ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የገና በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የተወለደበትና የፍቅር በዓል ነው አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በቫቲካን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በታኅሳስ 14/2013 ዓ.ም ባደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ “ዮሴፍም ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ፣ በገሊላ አውራጃ ከምትገኘው ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ የዳዊት ከተማ ወደሆነችው፣ ቤተ ልሔም ወደምትባል ከተማ ወደ ይሁዳ ወጣ። ወደዚያም ለመመዝገብ የተጓዘው፣ የመውለጃ ጊዜዋ ከተቃረበው ከእጮኛው ከማርያም ጋር ነበር። በዚያም እንዳሉ የምትወልድበት ጊዜ ደረሰ፤ የበኵር ልጇ የሆነውን ወንድ ልጅ ወለደች፤ በጨርቅም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማረፊያ ቦታ ስላላገኙ በግርግም አስተኛችው” (ሉቃስ 2፡4-7) በሚለው የኢየሱስን መወለድ በሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን “የገና በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የተወለደበት ሥጋ የለበሰበት የፍቅር በዓል ነው” ማለታቸው ተገልጿል።

ይህንን ዝግጅት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እንደምን አረፈዳችሁ!

ወደ ገና በዓል (የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የማሕበርሰብ ክፍሎች ዘንድ በመጪው አርብ ታኅሳስ 16/2013 ዓ.ም የሚከበረውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ለማለት ነው) እየተቃረብን በምንገኝበት በአሁኑ ወቅት ዛሬ የምናደርገው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የገና በዓል ለማክበር ዝግጅት ለማድረግ የሚረዳ ለአስተሳሰባችን ቀለብ የሚሆን ትምህርት ለማቅረብ እፈለጋለሁ። በእዚህ በገና በዓል ዋዜማ በእኩለ ሌሊት በሚደረገው የመስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት መልአኩ ለእረኞች ባወጀው አዋጅ ላይ “አትፍሩ፤ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች አምጥቼላችኋለሁና። ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀን ተወልዶላችኋልና፤ እርሱም ጌታ ክርስቶስ ነው” (ሉቃ 2: 10-12) በማለት ይነግራቸዋል።

ከእረኞቹ በመኮረጅ እኛም ደግሞ መንፈሳዊ ስፍራ ወደ ሆነው ወደ ቤተልሔም በመሄድ “በእንግዶችም ማረፊያ ቦታ ስላላገኙ በግርግም አስተኛችው” (ሉቃስ 2፡7)  ማርያም በረት ውስጥ ልጇን ወደ ወለደችበት ቦታ እስቲ እንሂድ። የገና በዓል ዓለም አቀፋዊ የሆነ በዓል ነው፣ እናም የማያምኑ ሰዎች እንኳን ሳይቀር ይህንን በዓል ያከብራሉ። ክርስቲያኖች ግን የገና በዓል ወሳኝ ክስተት ፣ እግዚአብሔር በዓለም ላይ ያቃጠለው ዘላለማዊ እሳት መሆኑን እና ከእውነተኛ ነገሮች ጋር ግራ በተጋባ መልኩ መገንዘብ እንደሌለበት ያውቃል። ስሜታዊ ወይም ሽመታ ብቻ ወደ ምናከናውንበት ዓይነት በዓል መቀነስ የለበትም የገና በዓል። ባለፈው ሳምንት እሁድ እለት የገናን በዓል አጋጣሚ ተጠቅመን ነገሮችን መሸመት ወደ ሚለው ቃል እንዳይታጠፍ በመግለጽ ለዚህ ችግር ትኩረት ሰጥቼ ተናግሬ ነበር። የለም-የገና በዓል በስጦታ እና በመልካም ምኞቶች የተሞላ ብቻ ሳይሆን በክርስቲያኖች እምነት ድክመት የተነሳ እና በሰው ልጅም ሰብዓዊ ድህነት የተነሳ ብቻ ወደ ስሜታዊነት ወይም ወደ ሽመታ ግብዣ መታጠፍ የለበትም። ስለሆነም የእምነታችንን አንፀባራቂ እምብርት ለመረዳት የማይችል አንድን ዓለማዊ አስተሳሰብ መግታት አስፈላጊ ነው ፣  አስፈላጊው እምነት “ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም አደረ፤ እኛም ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ ከአባቱ ዘንድ የመጣውን የአንድያ ልጁን ክብር አየን”(ዮሐ 1፡14) የሚለው ነው፣ እናም ይህ የገና ፍሬ ነው፣ ይልቁኑ እሱ የገና እውነት ነው ፣ ከእዚህ የተለየ ሌላ እውነት የለም።

የገና በዓል በአንድ በኩል በታሪክ ድራማ ላይ እንድናሰላስል ይጋብዘናል ፣ ይህም ወንዶች እና ሴቶች በኃጢአት የቆሰሉ ፣ ያለማቋረጥ እውነትን በመፈለግ ፣ ምህረትን እና ቤዛ ፍለጋ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ሲኖሩ በሌላ በኩል የሚያድነውን እውነት ሊነግረን እና በወዳጅነቱ እና በሕይወቱ ውስጥ ተካፋዮች እንድንሆን ወደ እኛ በመጣው የእግዚአብሔር ቸርነት ላይ ያጠነጥናል። እናም ይህ የሕይወት ስጦታ-ይህ ንፁህ ጸጋ ነው፣ በራሳችን ተግባር ያገኘነው ጥቅም አይደለም። አንድ ቅዱስ አባት ነበሩ፣ እንዲህም ይሉ ነበር “ነገር ግን እዛ ጋር፣ እዚህ ጋር ተመልከት በራሳችሁ ብቃት ብቻ ፈልጉ ከፀጋ በቀር ምንም አታገኙም” በማለት ይናገሩ ነበር። ሁሉም ነገር ፀጋ እና የጸጋ ስጦታ ነው። እናም ይህ የጸጋ ስጦታ እኛ በገና በዓል ትህትና እና ሰብአዊነት እንቀበላለን ፣ እናም በአሁኑ ጊዜ በበሽታው ሳቢያ እንኳን የተስፋፋውን ተስፋቢስነት ከልባችን እና ከልቦናችን ሊያስወግድ ይችላል። ያንን የመረበሽ እና ግራ መጋባት ስሜት ማሸነፍ እንችላለን፣ እራሳችን በድከመቶች እና ውድቀቶች እንድንወረር ባለመፍቀድ ፣ ረዳት የሌለው እና ትኩረት ያልተሰጠው ትሁት እና ምስኪን የሆነው ሕጻን ራሱ እግዚአብሔር ነው። እርሱ ሰው እንዲሆን እንደ ፈለገ እንደገና ባገኘነው ግንዛቤ ውስጥ እንድንኖር ያስፈልጋል። ሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ ቤተክርስቲያን በዘመናዊው ዓለም ውስጥ በሚል አርዕስት በቀረበው ዝነኛ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው አንቀፅ ላይ ይህ ክስተት እያንዳንዳችንን እንደሚመለከት ይናገራል፣ እንዲህም ይላል “የእግዚአብሔር ልጅ ሰው በመሆኑ በአንዳንድ ነገር ከእያንዳንዱ ሰው ጋር ተካፋይ ሆኗል። እርሱ በሰብዓዊ እጆቹ ሰራ። በሰብዓዊ አእምሮ አስቦ በሰብዓዊ ፈቃድ ሰራ፣ በሰብዓዊ ልብም ወደደ። እርሱ ከድንግል ማርያም በመወለዱ እንደኛ ሰው ሆነ፣ ከኃጢያት በስተቀር በሁሉም ነገር እኛን መሰለ” (2ኛው የቫቲካን ጉባሄ ሰነድ በላቲን ቋንቋ  ‘Gaudium et Spes’ ‘በእዚህ ዘመን ስለምትገኘው ቤተክርስቲያን’ ቁ. 22)። ነገር ግን ኢየሱስ የተወለደው ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ነው ፣ ይህ ከእኔ ጋር ምን አገናኘው? እሱንም ፣ እኔንም ፣ እያንዳንዳችንን ይነካል። ኢየሱስ ከእኛ አንዱ ነው እግዚአብሔር በኢየሱስ ውስጥ ከእኛ አንዱ ሆኗል።

ይህ እውነታ ብዙ ደስታን እና ድፍረትን ይሰጠናል። እግዚአብሔር እኛን ከሩቅ አልተመለከተንም ፣ አላለፈንም ፣ በችግራችን ወቅት አልተጣልንም ፣ በአካል እንዲያው ለይስሙላ ብቻ ሥጋ አልለበሰም፣ ይልቁንም የእኛን ተፈጥሮ እና ሰብአዊ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ስቧል። ከኃጢአት በቀር በሁሉም ነገር እንደ እኛ ሰው ሆነ። የሰው ልጅ ሁሉ በእርሱ ውስጥ ነው። እኛ እንደሆንን ሁሉ የሆነውን ነገር ሁሉ እርሱ ወስዷል። የክርስትናን እምነት ለመረዳት ይህ አስፈላጊ ነው። ቅዱስ አውጎስጢኖስ መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣቱን በተመለከተ የቅዱስ አጎስጢኖስ ኑዛዜ በሚል አርእስ ባቀረበው አስተንትኖ ውስጥ በእምነት ቃላቱ ላይ እንዲህ ሲል ጽፏል “ጌታዬን ኢየሱስ ክርስቶስ አልያዝኩትም ነበር፣ ትሁት ለሆነው እርሱ ራሴን ትሁት አድርጌ አቀረብኩ፣ የእሱ አቅመ ደካም የሆነ አካሉ እንዴት እንደ ሚመራኝ ገና አላወኩም ነበር ” በማለት ተናግሮ ነበር። የኢየሱስ “አቅመ ደካማነት” ምንድነው? የኢየሱስ “አቅመ ደካማነት” “ትምህርት” ነው! ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ፍቅር ይገልጥልናል። የገና በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የተወለደበት እና ሥጋ የለበሰበት የፍቅር በዓል ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በጨለማ ውስጥ የሚበራ የሰው ልጅ ብርሃን ነው ፣ ለሰው ልጅ ሕልውና እና ለጠቅላላው ታሪክ ትርጉም ይሰጣል።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶች ይህ አጭር አስተንትኖ የገናን በዓል በከፍተኛ ግንዛቤ እንድናከብር ይረዳናል። ነገር ግን ለመዘጋጀት ሌላ መንገድ አለ ፣ እኔን እና እናንተን ላስታውስ የምፈልገው ነገር  እርሱ በሁሉም ሰው የሚደርስበት ነገር ነው፣ እርሱ የተወለደበትን ሁኔታ በሚገልጸው የገና ዛፍ ሥር ሁነን ማሰላሰል ይኖርብናል። በቅዱስ ወንጌል ውስጥ ያዳመጥነው የክርስቶስ ልደት ማሳያ ታሪክ ውስጥ ተጨባጭ በሆነ ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል። ስለዚህ ባለፈው ዓመት በጻፍኩት ሐዋርያዊ መልእክት እንደገና በድጋሚ ማንሳት ለእኛ ጠቃሚ ነው። እሱም “አስደናቂ ምልክት” “ማራኪ ምስል” የሚል ነው። በአዚዚው የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ትምህርት ቤት ውስጥ የትውልድ ስፍራውን ለማሰላሰል ቆም ብለን እግዚአብሄር ወደ ዓለም መምጣት የፈለገበት “አስደናቂ” መንገድ አስገራሚነት በእኛ ውስጥ እንደገና እንዲወለድ በማድረግ ትንሽ ልጅ መሰል መሆን እንችላለን። እስቲ አስደናቂ የሆነውን ፀጋን እንጠይቅ -ከዚህ ምስጢር በፊት ፣ በእውነት በጣም ርህራሄ ያለው ፣ የሚያምር ፣ ከልባችን ጋር የተቀራረበ ፣ ጌታ የመገናኘት ጸጋን ይሰጠናል ፣ እሱን ለመገናኘት ፣ ወደ እርሱ ለመቅረብ ፣ ለመሳብ ለሁላችን ቅርብ እንዲሆን ለማደረግ ብርታቱን ይሰጠናል። ይህ በእኛ ውስጥ የርህራሄን መንፈስ ያድሳል። ባለፈው ቀን ከአንዳንድ የሳይንስ ሊቃውንት ጋር እየተነጋገርኩ በነበርኩበት ወቅት ስለ ሰው ሰራሽ አብሮኸተ (አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ) እና ስለ ሮቦቶች ተነጋገርን ነበር… ለሁሉም እና ለሁሉም ነገር የተቀየሱ ሮቦቶች አሉ። ይህ ደግሞ እያደገ በመሄድ ላይ የሚሄድ ቴክኖሎጂ ነው። እኔም “ግን ሮቦቶች በጭራሽ ማድረግ የማይችሉት ነገር ምንድነው?” ብዬ ጠየኳቸው። እነሱ በእዚህ ጉዳይ ላይ አስበውበት ነበር ፣ ሀሳቦችን አቀረቡ ፣ ነገር ግን በመጨረሻ ሁሉም ስለ አንድ ነገር ተስማምተዋል-ርህራሄን ማሳየት እንደ ማይችል። ሮቦቶች መቼም ቢሆን ርህራሄ የማድረግ አቅም አይኖራቸውም። እናም ዛሬ እግዚአብሔር የሚያመጣልን ነገር ይህ ነው፣ እግዚአብሔር ወደ ዓለም ለመምጣት የፈለገበት አስደናቂ እና ዋናው ነገር ደግሞ ለእግዚአብሔር ቅርብ የሆነው የሰው ልጅ ርህራሄ በውስጣችን ያድሳል። እና ዛሬ እኛ በጣም ርህራሄ ያስፈልገናል ፣ በእርሱ መንካት በጣም ያስፈልገናል ፣ በጣም ብዙ ሰቆቃ እያየን እንገኛለንና! ወረርሽኙ የበለጠ እንድንርቅ ያስገደደን ከሆነ ፣ ኢየሱስ የተኛበትን ግርግም እንመልከት፣ እርስ በርሳችን የምንቀራረብ ፣ ሰው የመሆንን ርህራሄ የሚያሳየንን መንገድ በእዚያ ውስጥ እናያለና። ይህንን መንገድ እንከተል። መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ!

23 December 2020, 15:08

በቅርብ ጊዜ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የተደረገው ግንኙነት

ሁሉንም ያንብቡ >