ፈልግ

በቤተሰብ ውስጥ ስለምገኘው ፍቅር ለመመሥከር ታስቦ የሚከበር ልዩ ዓመት ታወጀ! በቤተሰብ ውስጥ ስለምገኘው ፍቅር ለመመሥከር ታስቦ የሚከበር ልዩ ዓመት ታወጀ! 

በቤተሰብ ውስጥ ስለሚገኘው ፍቅር ለመመሥከር ታስቦ የሚከበር ልዩ ዓመት ታወጀ!

በዘመናችን በስፋት እየታቱ የሚገኙ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ ቤተሰብ ወደ ፊት እንዲራመድ ለማገዝ መንፈሳዊ፣ ሐዋርያዊ እና ባህላዊ ተነሳሽነት እንዲኖር ለማድረግ ይችላ ዘንድ የምዕመናንን፣ የቤተሰብን እና ሕይወትን የሚመለከቱ ነገሮችን በበላይነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት በቤተሰብ ውስጥ ስለሚገኘው ፍቅር ለመመሥከር ይችላ ዘንድ “የቤተሰብ ልዩ ዓመት” እንዲከበር ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሐሳብ ማቅረቡ ይታወሳል። ይህ የቤተሰብ ልዩ አመት በላቲን ቋንቋ “Amoris laetitia” (የፍቅር ሐሴት) በሚል አርእስት የተጻፈው ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ በቤተሰብ ውስጥ ስላለው ፍቅር በሰፊው የሚተነን ለጳጳሳት፣ ለካህናትና ለዲያቆናት፣ ለመነኮሳት፣ ለክርስቲያን ባለ ትዳሮች እና ለምዕመናን ሁሉ እ.አ.አ በመጋቢት 19/2016 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ያስተላለፉት የድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ  ይፋ የሆነበት አምስተኛ አመት በመጪው እ.አ.አ መጋቢት 19/2021 ዓ.ም ላይ የሚዘከር ሲሆን ከእዚያ እለት አንስቶ እስከ እ.አ.አ ሰኔ 26/2022 ዓ.ም ድረስ “ልዩ የቤተሰብ ቀን” እንዲከበር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 18/2013 ዓ.ም በይፋ ማወጃቸው ተገልጿል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻን ተከታታዮች ይህንን ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ ሙሉ ይዘቱን በአጭሩ እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድተከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ፍቅር በቤተሰብ ውስጥ በሚል ርእስ ለጳጳሳት፣ ለካህናትና ለዲያቆናት፣ ለመነኮሳት፣ ለክርስቲያን ባለ ትዳሮች እና ለምእመናን በሙሉ ያስተላለፉት የድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ አጠቃላይ ይዘት።

 

የፍቅር ሐሴት

ፍቅር በቤተሰብ ውስጥ

አሞሪስ ላኤቲሲአ (Amoris Laetitia)

በመጋቢት 30/2008 ዓ.ም ለንባብ የበቃው እና በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የተፃፈ  ሐዋሪያዊ ማሳሰቢያ

የአሞሪስ ላኤቲሲአ ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ አወቃቀር እና ትርጉም በአጭሩ

በቫቲካን ዜና የተዘጋጀ

ፍቅር በቤተሰብ ውስጥ

“የፍቅር ሐሴት” ወይም በላቲን “አሞሪስ ላኤቲሲአ” የተሰኘው እና ትኩረቱን ፍቅር በቤተሰብ ውስጥ ስላለው ሚና ላይ በማድረግ የምያወሳው ድሕረ ሲኖዶስ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን እ.አ.አ በመጋቢት 19/2016 ዓ.ም በቅዱስ ዮሴፍ አመታዊ የንግሥ በዓል ዕለት በቅዱስ አባታችን ተፈርሞ ለንባብ እንዲበቃ መታዘዙ በአጋጣሚ የተፈጠር ጉዳይ አልነበረም።

ይህ ሐዋሪያዊ ቃለ ማሳሰቢያ ከእዚህ ቀደም በቅዱስ አባታችን አነሳሽነት፣ በቤተስብ ጉዳይ ላይ ትኩረትን በማድረግ እ.አ.አ በ2014 ዓ.ም በተዘጋጀው ልዩ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ሲኖዶስ እና በመቀጠልም እ.አ.አ በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም ከመቶ ዘጠና በላይ የሚሆኑ ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ  ጳጳሳት የተሳተፉበት መደበኛው የጳጳሳት ሲኖዶስ ድምር ውጤት ነው።

አሞሪስ ላኤቲሲአ (የፍቅር ሐሴት) የተሰኘው ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ ቀደም ብለው ከተካሄዱት ሁለት ሲኖዶሶች ባሻገር ከእዚህ በፊት የነበሩት የቤተክርስቲያን ሰነዶችን፣ ከቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮስ በፊት የነበሩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አስተምሮዎች እንዲሁም በቤተሰብ ዙሪያ እርሳቸው እራሳቸው የሰጡትን አስተምሮ አጠቃሎ የያዘ ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ ነው።

እንደ ተጨማሪ ግብሃት በዓለም ዙሪያ ለምሳሌም በኬንያ፣ በአውስትራሊያ፣ በአርጄንቲና . . . ወዘተ ከተካሄዱትን ጳጳሳዊ ጉባሄዎች የማጠናከሪያ ሐሳብ የወሰደ ሲሆን በተጨማሪም የጥቁሮች መብት ተሟጋች የነበረው እና “I have adream” (ሕልም አለኝ) በሚለው አባባሉ የሚታወቀው አሜሪካዊው የሰብሃዊ መብት ተሟጋች የነበረው ማርቲን ሉተር ኪንግ እና  የማሕበርሰብ ስነ-ልቦና አጥኝ የነበረው ጀርመናዊው ኤንሪክ ፍሮም ጉልህ ሊባል በሚችል መልኩ የተጠቀሱበት እና “ባቤትስ ፊስት” (Babette’s Feast) የተሰኘው እና እ.አ.አ በ1987 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በዴንማርክ ለእይታ የቀረበ ድራማ ላይ በተጠቀሰው እና ትኩረቱን በ19ኛ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ በዴንማርክ ፓስተር ከነበረው አባታቸው ጋር ጭምት የሆነ ሕይወት ይኖሩ ስለ ነበሩ ሁለት እህተማማቾች የሚተርከው ዋና ጽንሰ ሐሳብም በሐውርያዊው ማሳሰቢያ ውስጥ ተጠቅሱዏል።

መግቢያ (ከአንቀጽ 1-7)

ከምዕራፍ አንድ እስከ ሰባት በሐዋሪያዊው ማሳሰቢያ ውስጥ የተጠቀሰው በመቀጠል በዝርዝር ለሚቀርቡት ሐሳቦች እንደ መንደርደሪያ የሚሆኑ ሐሳቦችን የያዘ ነው። ይህ 325 አንቀጾች ያሉት ሐዋሪያዊ ማሳሰቢያ በዘጠኝ ምዕራፎች የተከፈለ ነው። የመጀምሪያዎቹ ሰባት የመግቢያ አንቀጾች የሐዋርያዊውን ማሳሰቢያ አርዕስት ውስብስብነት በግልጽ በማስቀመጥ በቀጣይነትም አስቸኳይ እና ጥልቅ የሆነ ጥናት እንዲደርግበት የምያሳስብ ነው።

በተጨማሪም ቀደም ብለው በተካሄዱት ሁለት ሲኖዶሶች ላይ ቅዱሳን አባቶች መልክ እንዲይዝ ያሳሰቡት የነፍሳት ዕንቁ “multifaceted gem” (አ.ላ. ቁ. 4)  የተሰኘው እና ወድ የሆኑ የሰው ልጅች የማንነት እሴቶች ተጠብቀው እንዲቀጥሉ የሚጋብዝ ሐሳቦችም ተጠቅሰውበታል። ነገር ግን ቅዱስነታቸው ጥንቃቄ በተሞላው እና ውዝግብ በማይፈጥር መልኩ “ቀኖናዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ፣ የስነ- ምግባር ጉድለቶች ወይም ሐዋሪያዊ ተግዳሮቶች፣ ቤተ ክርስቲያን በተሰጣት ስልጣን በምትሰጠው ኦፊሴልያዊ  አስተምሮ ወይም (magisterium) ብቻ መፈታት የለባቸውም” የሚል ሐሳብ አንጸባርቀዋል።

 በእርግጥም “ለአንዳንድ ለሚነሱ አንገብጋቢ ጥያቄዎች እያንዳንዱ አገር ወይም ክልል. . . ወዘተ፣ ባህሉን እና ወጉን በጠበቀ መልኩ እና የማሕበረሰቡን ጥቅም ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ አንገብጋቢ ለሆኑ ችግሮቻቸው መፍትሄን መስጠት ይችላሉ። ‘ባህሎች አንዱ ከአንዱ የተለዩ በመሆናቸው አጠቃላይ ወይም ዓለማቀፋዊ የሆኑ መርሆች እንዲከበሩ እና ተጋብራዊ እንዲደረጉ ከተፈለገ  እንደየባህሉ ሁኔታ መወሰድ ይኖርባቸኋል’” (አ.ላ. ቁ. 4)። “እነዚህ ዓለማቀፋዊ የሆኑ መርሆችን ‘በባህል ውስጥ ማስረጸ’ የሚለው መርህ ሐሳብ የሚተገበረው የችግሮችን መንስሄ በማጥናት፣ እንዲሁም ምፍትሄን በመንደፍ፣ በተጨማሪም  የቤተክርስቲያን ቀኖናን እና ቤተ ክርስቲያን በተሰጣት መንፈሳዊ ስልጣን የምታስተምራቸውን አስተምሮዎችን ተመርኩዞ ለአንገብጋቢ ችግሮች ተገቢ በሆነ መልኩ ምልስ ሊሰጥ ይገባል። ነገር ግን በእዚህ ዓይነቱ ዘዴ የተፈታ ማንኛውም ዓይነት አንገብጋቢ ችግር ይዘቱ ‘ዓለማቀፋዊ’ ሊሆን አይችልም”።

እ.አ.አ በ2015 ዓ.ም በተካሄደው ሲኖድ ላይ ቅዱስነታቸው በግልጽ እንዳስቀመጡት “ለአንድ ጳጳስ ጤናማ ጉዳይ ሆኖ የሚታየው ጉዳይ፣ በሌላ አህጉር ወይም ሀገር ለሚኖር ጳጳስ ግን እንደ እንግዳ እና አሳፋሪ ነገር ተደርጎ ሊቆጠር ይችል። በአንዱ ጳጳስ ማሕበርሰብ ውስጥ እንደ የሰው ልጆች የመብት ጥሰት ተደርጎ የሚቆጠር ተግባር  በሌላ አሀጉር ወይም ሀገር ውስጥ ለሚኖር ጳጳስ ግን እንደ ግልጽ እና የማይጣሱ ትክክለኛ የሰው ልጆች መብትን የምያስከብር ደንብ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።  በአንዱ ማሕበረሰብ ውስጥ እንደ ሕሊና ነፃነት የሚቆጠሩ ተግባሮች በሌላው ማሕበርሰብ ውስጥ ግን እንደ ግራ መጋባት ይቆጠራሉ” ማለታቸው ይታውሳል።

ቅዱስነታቸው በእዚሁ ሐዋርያዊ ማሳሰቢያቸው “በመገናኛ ብዙኃን የሚደርጉ ክርክሮች፣ አንዳንድ አሳታሚዎች አልፎ ተርፎም በቤተክርስቲያን አገልጋዮች መካከል ጉዳዩን በጥልቀት ሳይመረምሩ እና አንድ አቋም ላይ ሳይደርሱ ተመጣጣኝ ያልሆነ አጠቃላይ ለውጥ እንዲመጣ መፈለጋቸው እና  ሁሉንም ዓይነት ጉዳዮች አጠቃላይ ደንቦችን ተግባራዊ በማድረግ ለመፍታት ዝንባሌ ማሳየታቸው እንዲሁም መለኮታዊ የሆኑ አስተምሮዎችን ከግምት በማስገባት ወደ አልተፈለገ ድምዳሜ ማምራት” (አ.ላ. ቁ. 2) ቅዱስነታቸው በግልጽ እንዳስቀመጡት የለውጥ ጥያቄዎችን እና ውስብስብ የሆኑ ሕግጋትን አጠቃላይ ተግባራት ጎን ለጎን አስቀምጠን በግልጽ ከመፈርጅ መቆጠብ  እንደ ሚገባ ገልጸኋል።

28 December 2020, 13:17