ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እና የደቡብ ሱዳን  ባለ ስልጣናት በሚያዚያ 03/2011 ዓ. ም. በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እና የደቡብ ሱዳን ባለ ስልጣናት በሚያዚያ 03/2011 ዓ. ም. በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ሰላም፣ ብርሀን፣ እና ተስፋ ደቡብ ሱዳን ውስጥ እውን ሊሆኑ ይችላሉ”

የደቡብ ሱዳን የሐይማኖት አባቶች እና ከፍተኛ የመንግሥት ባለ ስልጣናት በጋራ ከሚያዚያ 2-3/2011 ዓ. ም. ድረስ በቫቲካን የሁለት ቀን ሱባሄ ማድረጋቸው ያታወሳል። በእዚህ ሱባሄ ማብቂያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ያደረጉትን ንግግር በድጋሚ እንደ ሚከተለው እናቀርባለን።

የመግቢያ ሰላምታ

1. እዚህ ለተገኛችሁ የደቡብ ሱዳን ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት እና በሪፖብሊኳ የተከሰተውን አወዛጋቢ ግጭት ለመፍታት ታስቦ እ.አ.አ. በግንቦት 12/2019 ዓ.ም ላይ ይህንን አወዛጋቢ ግጭት ለመፍታት ታስቦ በሚፈረመው ስምምነት መሰረት የአገሪቷ ምክትል ፕሬዚዳንት ለሆኑት እንዲሁም፡ ለእያንዳንዳችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ሞቅ ያለ ሰላምታዬን አቀርብላችኋለሁ።  በእራሳቸው ማህበረሰብ ውስጥ የሚገኙትን እና በአደራ ተሰጥቶዋቸው የነበሩትን መንጋዎች በመንፈሳዊነት በመንከባከብ ላይ ለነበሩ በደቡባዊ ሱዳን ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ አባያተ ክርስቲያናት የምክር ቤት አባላት፣ ወንድማዊ ሰላምታዬን አቀርባለሁ። በዚህ በቫቲካን ውስጥ በተዘጋጀው ሱባሄ ላይ እንድትካፈሉ ያቀረብኩትን ጥሪ በመልካም መንፈስ እና በተከፈተ ልብ በመቀበላችሁ የተነሳ ልባዊ ምስጋናዬን ለሁላችሁም አቀርባለሁ። በተመሳሳይ መልኩም የዚህ ሱባሄ የመነሻ ሐሳብ ያቀረቡትን የካንትርበሪ ሀገረ ስብከት የአንግሊካን ሊቀ ጳጳሳት ብጹዕ አቡነ ጃስቲን ዌልቢይ እኔ እንዲሁም የቀድሞ የስኮትላንድ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ ጉባኤ አስተባባሪ የነበሩት የተከበሩ ጆን ቻርለስ ለየት ባለ መልኩ ሰላምታዬን ለማቅረብ እወዳለሁ። እናንተን የተቀላቀልኩት ይህንን የሁለት ቀን የጸጋ ጊዜ እንድንቋደስ የፈቀደውን እግዚኣብሔርን ከልብ በማመስገን እና በማወደስ ሲሆን ከእናንተ ጋር እንድገናኝ ስለቻልኩኝ ከልብ የመነጨ ምስጋና እና ውዳሴ እና ለእግዚአብሔር በማቅረብ ከእርሱ ጋር በተቀደሰ ኅዳሴ ውስጥ እነዚህን ሁለት የጸጋ ቀናት እንድካፈል ስላስቻለኝ አመሰግነዋለሁ።

ሰላም ጌታ ለእኛ የሰጠን የመጀመሪያው አስፈላጊ ስጦታ ነው

“ሰላም ለእናንተ ይሁን!” (ዮሐ. 20፡19)። ከሞት የተነሳው ጌታ ፍርተው እና አዝነው በላይኛው ክፍል ውስጥ ተቀምጠው ለነበሩት የእርሱ ደቀ-መዛሙርት በተገለጠላቸው ጊዜ ባቀረበላቸው አበረታች እና አጽናኝ ቃላትን ተጠቅሜ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ። "ሰላም" የሚለው እና ጌታ በቅድሚያ የተጠቀመበት ቃል እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር መሆኑን እንገነዘባለን። ከእርሱ አሳዛኝ ስቃይ እና በሞት ላይ ድል ተቀዳጅቶ ከተነሳ በኋላ ለሐዋርያቱ የተሰጠ የመጀሪያው ስጦታ ሰላም ነው። ከታላቅ የስቃይ ሁኔታ ውስጥ ለመጣችሁ፣ ለእናንተ እና ለሕዝቦቻችሁ በግጭቶቹ ምክንያት እጅግ በጣም ደክመው ለሚገኙ ሕዝቦቻችሁ እኔም ተመሳሳይ በሆነ መንገድ ሰላምታዬን አቀርብላችኋለሁ። በቤቱ “በላይኛው ክፍል” ውስጥ ያስተጋባው የጌታ ቃል እያንዳንዳችሁን ወጣት ለሆነችሁ አገራችሁ ለምትፈልገው እድገት አዲስ የሥራ ጥንካሬ እንዲሰጣችሁ እመኛለሁ። ገና ወጣት በነበረው የክርስቲያን ማኅብረተሰብ ላይ በበዓለ አምሣ የወረደው እሳት ለደቡብ ሱዳን ሕዝቦች በሙሉ አዲስ የተስፋ ብርሃን ይፈንጥቅ። እነዚህን ሁሉ ሐሳቦች በልቤ ውስጥ አኑሬ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” በማለት ሰላምታዬን በድጋሜ አቀርባለሁ።

ሰላም የአገር መሪዎች ሊያረጋግጡት የሚገባው የመጀምሪያው ተግባር ነው

ሰላም ጌታ ለእኛ የሰጠን የመጀመሪያው ስጦታ በመሆኑ የተነሳ የአገር መሪዎች በቅድሚያ ሊያረጋግጡት የሚገባው የመጀመሪያው ቃል ኪዳን ነው። ሰላም ለእያንዳንዱ ግለሰብ መብትና ለሕዝቡ ሁለንተናዊ እድገት መሰረታዊ የሆነ ነገር ነው። እግዚአብሔር አብ የሰላም ንጉሥ አድርጎ የላከው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልንከተለው የሚገባውን አብነት ሰጥቶናል። እርሱ ራሱ በከፈለው መስዋዕትነት እና ተዐዝዞ  ለዓለም ሰላም ሰቱዋል። ለዚህም ነው ታዲያ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ መላእክት ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም፣ ሰላምም እርሱ ለሚወዳቸው ሰዎች በምድር ይሁን!” በማለት ሰማያዊውን መዝሙር የዘመሩት። የደቡብ ሱዳን ሕዝቦች በሙሉ በአንድነት ያንን የመላእክት ድምጽ አዳምጠው በማስተጋባት “እግዚአብሔር ሆይ! እጅግ ታላቅ በሆነችው በደቡብ ሱዳን ምድር ውስጥ ያለው ታላቅ የደስታ ምንጭ ስለሆነው ስላንተ ፀጋን እናከብርኃለን፣ እናሞግስኃለን፡ ሰላም በሰፈነበት መልኩ እርስ በእርስ በመተባበር እንድንኖር አድርገን” (የደቡብ ሱዳን ብሔራዊ መዝሙር የመጀመሪያ አንቅጽ ላይ የተወሰደ)። የሰው ልጆች በሙሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ከሰማይ ሰራዊት ጋር አብረው የእግዚአብሔርን ክብር በመዘመር በሁሉም ወንዶችና ሴቶች መካከል ሰላም እንዲሰፍን እመኛለሁ!

የእግዚኣብሔር እይታ

2. ሁላችንም ይህ ስብሰባ ልዩ እና ልዩ በሆነ መልኩ የተዘጋጀ እንደ ሆነ እንገነዘባለን፣ ምክንያቱም በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና የአገር መሪዎች መካከል የተካሄደ የሁለትዮሽ ስብሰባ ወይም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አይደለም፣ እንዲሁም ከተለያዩ የክርስቲያን ማኅበር ተወካዮች ከተውጣጡ ሰዎች ጋር የተደረገ ስብሰባ አይደለም። ይልቁኑ መንፈሳዊ ሱባሄ ነው። ሱባሄ” የሚለው ቃል በራሱ እራሳችንን ከተለመደው የአኗኗር ሁኔታ ወይም እንቅስቃሴዎች ራሳችንን አቅበን ወደ አንድ አዲስ ለየት ባለ መልኩ ወደ ተዘጋጀ ስፍራ ለመሄድ መፈለግን ያመለክታል። "መንፈሳዊ" የሚለው ቅጥያ ስም  እንደሚያመለክተው ይህ አዲስ ቦታ እና ልምምድ ለራሳችን እና ለወከልነው ማኅበረሰብ መልካም ፍሬዎችን እንድናፈራ የሚያደርገን፣ በመተማመን የምንጸልይበት፣ ጥልቅ የሆነ አስተንትኖ የምናደርግበት እና እርቅ የሚፈጠርበት ግንኙነትን  የሚያመላክት መሆን አለበት።

የዚህ ሱባሄ ዋና ዓላማ በእግዚአብሔር ፊት በአንድነት እንድንቆም እና ፈቃዱን እንድናስተውል ማደርግ ነው። በእኛ ሕይወትና ለእኛ በአደራ የተሰጠንን የተጣለብንን ተልዕኮ ላይ ማሰላሰል፣ በአሁኑ እና በመጪው ጊዜ ሳይቀር ለደቡብ ሱዳን ሕዝቦች ያለንን ታላቅ የተከበረ የጋራ ኃላፊነት ለመገንዘብ እና እራሳችንን ለዚህ ተግባር ተፈጻሚነት ለማስገዛት፣ ለማበረታታት፣ እርቅ ለመፍጠር እና አገራችሁን ለመገንባት ነው። የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች! እግዚአብሔር እንደ ፖለቲከኛ እና እንዲሁም እንደ የሐሃይማኖት መሪዎች ሕዝቡን የመንከባከብ፣ የመምራት ኃላፊነት እንደሰጠን መርሳት የለብንም። እርሱ ብዙ ነገሮችን ለእኛ በአደራ ሰጥቶናል እናም በዚህ ምክንያት ከእኛ የበለጠ ይጠብቃል! በማኅበረሰባችን ውስጥ በተለይም ደግሞ ለተገለሉ እና በጣም ችግረኞች ለሆኑ ሰዎች በጣም አስፈላጊ የሆነውን የእኛን አገልግሎት እና አስተዳደር ለእኛ ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ለእኛን ማኅበረሰብ አባላት ለመጠበቅ ያስችለን ዘንድ ከፍተኛ ጥረት ይጠይቃል።

የፍትህ ረሃብተኞች እና ጥማተኞች ጩኸት በህሊናችን ውስጥ በማስተጋባት ቁርጠኛ የሆነ አገልግሎት እንድናደርግ ይጠይቀናል። እነዚህ ሰዎች በዓለም እይታ ዝቅተኛ የሆነ ቦታ ቢኖራቸውም ቅሉ በእግዚኣብሔር ዐይኖች ውስጥ ግን ከፍትኛ የሆነ ስፍራ አላቸው። "የእግዚአብሔርን እይታ" የሚለውን አገላለጽ በመጠቀም ጌታ ኢየሱስ ያለውን እይታ አስባለሁ። እያንዳንዱ መንፈሳዊ የሆነ ሱባሄ ልክ በእየለቱ የሕሊና ምርመራ እንደ ምናደርገው ሁሉ በመላው ሕይወታችን፣ በጠቅላላው ታሪካችን፣ በድክመታችን እና ሌላው ቀርቶ በመጥፎ ነገሮቻችን ውስጥ እንኳን ሳይቀር እውነትን ለማየት የሚችል ከእኛ ጋር በመሆን ሙሉ በሙሉ ወደዚህ እውነት እንድናመራ በሚያደርገን በጌታ እይታ ውስጥ እንድንቆም ያደርገናል። የእግዚኣብሔር ቃል ኢየሱስ ከደቀ-መዛሙርቱ ጋር በተገናኘበት ወቅት በእነርሱ ሕይወት ውስጥ ምን ያህል በጣም ወሳኝ የሆኑ ጊዜ እንደ ነበረ የሚገልጹ ድንቅ የሆኑ ምሳሌዎችን ይሰጠናል። ጌታ ሐዋሪያው ጴጥሮስን የተመለከተበትን ሦስት አጋጣሚዎችን አሁን ለማንሳት እፈልጋለሁ። 

ኢየሱስ ጴጥሮስን ለመጀመሪያ ጊዜ የተመለከተው ወንድሙ እንድርያስ ወደ ኢየሱስ አምጥቶት መሲሕ መሆኑን በነገረው ወቅት ነበር። ኢየሱስም ጴጥሮስን ትኩር አድርጎ ከተመለከተው በኋላ አንተ ጴጥሮስ ተብልህ ትጠራለህ አለው “ዮሐ 1፡41-42)። በኋላ ላይ ደግሞ ጌታ አንተ “ዓለት ነህ” በማለት በዚህ "ዓለት" ላይ ደግሞ ቤተ ክርስቲያኑን እንደ እንደ ሚገነባ ነግሮት ነበር፣ ይህም እርሱ ሕዝቡን ለማዳን ያለውን የደህንነት እቅድ ጴጥሮስ ያስፈጽም ዘንድ ያመለክታል። ኢየሱስ የመጀመሪያው እይታ ትኩረትን ያደርገው "በምርጫ" ላይ ሲሆን ይህም ለየት ላለ ተልዕኮ እንዲነሳሳ አደረገው።

ኢየሱስ ጴጥሮስን ለሁለተኛ ጊዜ የተመለከተው ደግሞ በጸሎተ ሐሙስ ምሽት ላይ ነበር። ጴጥሮስ ኢየሱስን ሦስት ጊዜ ክዶታል። ኢየሱስ በወታደሮች በግዳጅ ተይዞ በተወሰደበት ወቅት ጴጥሮስን አትኩሮ  ተመልክቶት ነበር፣ እርሱ በእዚያን ወቅት በከፍተኛ ደረጃ በሕማም ውስጥ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ሰላማዊ የሆነ ንስሃ በውስጡ እንዲቀሰቀስ አደረግ። ሐዋሪያው የጌታውን ጥሪ፣ መተማመን እና ጓደኝነቱን በመካዱ የተንሳ ወደ ውጪ ወጥቶ አምርሮ አለቀሰ (ማቴ 26:75) ። የኢየሱስ ሁለተኛ እይታ የጴጥሮስን ልብ ነካው፣ መንፈሳዊ ለውጥ እንዲያመጣ አደረገው።

በመጨረሻም ኢየሱስ ከሙታን ከተነሳ በኋላ በተብራጠስ ባሕር አቅራቢያ ኢየሱስ እንደ ገና እይታውን በጴጥሮስ ላይ በማድረግ ትወደኛለህን?” በማለት ሦስት ጊዜ ጥያቄ አቀረበለት። የእርሱን መንጋ እንዲጠብቅ እንደገና ተልዕኮ ይሰጠዋል፣ እናም ይህ ተልዕኮ የሕይወት መሥዋዕት በማስከፈል እንደ ሚጠናቀቅ አመላከተው (ዮሐ 21፡15-19)።

በእውነቱ ሁላችንም ለእምነት ሕይወት እንደተጠራንና በእግዚአብሔር እንደተመረጥን መናገር ይቻላል፣ በተጨማሪም ሕዝቦቻችን በታማኝነት እንድናገለግላቸው መርጠውናል። በዚህ አገልግሎት ውስጥ አንዳንድ ስህተቶች እንፈጽም ይሆናል፣ አንዳንዶቹ ትናንሽ ሊሆኑ ይችላሉ አንዳንዶቹ ደግሞ በጣም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ የተጸጸቱትን ሰዎች ኃጢአት ይቅር ይልላቸዋል። ሁልጊዜ የእርሱን ታማኝነት ያድሳል በተለይም ለእኛ እና ለሕዝቡ ያለውን ታማኝነት ያድሳል።

የተከበራችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ የኢየሱስ እይታ በእያንዳንዳችን ላይ እዚህ እና አሁን በእኛ ላይ ያርፋል። ዛሬ ኢየሱስ እኔን እንዴት ነው የሚመለከተኝ? ምን እንዳከናውን ነው የሚጠራኝ? እኔ ይቅር እንድል ጌታ ከእኔ የሚፈልገው ነገር ምንድነው? የተኛውን ባሕሪዬን እንድቀይር ነው ጌታ የሚፈልገው? አምላክ ለሕዝቦቹ መልካም ነገር እንዳከናውን የሰጠኝ ተልዕኮ እና ኃላፊነት ምንድን ነው? እነዚያ ሕዝቦች የእኛ ሳይሆኑ የእርሱ ናቸው፣ እርግጥ ነው እኛ ራሳችን የእዚያ ሕዝብ አባል ነን። በቀላሉ እኛ እነርሱን የማገልገል ኃላፊነት እና ልዩ ተልዕኮ አለብን ማለት ነው።

የተከበራችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ኢየሱስ በእያንዳንዳችን ላይ እዚህ እና አሁን እኛን በመመልከት ላይ ይገኛል። በፍቅር ይመለከተናል፣ አንድ ነገር ይጠይቀናል፣ አንድ ነገር ይቅር ይለናል፣ እናም ተልዕኮ ይሰጠናል። ይበልጥ ፍትሃዊ ዓለም በመፍጠር የእርሱ የሥራ ተባባሪዎች እንድንሆን መርጦን ለእኛ ትልቅ ቦታ ሰጥቶናል። የእርሱ ዓይኖች ልባችን ውስጥ በጥልቀት ገብተው እንደሚመለከቱ  እርግጠኞች መሆን እንችላለን; ይወዳል፣ ይለወጣል፣ ያስታርቀናል እንዲሁም አንድ ያደርገናል። የእርሱ ደግ እና መሐሪ ዓይኖች ወደ ኃጢአትና ሞት የሚያመሩትን ጎዳናዎች እንድንተው ያበረታቱናል፣ በተቃራኒው የሰላምና መልካም ጎዳናዎችን እንድንከተል ያደርጉናል።

3.የሕዝቡ እይታ

የእግዚአብሔር እይታ በተለየ ሁኔታ በእናንተ ላይ ነው፡ ሰላምን ያቀርብላችኋል። በተጨማሪም አንድ ሌላ እይታ እናንተን እይተመለከታችሁ ይገኛል፣ ይህም እይታ ፍትህን፣ እርቅን እና ሰላምን በከፍተኛ ሁኔታ እየፈለገ የሚገኘው የሕዝባችሁ እይታ ነው። በተመሳሳይ መልኩ በመንፈሳዊነት ለእናንተ አገር ዜጎች ያለኝን አጋርነት እያረጋገጥኩኝ፣ በተለይም ለስደተኞች እና ለታመሙ፣ በአገሪቱ ውስጥ ሆነው በከፍተኛ ጉጉት እየተጠባበቁ የሚገኙት እና ትንፋሻቸው እስኪያጥር ድረስ የዚህን ታሪካዊ ቀን ውጤት በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የአገሪቷ ዜጎች ሁሉ በመንፈስ ከእነርሱ ጋር መሆኔን ላረጋግጥላቸው እወዳለሁ። በእነዚህ የሱባሄ ቀናት በታላቅ ተስፋ እና ከልብ በመነጨ መልኩ ጸሎት በማድረግ አብረውን እንደ ነበሩ እርግጠኛ ነኝ። ኖኅ በወቅቱ የተከሰተውን የውሃ መጥለቅለቅ ፍጻሜ ለማረጋገጥ እና እግዚኣብሔር በሰዎች መካከል አዲስ የሰላም ዘመን መጀመሩን ለማወቅ የሚረዳውን የውይራ ዝንጣፊ  ርግቧ ይዛ እስክትመጣ ድረስ በተስፋ ተጠባበቀ (ኦ. ዘፍ. 8፡11) ። በተመሳሳይም መልኩም  ወደ አገራችሁ ስትመለሱ ሁሉንም አባላት ያሳተፈ እርቀና፣ ለሁሉም የሰላም እና የብልጽግና ዘመን ይዛችሁ ትመጡ ዘንድ ሕዝቦቻችሁ እየተጠባበቃችሁ ይገኛል።

በቅድሚያ የሚወዱዋቸውን ቤተሰቦቻቸውን እና ቤቶቻቸውን፣ ተበታትነው እና ተለያይተው የቀሩ እስካሁንም ቢሆን መገናኘት ላልቻሉ ቤተሰቦቻቸው፣ ልጆቻቸው እና አረጋዊያን፣ በግጭቶች እና በዓመፅ ምክንያት ከፍተኛ ችግር ለደረሰባቸው ሴቶች እና ወንዶች፣ በሞት በረሃብ እና በሐዘን ምክንያት እስካሁን እያነቡ የሚገኙ ሰዎች ሁሉ በመንፈስ ከእናንተ ጋር መሆኔን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። የድሆችንና የችግረኛውን ጩኸት በእርግጥ ሰምተናል፣ ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ ብሎ ይሰማል፣ ፍትህና ሰላምን ሊሰጣቸው ለሚፈልገው ወደ አባታችን ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ይደርሳል። እነዚህ በመከራዎች ውስጥ የሚገኙትን ነፍሳት በእየጊዜው እያሰብኩኝ እና የጦርነት እሳት ከስሞ እነርሱም ወደ እየቤቶቻቸው ተመልሰው በሰላም እና በእርጋታ ይኖሩ ዘንድ እጸፀልያለሁ። ሰላም በአገራችሁ ውስጥ ይሰፍን ዘንድ ሁሉን ቻይ ወደ ሆነው አምላክ እጸልያለሁ፣ እናም በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ሁሉ በሕዝቦች መካከል ሰላም ይወርድ ዘንድ እንዲሰሩ እጠይቃለሁ።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ሰላምን ማረጋገጥ ይችላል። ይህንን ደጋግሜ መናገር በፍጹም አልታክትም፣ ሰላምን ማረጋገጥ ይቻላል። ያም ሆኖ ይህ ይህ የእግዚአብሔር ታላቅ ጸጋ የሆነው ሰላም ማረጋገጥ ደግሞ የሕዝቡን ኃላፊነት በተሸከሙት ሰዎች ጫንቃ ላይ የገኛል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሳቱ የተነሳ እኛ ክርስቲያኖች ሰላምን ማረጋገጥ ይቻላል ብለን እናምናለን። እርሱ ክፉን ነገር በመልካም ቀይሩዋል። እርሱ የጦርነት ነበልባል የሆኑት እኩይ የሚባሉ ተግባራት ለምሳሌም  ኩራት፣ ስግብግብነት፣ የሥልጣን መሻት፣ ራስ ወዳድነት፣ ሐሰት እና ግብዝነት እነዚህ ሁሉም ነገሮች በሰላም መስፈን ምክንያት የተነሳ ድል እንደ ሚመቱ ለደቀመዛሙርቱ አረጋግጦላቸዋል።

በጸሎት መንፈስ በተሞላ ተስፋ ተሞልቼ ሁላችንም በተነሳሳ መንፈስ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚተጉ ሰዎችን እንድንደግፍ እና ሁላችንም በከፍተኛ ሁኔታ ሰላም አስከባሪዎች እንድንሆን፣ የወንድማማችነት መንፈስ ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ በመትጋት እና ከእያንዳንዱ የማኅበረሰብ አባላት ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመመሥረት፣ ጠንካራ፣ ቀጥተኛ፣ እና በድፍረት በተሞላ መንፈስ ሰላም ይረጋገጥ ዘንድ ውይይት፣ ድርድር እና የይቅርታ መንፈስ ይጀመር ዘንድ መትጋት ይኖርብናል። እንግዲያውስ አንድ የሚያደርጉዋችሁን ነገሮች እንድትሹ፣ አንድ ዓይነት ሰዎች በመሆናችሁ የተነሳ እናንተን የሚከፋፍሉዋችሁን ነገሮች ሁሉ ማሸነፍ እንድትችሉ የተቻልችሁን ሁሉ እንድታደርጉ እጠይቃችኋለሁ። ሰዎች ባለፈው ጊዜ በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ግራ ተጋብተዋል፣ ሰልችቱዋቸዋልም፣ በጦርነት ሁሉም ነገር ወድሙዋል! ዛሬ ሰዎችዎ የተሻለ ብሩህ ተስፋ ይጠብቃሉ፣ ይህም የሚረጋገጠው በእርቅ እና በሰላም ብቻ ነው።

በታላቅ ተስፋ እና እምነት ባለፈው መስከረም ወር ላይ የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የፖለቲካ ባለስልጣናት ተወካዮች የሰላም ስምምነት ፈርመዋል። እንደዚሁም ይህንን የሰላም ስምምነት ሰነድ የፈረሙትን እዚህ የሚገኙትን እና እንዲሁም እዚህ የሌሉትን ተወካዮች ሁሉ የሱዳን ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች የውይይት መንገድን በመምረጣቸው፣ ድርድር ለማድረግ ዝግጁ በመሆናቸው፣ ሰላምን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ በመሆናቸው፣ እርቅን ለመፍጠር ዝግጁ በመሆናቸው እና በስምምነቱ ላይ የተጠቀሱትን ሐሳቦች ተፈጻሚ ለማድረግ ላላቸው ፍላጎት ሁሉ ላደንቃቸው እፈልጋለሁ። የፖለቲካ እና የጎሳ ክፍፍል በተገቢው ሁኔታ ምላሽ እንደሚያገኝ እና ሁሉንም በዘላቂነት ተጠቃሚ የሚያደርግ ሰላም በመገንባት ዜጎች ያላቸውን ሕልም እውን እንዲያደርጉ በዘላቂነት እንደ ምትሰሩ ከልብ የመነጨ ተስፋ እንዳለኝ ልገልጽ እወዳለሁ።

በመጨረሻም በደቡብ ሱዳን የሲቪል እና የሐይማኖት መሪዎች ባለስልጣናት በዚህ ሱባሄ ላይ  በመሳተፋችሁ ምስጋናዬን እና አደናቆቴን እገልጻለሁ። ለሁሉም የደቡብ ሱዳን ሕዝቦች ከልብ የመነጨ መልካም ምኞቴን፣ ሰላም እና ብልጽጋን እንደ ምመኝላችሁ ልግልጽላችሁ እወዳለሁ። መሐሪ የሆነ አምላክ በደቡብ ሱዳን የሚገኙ የእያንዳንዱን ሰው ልብ እንዲነካ፣ በጸጋው እና በበረከቱ አገራችሁን እንዲሞላ፣ ዘላቂ የሆነ የሰላም ፍሬ እንዲሰጣችሁ፣ እንዲሁም በአገራችሁ ውስጥ እየፈሰሰ የሚገኘው የአባይ ወንዝ ሕይወት እና ብልጽግና እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ። በመጨረሻም በእግዚአብሔር ጸጋ እዚህ ከእኔ ጋር ከሚገኙት ውድ ከሆኑት ወንድሞቼ ጋር በጋራ በመሆን ውድ አገራችሁን እንደ ምጎበኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

የማሳረጊያ ጸሎት

4. ይህንን አስተንትኖ የቅዱስ ጳውሎስን ጥሪ ተከትዬ ለማጠቃለል እፈልጋለሁ። ሐዋርያው እንዲህ ይላል “እንግዲህ ከሁሉ አስቀድሞ ልመናና ጸሎት፣ ምልጃና ምስጋና ለሰዎች ሁሉ፣ ለነገሥታትና ለባለ ሥልጣናት ሁሉ እንዲደረግ አሳስባለሁ፤ ይህም በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትና በቅድስና ሁሉ፣ በሰላምና በጸጥታ እንድንኖር ነው” (1 ጢሞ 2፡1-2) በማለት ጽፉኋል። ቅዱስ አባት ሆይ፣ ዘለዓለም መልካም የሆንክ አባት ሆይ በመንፈስ ቅዱስ እንድንታደስ ትጠይቀናለህ፣ ከሁሉም በላይ ኃይልህን የምሕረት ጸጋ በማምጣት አሳየን። በክርክርና በብጥብጥ በተበላሸው ዓለም ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን የሰዎችን ልብ በአባትነት ፍቅር በመንካት ሰዎች እርቅ እንዲፈጥሩ እንደ ምታደርግ እናውቃለን። ሰዎች ብዙን ጊዜ የአንተን ቃል ኪዳን ጥሰዋል። ሆኖም እነርሱን ከመተው ይልቅ ከእነርሱ ጋር ያለህን ቁርጠኛ የሆነ ግንኙነት ልጅህ እና አዳኝ በሆነው በኢየሱስ ታድካቸው እንደገና ጠንካራ የሆነ ለዘዓለም  የማይበጠስ ትስስር ፈጠርክ።

ሰለዚህ ብርቱ በሆነው በአንተ መንፈስ ቅዱስ ኃይል የሰዎችን ልብ ሁሉ ትነካ ዘንድ እና በጠላትነት የተፈራረጁ ሰዎች ወደ ውይይት እንዲመለሱ፣ ተቀናቃኝ የነበሩት ሁሉ ደግሞ እጅ ለእጅ ተያይዘው እና ሰዎች በአንድነት መንፈስ እንዲገናኙ ትረዳቸው ዘንድ እንጠይቅኃለን። አባት ሆይ በአንተ ስጦታ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መፍትሄ ለመፈለግ በሙሉ ልብ እንድንተጋ፣ ለጥላቻ ሳንሸነፍ እና ፍቅር በጥላቻ ላይ ድል እንዲጎናጸፍ፣ ሰላምን ፍለጋ የሚደርገው ጥረት ክርክሮችን እንዲያስወግድ፣ ፍቅር አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ ይቅርታን በማድረግ እና በምሕረትህ ላይ ብቻ በመተማመን ተመልሰን ከአንተ ጋር እንድንገናኝ አድርገን። መንፈስ ቅዱስህን ለሁሉም ማዳረስ እንችል ዘንድ ልባችን የተከፈተ እንዲሆን አድርግልን፣ ስለ ክርስቶስ ስም ብለን አዲስ ህይወት እንድንኖር፣ ስምህን ለዘለዓለም  በማወደስ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ማገልገል እንችል ዘንድ ቅዱስ መንፈስህ ያነሳሳን፣። አሜን!

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን ለዘላለም በልባችሁ ውስጥ ይኑር!

 

11 November 2019, 11:38