ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የክርስቲያን ምስክሮች በፍቅር ክፉን ወደ መልካምነት ይለውጣሉ አሉ!

የጎርጎስሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ-ክርክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት የገና በዓል በታኅሳስ 16/2013 ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ከተከበረበት የገና በዓል በመቀጠል ባለው እለት የቤተክርስቲያን የመጀመርያው ሰማዕት ተብሎ የሚጠራው የቅዱስ እስጢፋኖስ ዓመታዊ በዓል እንደ ሚከበር ይታወቃል። የእዚህ  የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ሰማዕት በመባል የሚታወቀው የቅዱስ እስጢፋኖስ ዓመታዊ በዓል በታኅሳስ 17/2013 ዓ.ም. በተከበረበት ወቅት በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን ባደረጉት አስተንትኖ የክርስቲያን ምስክሮች በፍቅር ክፉን ወደ መልካምነት ይለውጣሉ ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 17/2013 ዓ.ም በቫቲካን የቅዱስ እስጢፋኖስን ዓመታዊ በዓል አስመልክተው ያሰሙትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞች እና እህቶች እንደምን አረፈዳችሁ!

ትናንት (ታኅሳስ 16/2013 ዓ.ም) የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል ኢየሱስን ወደ ዓለም የመጣ “እውነተኛው ብርሃን” እንደ ሆነ በመጠቀስ ይህ ብርሃን “በጨለማ የሚያበራ፣ ጨለማውም ያላሸነፈው” (ዮሐንስ 1፡9፣5) ብርሃን እንደ ሆነ ይናገር ነበር። የኢየሱስ ምስክር የነበረው ቅዱስ እስጢፋኖስ በጨለማ ውስጥ ሲያበራ ዛሬ እናያለን። እሱ በሐሰት ተከሷል እና በጭካኔ በድንጋይ ተወግሯል፣ ነገር ግን በጥላቻ ጨለማ ውስጥ የኢየሱስን ብርሃን ያበራል-ስለ ገዳዮቹ ይጸልያል እናም ይቅር ይላቸዋል። እሱ ብርሃንን ወደ ጨለማ ውስጥ ማምጣት ከቀጠሉ ወንድሞችና እህቶች ቡድን ውስጥ የመጀመርያው ሰማዕት ሲሆን ይህ ማለት ደግሞ ምስክርነት የሰጠ፣ ለክፉ ነገር መልካም ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ፣ ለዓመፅ እና ሐሰት ለሆኑ ነገሮች እጅ የማይሰጡ፣ ነገር ግን ጠመዝማዛ የሆኑ የጥላቻ አካሄዶችን የዋህ በሆነ ፍቅር የሚሰባብሩ ሰዎች ማለት ነው። እነዚህ ምስክሮች በዓለም ሌሊቶች ውስጥ የእግዚአብሔርን ንጋት ያበራሉ።

ነገር ግን እንዴት ነው ምስክር መሆን የሚቻለው? ኢየሱስን በመምሰል ነው። ኢየሱስን መምሰል የሁሉም ክርስቲያን መንገድ ሊሆን ይገባል። “የሰው ልጅ ሊያገለግልና ሕይወቱን ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ሊሰጥ መጣ እንጂ ሊገለገል አልመጣምና” (ማርቆስ 10፡45) የሚለውን እውን በማደረግ  ቅዱስ እስጢፋኖስ አብነት ሆኖናል፣ እናም እርሱ ድይቆን ነበር፣ ዲያቆን ማለት ደግሞ አገልጋይ ማለት ነው፣ ማእድ በማቅረብ ድሆችን ያገለግል ነበር (የሐዋ ሥራ 6፡2)። እሱ በየቀኑ ጌታን ለመምሰል ይሞክራል፣ እናም በመጨረሻው ጊዜም ይህንን ሐሳቡን እውን ያደረገዋል፣ ልክ በኢየሱስ ላይ እንዳደረጉ እና እርሱን በያዝበት መልኩ ተያዘ፣  ተፈርዶበት ከከተማ ውጪ ተወግሮ ሞተ፣ እንደ ኢየሱስ በመጸለይ ይቅር ይላቸዋል።  በድንጋይ በሚወገርበት ጊዜ “ጌታ ሆይ ይህንን ኃጢአት አትቁጠርባቸው” (የሐዋ ስራ 7፡60) በማለት ጸልዩአል።

ሆኖም አንድ ጥያቄ ሊነሳ ይችላል-በዓለም ላይ ክፋት በተንሰራፋበት በእዚህ ጊዜ እነዚህ የጥሩነት ምስክሮች በእውነት ያስፈልጋሉ? መጸለይ እና ይቅር ማለት ምን ጥቅም አለው? የምናከናውነው መልካም ምሳሌ ለመሆን ብቻ ነው? የለም ብዙ ተጨማሪ ነገር አለ። አንድ ለየት ያለ ነገር እናገኛለን። እስጢፋኖስ ከጸለየላቸውና ይቅር ካላቸው ሰዎች መካከል መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ሚለው “ሳውል የተባለ አንድ ጎልማሳ” ነበረ (የሐዋ. ሥራ 7፡58) “ሳውልም በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ነበር” (የሐዋ ሥራ 8፡1) እንደ ተጠቀሰው። ብዙም ሳይቆይ በእግዚአብሔር ቸርነት ሳውል ተለውጦ በታሪክ ውስጥ ትልቁ ሚስዮናዊ በመሆን ጳውሎስ የሚል ሥም አገኘ። ጳውሎስ የተወለደው ከእግዚአብሄር ጸጋ ነው ፣ ነገር ግን በእስጢፋኖስ ይቅርታ በኩል ነበር። ይህም የእርሱ መንፈሳዊ ለውጥ ያመጥበት ዘር ሆነ። የፍቅር ምልክቶች ታሪክን እንደሚለውጡ ማረጋገጫ ነው -ትናንሽ ፣ የተደበቁ ፣ የዕለት ተዕለትም ተግባራትን ጭምር። ምክንያቱም እግዚአብሔር በሚጸልዩ፣ በሚወዱ እና ይቅር በሚሉ ትሁታን ብርታት አማካይነት ታሪክን ይመራል።

ይህ ለእኛም ይሠራል። በተለመደው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ሕይወትን የሚቀይር ያልተለመደ ሥራ እንድናደርግ ጌታ ይፈልጋል። በምንኖርበት፣ በቤተሰብ ፣ በስራ ቦታ ፣ በየትኛውም ቦታ ቢሆን ፣ የፈገግታ ብርሃን በመስጠት እና የጩኸት እና የሐሜት ጥላዎችን በመሸሽ ብቻ እንኳን የኢየሱስ ምስክሮች እንድንሆን ተጠርተናል። እናም ከዚያ አንድ የተሳሳተ ነገር ስናይ ከመተቸት ፣ ከማማት እና ማጉረምረም ይልቅ ስህተት ለሠሩ ሰዎች እና ለዚያ አስቸጋሪ ሁኔታ እንጸልይ። እናም በቤት ውስጥ ውይይት ሲነሳ ለማሸነፍ ከመሞከር ይልቅ ለማብረድ እንሞክር። እናም በእያንዳንዱ ጊዜ በአዲስ መልክ መጀመር እና ቅር ያሰኙንን ሰዎች ይቅር ማለት ይገባል። ቅዱስ እስጢፋኖስ የጥላቻ ድንጋዮች እየተቀበለ በነበረበት ወቅት በይቅርታ ቃል ምላሽ ሰጠ። በእዚህ መልኩ ታሪክን ቀየረ። እኛም እንደ አንድ ጥሩ የግጥም መጽሐፍ በሚሰጠን ምሳሌ መሰረት “ እንደ አንድ ጥሩ የዘንባባ ዛፍ ስትሆን እነሱ በአንተ ላይ ድንጋይ ይወረውራሉ እና እነሱም ቀኖችህ እንዲበላሹ ያደርጋሉ” የሚል ውብ ምሳሌ ተጠቅመን እኛም ክፋትን በየቀኑ ወደ መልካም መለወጥ እንችላለን።

ዛሬ በኢየሱስ ስም ምክንያት በስደት ለሚሰቃዩት ሰዎች እኛ እንፀልያለን፣ የብዙዎች ሁኔታ እጅግ በጣም ያሳዝናል። እነዚህን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን በየዋህነት ለጭቆና ምላሽ ለሚሰጡ እና እንደ ኢየሱስ እውነተኛ ምስክሮች ክፉን በመልካም ለማሸነፍ ይችሉ ዘንድ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል በአደራ እንሰጣለን።

 

26 December 2020, 13:21

የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >