስን ሐዋርያዊ ጉብኝት በጉጉት እየተጠባበቁ ነወ የኢራቅ ክርስቲያኖች የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስን ሐዋርያዊ ጉብኝት በጉጉት እየተጠባበቁ ነወ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በኢራቅ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የተሳካ የሆን ዘንድ ጸሎት እንዲደረግላቸው ጠየቁ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከየካቲት 26-29/2013 ዓ.ም በኢራቅ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደ ሚያደርጉ ከቫቲካን ዜና የተገኘው መረጃ የሚያስረዳ ሲሆን ይህ እርሳቸው የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ቅድመ ዝግጅት ለመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በሙሉ ፍሬ እንዲያፈራ ምእመናን ጉዞውን በጸሎት እንዲያጅቡት መጠየቃቸው ተገልጿል። የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮ በየካቲት 24/2013 ዓ.ም ረቡዕ ጠዋት በቫቲካን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካደረጉ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት ወደ ኢራቅ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማደረግ በሚሄዱበት ወቅት ምዕመኑ ከእርሳቸው ጋር በጸሎት አብሮ እንዲጓዝ ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጿል።

“እግዚአብሄር ከፈቀደ ከነገ ወዲያ ለሶስት ቀናት ያህል ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ኢራቅ እሄዳለሁ። ለረዥም ጊዜ ያህል እነዚያን በጣም የተሠቃዩ ሰዎችን ለመገናኘት ፈልጌ ነበር፣ ያንን በሰማዕታት ደም የተገነባውን በአብርሃም ምድር የምትገኘውን ቤተክርስቲያን ለመጎብኘት ከፍተኛ ፍላጎት ነበረኝ” ሲሉ ሳምንታዊውን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካጠናቀቁ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

በአገሪቱ ካሉ ሌሎች የሃይማኖት መሪዎች ጋር በመሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ሌላ ምዕራፍ በእምነት ወንድሞች በሆኑ ሰዎች መካከል” እንደሚፈጠር ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

“የተሻለ ሐዋርያዊ መንገድ እንዲከፈት እና የተስፋ ፍሬዎችን እንዲያፈራ ይህን ሐዋርያዊ ጉዞ በጸሎታችሁ እንድታጅቡት እጠይቃለሁ” ብለዋል። የኢራቅ ህዝብ እየጠበቀን ነው ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ወደ ኢራቅ “ለመሄድ ያልተፈቀደላቸው” የቀድሞ ርዕሰ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ኢራቅን ለመጎብኘት ከፍተኛ ጉጉት የነበራቸው እንደ ነበር ያስታወሱ ሲሆን ይህ ጉብኝተ እርሳቸው አሁን በሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት እውን እንደ ሚሆን ያላቸውን ተስፋ አክለው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.አ.አ በ2000 ዓ.ም ታላቁ ኢዮቤልዩ አመት ከመጀመሩ በርካታ ወራት በፊት ኢራቅን ለመጎብኘት ያላቸውን ፍላጎት በወቅቱ መግለጻቸው ይታወሳል።

“የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ ወደ የከለዳውያን አገር ወደ ሆነቺው ኡር መሄድን እፈልጋለሁ ፣ በደቡብ ኢራቅ ወደምትገኘው በአሁኑ ወቅት ሙካያር በመባል ወደ ምትታወቀው በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ መሠረት ደግሞ አብርሃም የጌታን ቃል የሰማበት ከተማ ለመጎብኘት እሄዳለሁ” በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተናግረዋል።

ምንም እንኳን በኢራቅ የሚገኙ በርካታ ከተሞች በመጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሰው የሚገኙ ቢሆንም እስካሁን ድረስ አንድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ አገሪቷን እንዳልጎበኙ የሚታወቅ ሲሆን እናም የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ካላቸው ሁሉም ሀገሮች መካከል ኢራቅ በሊቀ ጳጳስ ያልተጎበኘች ቅዱስ የሆነች ምድር ብቸኛ ሀገር ሆና ቆይታለች።

03 March 2021, 20:49