ፈልግ

 ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ አያቶች እና አረጋውያን የሚታሰቡበት ዓለም አቀፍ ቀን ይፋ አደረጉ! ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ አያቶች እና አረጋውያን የሚታሰቡበት ዓለም አቀፍ ቀን ይፋ አደረጉ! 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ አያቶች እና አረጋውያን የሚታሰቡበት ዓለም አቀፍ ቀን ይፋ አደረጉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በምትገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለአያቶች እና ለአረጋውያን መታሳቢያ ይሆን ዘንድ ዓለም አቀፍ ቀን እንዲከበር መወሰናቸውን በጥር 23/2013 ዓ.ም አስታወቁ። ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን ይፋ ያደረጉት በእለቱ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ እና የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን ጸሎት ከደገሙ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት እንደ ነበረም ተገልጿል። ከዚህ ዓመት ጀምሮ የኢየሱስ አያቶች የሆኑት የቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና መታሰቢያ በዓል በሐምሌ ወር አራተኛ ሳምንት ላይ እንደ ሚከበር ቅዱስነታቸው አያይዘው ገልጸዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን 

እሁድ ጥር 23/2013 ዓ.ም የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን የብስራተ ገብሬል ጸሎት ከደገሙ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለአያቶች እና ለአረጋውያን መታሰቢያ የሚሆን የዓለም አቀፍ ቀን በቤተክርስቲያን ደረጃ እንዲከበር የወሰኑ ሲሆን ይህም እለት በየአመቱ በሐምሌ ወር በአራተኛው ሳምንት እሁድ እለት የሚከበረውን የኢየሱስ አያቶች የሆኑት የቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና በዓል ጋር መሳ ለመሳ እንደ ሚከበር ቅዲስነታቸው አስታውቀዋል።

መጪውን ኢየሱስ በሕጻንነቱ ወደ ቤተ መቅደስ የተወደበት እለት የሚከበረውን በዓል በማስታወስ - አረጋውያኑ ስምዖንና እና ነቢይት የነበረችው ሃና ሕፃኑን ኢየሱስን ሲያገኙት መሲሕ መሆኑን እንደ ተገነዘቡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የገለጹ ሲሆን “መንፈስ ቅዱስ ዛሬም ቢሆን በአረጋውያን ላይ የጥበብ ሀሳቦችን እና የጥበብ ቃላትን ያነሳሳል” ብለዋል። የአረጋውያን ድምፅ “ውድ ነው” ሲሉ የተናገሩት ቅዱስነታቸው “የእግዚአብሔርን ውዳሴ ስለሚዘምርና የሕዝቦችን ሥር መሰረት ስለሚጠብቁ ነው” ብሏል።

አረጋውያኑ አሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሐሳባቸውን ለማጽናት በማሰብ  “እርጅና ስጦታ መሆኑን እና አያቶች የሕይወትን ተሞክሮ ለወጣቶች ለማስተላለፍ በተለያዩ ትውልዶች መካከል ትስስር መፍጠር እንደ ሚችሉ” ቅዱስነታቸው አውስተዋል።

አዛውንቶች መዘንጋት የለባቸውም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መልእክታቸው ሲቀጥሉ የአያቶችን እና የአረጋውያንን ቀን እንዲመሰረት መደረጉን ያወሱ ሲሆን ምክንያቱም “አያቶች ብዙውን ጊዜ ይዘነጋሉ፣ እናም አረጋውያን የተቀበሉትን ይህን ስር መሰረቶቻችንን በመጠበቅ እና በማስተላለፍ ይህን ሀብት እንዳንረሳ ለማደረግ ታቅዶ የሚከበር ቀን ነው” ብለዋል ፡፡

አያቶች እና የልጅ ልጆች እርስ በእርስ መገናኘታቸው አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ሰጥተዋል ፣ ምክንያቱም “ነቢዩ ኢዩኤል እንደሚለው ፣ አያቶች የልጅ ልጆቻቸውን ሲያዩ ወጣቶች ደግሞ ከአያቶቻቸው ጥንካሬን በማግኘት ወደፊት በመሄድ ትንቢት ይናገራሉ” በማለት ስለሚመክረን ነው ብለዋል።

የአሞሪስ ላቲቲያ (የፍቅር ሐሴት) የቤተሰብ ዓመት የመጀመሪያ ፍሬዎች

የምዕመናን፣ የቤተሰብን እና የሕይወት ጉዳይ በበላይነት የሚመለከተው እና የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ብጽዕ ካርዲናል ኬቪን ፋሬል ይህንን በዓለም አቀፍ ደረጃ በምትገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚከበረው  የመጀመርያው የአያቶች እና የአረጋዊያንን ቀን ተከትሎ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአያቶች እና የአረጋውያን ቀን መመስረት “የአሞሪስ ላቲቲያ (የፍቅር ሐሴት ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ) የቤተሰብ አመት የመጀመሪያ ፍሬ ነው ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን አያቶች እና አረጋዊያን ለመላው ቤተክርስቲያን ስጦታ መሆናቸው እንዲቀጥል ታስቦ የሚከበር ቀን ነው ብለዋል።

አክለውም “ከእንግዲህ በማንኛውም የክርስቲያን ማህበረሰብ ውስጥ ለአረጋውያን የሚደርገው ሐዋርያዊ እንክብካቤ ችላ የማይባል እና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው ፡፡ ‘ሁላችንም ወንድማማቾች ነን’ በሚለው ጳጳሳዊ መልእክት ውስጥ ቅዱስ አባታችን ማንም ብቻውን እንደማይድን ያስታውሰናል ፡፡ ይህን በአእምሯችን ይዘን ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፈውን መንፈሳዊና ሰብዓዊ ሀብት ከፍ አድርገን ልንመለከተው ይገባል ” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወቅቱ የዓለም የጤና እክሎችን ከግምት ባስገባ መልኩ በመጭው ሐምሌ 18/2013 ዓ.ም እሁድ ምሽት ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ ይህንን የመጀመሪያውን የአረጋዊያን እና የአያቶች ዓለም አቀፍ ቀን ምክንያት በማደረግ መስዋዕተ ቅዳሴ በማሳረግ እራሳቸው ራሳቸው በመምራት የመጀመሪያውን የዓለም አቀፍ ቀን ያከብራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የምዕመናን፣ የቤተሰብን እና የሕይወት ጉዳይን የሚመለክቱ ነገሮችን በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ብጽዕ ካርዲናል ኬቪን ፋሬል አክለው ገለጸዋል።

ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቅድሚያ የሚሰጧቸው ጉዳዮች

የምዕመናን፣ የቤተሰብን እና የሕይወት ጉዳይን የሚመለክቱ ነገሮችን በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጳጳሳዊ ምክር ቤት ውስጥ የሚሰሩት አቶ ቪቶሪኦ ሼልዞ ለአረጋውያን በሚደረገው ሐዋርያዊ እንክብካቤ ውስጥ ተሳታፊ ናቸው። የአያቶች እና የአረጋውያን የዓለም ቀን መከበር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለእግዚአብሄር ቃል እና ለድሆች ከተመሠረቱት አለም አቀፍ ቀናት ጋር የተቆራኘ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ቪቶሪኦ ሼልዞ ከቫቲካን ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ድሆች ፣ መጽሐፍ ቅዱስ እና አዛውንቶች” የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት  ፍራንቸስኮስ በጵጵስና ዘመናቸው ውስጥ “ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች” እንደሆኑና “የቤተክርስቲያኗን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለማለም” ተብለው የተቀመጡ ጉዳዮች መሆናቸውን አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

በአረጋውያን እና በወጣት ትውልድ መካከል ያለውን ልዩነት መቀነስ አስፈላጊ ነው ያሉት አቶ ቪቶሪኦ ሼልዞ “አዛውንቶች በራሳቸው አያድኑም። እንደ አለመታደል ሆኖ በወረርሽኙ ወቅት ስንት አዛውንቶች እንደ ተጎዱ ተመልክተናል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተመሳሳይ ሁኔታ “ወጣቶች ፣ ጎልማሶች እና ህብረተሰባችን ያለ አዛውንቶች እራሳቸውን ማዳን እንደማይችሉ” ሊያስታውሱን ይፈልጋሉ በማለት ተናግረዋል። በተለያዩ ደረጃዎች ውስጥ በሚገኙ ትውልዶች መካከል ውይይት ማደረግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው “ከቀውስ ውስጥ  በተሻለ እና ጥሩ በሆነ መልኩ እና ሁኔታ ለመውጣት እያንዳንዱ ህብረተሰብ ከሥር መሰረቱ ጋር መግባባት እና ከአረጋውያን ጋር ከመወያየት ጀምሮ አዳዲስ እሴቶችን ማቀናጀት ይኖርበታል” ብለዋል።

የአረጋውያን ሕልሞች

አቶ ቪቶሪኦ ሼልዞ ንግግራቸውን ሲቀጥሉ “የማግለል ባሕል ተቃራኒው ለአዛውንቶች በትክክል ሐዋርያዊ እንክብካቤ ማደረግ ነው - አዛውንቶችን በየቀኑ በአካባቢያችን የሕይወት ማእከል ውስጥ ማስቀመጥ ይኖርብናል። በድንገተኛ ሁኔታዎች ብቻ ውስጥ ሳይሆን ይህንን ለመገንዘብ ሳንዘገይ ለአረጋዊያን በተቻለን አቅም እንክብካቤ ማደረግ ይኖርብናል” ብለዋል።

አረጋውያኑ “ሁልጊዜ ፍሬ የሚሰጡ ዛፎች እና ሕልማቸውን የሚቀጥሉ ሰዎች” ናቸው በማለት የተናገሩት አቶ ቪቶሪኦ ሼልዞ ስለዚህ ወጣቶች “ከአረጋውያን ህልም ጋር ወደ ውይይት መምጣት” አለባቸው ብለዋል። ይህ ብዙውን ጊዜ በርዕሰ ሊቀ ጳጳስ ፍራንቸስኮስ የሚደጋገም መልእክት መሆኑን ጨምረው ያስታውሱት አቶ ቪቶሪኦ ሼልዞ የአረጋውያን ህልሞች ህብረተሰባችንን ገንብተዋል፣ ለምሳሌ እኔ አውሮፓን እያሰብኩ ያለሁት ከእንግዲህ ጦርነት የሌለበት ዓለም አድርጌ ነው፣ ‘ሁላችንም ወንድማማቾች ነን’ የተሰኘው ጳጳሳዊ መልእክት “ጦርነት የሌለበት ዓለም በዚህ ህልም” የተሞላ ነው፣ “አረጋዊያን እና አያቶቻችን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ” ያዩት ህልም ነው በማለት አክለው ገልጸዋል።

አቶ ቪቶሪኦ ሼልዞ አክለው እንደ ገለጹት “ምናልባት ለኅብረተሰባችን የወደፊት ህልሞች ምን መሆን እንደሚገባቸው ለመረዳት“ ከእነዚህ ህልሞች ጋር ወደ ውይይት መግባት አለብን ” በማለት ከቫቲካን ኒውስ ጋር የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀዋል።

31 January 2021, 15:36