ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “በዓለም ላይ የሚታየውን ኢፍትሃዊነት በግድየለሽነት አትመልከቱ” አሉ

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሚያዝያ 13/2011 ዓ.ም. ድምቀት ተከብሮ ማለፉ ይታወሳ። በታላላቅ መንፈሳዊ በዓላት በተለይም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት የገና በዓል ቀን እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በተነሳበት የትንሳኤ ቀን ልማዳዊ በሆነ መልኩ አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በላቲን ቋንቋ Urbi et Orbi በአማሪኛው ለከተማው (ሮም) እና ለዓለም  የተሰኘ መልእክት በዓላቱን አስመልክተው እንደ ሚያስተላልፉ ይታወቃል። በእዚህም መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 13/2011 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ Urbi et Orbi በአምሪኛው ለከተማው (ሮም) እና ለዓለም በተሰኘው መልእክታቸው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት “ድልድዮች እንጂ ግንቦችን አትስሩ፣ በዓለም ላይ እየታየ ለሚገኘው ኢፍትሃዊ ተጋብር በግድየለሽነት መንፈስ አትመልከቱ”  ማለታቸው ተገሉጹዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሚያዝያ 13/2011 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኝዎች በእለቱ የጎትጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የተከበረውን የትንሣኤ በዓል ምክንያት አድርገው ያስተላለፉትን Urbi et Orbi በአምሪኛው ለከተማው (ሮም) እና ለዓለም የተሰኘውን መልእክታቸውን ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንላችሁ!

ዛሬ የቤተ ክርስቲያናችን የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት “ኢየሱስ ተነስቷል!" ብለው ያወጁትን አዋጅ በድጋሚ ታድሳለች። እኛ ከአንዱ አፍ ወደ ሌላው አፍ፣ ከአንዱ ልብ ወደ ሌላው ልብ በመሄድ "ሃሉሉያ፣ ሃሉሉያ!" የተሰነኘው የምስጋና ውዳሴ በድጋሚ እናስተጋባለን። በፋሲካ በዓል ማለዳ ላይ ለቤተ ክርስቲያን እና ለሰው ዘር በተለይ ለወጣቱ ትውልድ ሁሉ በቅርብ ጊዜ ወጣቶችን በተመለከተ ያፋ ባደረኩት ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ውስጥ በመግቢያው ላይ ያስቀመጥኩትን ቃል ተጠቅሜ እንዲ ለማለት እፈልጋለሁ፡

“ክርስቶስ ሕያው ነው! እርሱ ተስፋችን ነው፣ እናም በአስደናቂ መንገድ ወጣቶችን ወደ ዓለማችን ያመጣል። እርሱ የሚነካቻው ነገሮች ሁሉ ወጣት፣ አዲስ፣ ሙሉ ህይወት ያላቸው ነገሮች ይሆናሉ። የመጀመሪያዎቹን ቃላት ተጠቅሜ ለእያንዳንዱ ወጣት ክርስትያን እንዲህ ማለት እፈልጋለሁ፣ ክርስቶስ ሕያው ነው እኛም በሕይወት እንድኖር ይፈልጋል! እርሱ በእናንተ ውስጥ ነው፣ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፣ እርሱ አይተዋችሁም! ምንም ያህል ብትቅበዘበዙም ከሙታን የተነሳው እርሱ ግን ሁል ጊዜ እዚያ ነው። እርሱ እናንተን ይጠራችኋል፣ ወደ እርሱ ተመልሳችሁ ሁሉንም ነገር በአዲስ መልክ እንድትጀምሩ እናንተ እየተጠባበቃችሁ ይገኛል። በሐዘን፣ ቅሬታ ወይም በፍርሀት፣ በጥርጣሬ ወይም በውርደት መንፈስ የተነሳ የእርጅና ስሜት ሲሰማችሁ ጥንካሬያችሁን እና ተስፋችሁን ለመመለስ እርሱ ሁል ጊዜ በእዚያው ይገኛል” (ክርስቶስ ሕያው ነው ከተሰኘው ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ከአንቀጽ 1-2 ላይ የተወሰደ)።

የተወደዳችሁ ወንድሞች እና እህቶች ይህ መልዕክት በአለም ውስጥ ለሚገኝ ለእያንዳንዱ ሰው ጭምር የተላለፈ መልእክት ነው። የክርስቶስ ትንሣኤ ለሁሉም ወንድ እና ሴቶች ሁሉ የአዲስ ሕይወት መርህ ነው፣ ከእውነተኛው ልብ እና ሕሊና የሚጀምር የሕይወት ለውጥ መሰረት ነው። በተጨማሪም ፋሲካ በዓል ከኃጢአትና ከሞት ባርነት ነፃ የወጣ፣ ለእግዚኣብሔር መንግሥት ራሱን ክፍት ያደርገ ዓለም፣ የፍቅር መንግሥት፣ የሰላም እን የወንድማማችነት መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችል የአዲሱ ዓለም መጀመሪያ ነው።

ክርስቶስ ሕያው ነው፣ እርሱ ከእኛ ጋር ይኖራል። ከሙታን በመነሳቱ የተነሳ እርሱ የእርሱን በብርሃን የተሞላ ፊት ያሳየናል፣ እናም እኛን በችግራችን፣ በሕመማችን እና በሐዘናችን ውስጥ ሁሉ ሆነን እንድንኖር አይተወንም። ሕያው የሆነው እርሱ ቀጣይነት ባለው ግጭት ውስጥ የሚገኙትን እና በእነዚህ ግጭቶች የተነሳ በየጊዜው መከራቸው እየበዛ ለሚገኘው የሶሪያ ሕዝብ ተስፋ ይሁን። አሁን ለሰዎች ነፃነት፣ ሰላም እና ፍትህ ተስፋቸውን ለመመለስ ከሚደረገው ጥረት ባሻገር በመሄድ ለሰብአዊ ቀውስ የተጋለጡትን እና ከመኖሪያ ሥፋራዎቻቸው የተፈናቀሉትን በተለይም ደግሞ እንደ ሊባኖስ ባሉ አገሮች ውስጥ ተጠልለው የሚኖሩ ስደተኞችን ወደ እናት አገራቸው እንዲመለሱ ከሁሉም ጋር በመተባበር ፖለቲካዊ የሆኑ መፍትሄዎች እንዲመጡ የገቡትን ቃል ኪዳን ማደስ ያስፈልጋል።

የፋሲካ በዓል ቀጣይነት ባለው መልኩ በመከፋፈል እና በውጥረት ላይ በሚገኙ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ላይ ትኩረታችንን እንድናደርግ ያደርገናል። በአገባቢው የሚገኙ ክርስቲያኖች ከሙታን የተነሳውን ጌታ እና ሕይወት በሞት ላይ ድል የተጎናጸፈበትን እለት በትዕግስት ተመልተው መመስከር ይኖርባቸዋል። በተለይም ደግሞ በየመን የሚኖሩ ሕዝቦችን በተለይም በአስቸጋሪ ሁኔታ እና በጦርነት ውስጥ የሚገኙ ሕጻናትን ለማሰብ እውዳለሁ። በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ሁሉም የመንግስት መሪዎች እና ህዝቦች ከእስራኤል እና ፍልስጤም ጀምሮ በዚህ በትንሳኤው ብርሃን ተሞልተው ለሰላም እንዲሰሩ እና የእነዚህን በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች ችግር ለማቃለል እና ሰላምና መረጋጋትን ለወደፊት እውን ለማድረግ እንዲሰሩ የትንሳኤው ብርሃን እንዲያበራላቸው እመኛለሁ።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሊቢያ በተነሳው ግጭት እና የደም መፍሰስ ሰለባ የሆኑ ራሳቸውን መከላከል ባለማቻላቸው የተነሳ በተለይም በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለሞት የተጋለጡ ሰዎችን ፣ በአስገዳጅ ሁኔት ቤት ንበረታቸውን ጥለው የተሰደዱ ቤተሰቦችን ለማስታወስ እወዳለሁ። በዚህ ግጭት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑት ባለድርሻ አካላት ኃይል ከመጠቀም ይልቅ ውይይት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ ከእዚህ ቀደም የነበሩትን ግጭቶች እና የፖለቲካ አለመረጋጋቶች ምክንያት የፈጠሩት ቁስሎች ዳግመኛ በአዲስ መልክ እንዳያገረሹ በጥንቃቄ እንዲሰሩ አሳስባቸዋለሁ።

ሕያው የሆነው ክርስቶስ ተወዳጅ በሆነው በአፍሪካ አህጉር ውስጥ አሁንም ቢሆን በማህበራዊ አለመረጋጋት፣ ግጭቶች፣ እና አንዳንድ ጊዜ አካራሪዎች በሚፈጽሙት ጥቃት የተነሳ ለስጋት፣ ለጥፋትና ለሞት የተጋለጡትን በተለይም በቡርኪና ፋሶ፣ በማሊ፣ በኒጀር፣ በናይጀሪያ እና ካሜሩን ሰላሙን ያወርድ ዘንድ ምኞቴ ነው። በአሁኑ ወቅት ፖለቲካዊ የሆነ አለመረጋጋት በከፍተኛ ደረጃ እየታየባት የምትገኘውን ሱዳን ለማስታወስ እፈልጋለሁ፡ የሁሉም ሕዝብ ድምጽ እንደሚሰማ እና ሀገሪቷ ለረጅም ጊዜ ስትመኘው የነበረው ነጻነት፣ እድገትና ደህንነት ይረጋገጥ ዘንድ ሁሉም የአገሪቷ ዜጎች በዚህ ረገድ እንደ ሚሰሩ ተስፋዬ ነው።

ከሞት የተነሳው ጌታ ከበርካታ ቀናት በፊት በቫቲካን በተካሄደው ሱባሄ ተካፋይ የነበሩትን የደቡብ ሱዳን የሲቪል ባለስልጣናት እና የሃይማኖት መሪዎች ለሰላም የሚያደርጉትን ጥረት ይደግፍ። በእዚያች አገር ውስጥ የተከፈተው አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ሁሉም የፖለቲካ፣ የማህበራዊ እና የኃይማኖት ተቋማት ለጋር ተጠቃሚነት እና በአገሪቷ ውስጥ እርቅ ለማስፈን በንቃት ይሰሩ ዘንድ አሳስባለሁ።

ይህ የትንሳኤ በዓል ቀጣይነት ባለው መልኩ በግጭቶች ለሚሰቃዩ በዩክሬይን ምስራቃዊ ክፍል ለሚገኙ ሕዝቦች መጽናናትን ያምጣ። የሰብዒዊ ርዳታዎችን እና ዘላቂ የሆነ ሰላምን ለመፍጠር እየተደረጉ የሚገኙትን ጥርቶች ጌታ ያበረታታ።

በተለያዩ ፖለቲካዊ እና እኮኖሚያዊ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ በአሜሪካ አህጉር ውስጥ ያሉ አገራትን የትንሳኤው ደስታ ሕይወታቸውን ይሙላ። በተለይም የቬንዙዌላን ሕዝቦች እና ተለዋዋጭ በሆኑ ችግሮች ምክንያት የሕይወት ዋስታናቸውን ማረጋገጥ ያልቻሉ ሕዝቦችን ሁሉ ለማስታወስ እፈልጋለሁ። የፖለቲካ ሃላፊነቶች የተጣሉባቸውን ሰዎች በሙሉ በኅብረተሰቡ ውስጥ ያደረሱትን ኢፍትሀዊ ድርጊቶች፣ የመብት ጥሰቶች እና የጥቃት ድርጊቶች ለማቆም እና የክፍፍል መንፈስን ለመፈወስ እና ህዝቡ ሰብዓዊያ የሆነ እርዳታ ያገኙ ዘንድ ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹ ጌታ እንዲረዳቸው እጸልያለሁ።

ከሙታን የተነሳው ጌታ በአሁኑ ወቅት በኒካራጓ ሰላምን ዘላቂ በሆነ መልኩ ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ እየተደረጉ የሚገኙትን ተግባሮች አጠናክረው ይቀጥሉ ዘንድ እና ሁሉንም የኒካራጓን ሕዝብ ተጠቃሚ ማደርግ የሚችል ሰላማዊ ውይይት እንዲካሄድ የሚደርገውን ጥረት ጌታ ይደግፈው።

በዘመናችን እየተካሄዱ የሚገኙትን በጣም ብዙ የሆኑ ግጭቶችን እያየን እንዳላየ እንዳንሆን እና በግድዬለሽ ስሜት ጉዳዩን እንዳንመለከት የሕይወት ጌታ የሆነው እርሱ ይርዳን። የግድግዳዎች ሳይሆን የድልድዮች ገንቢዎች እንድንሆን ጌታ ይርዳን። በጦርነት ቀጣናዎች እና በአከባቢያችን በሚገኙ በከተማዎች ውስጥ የእርሱ ሰላም እንዳይሰፍን በማደናቀፍ ላይ የሚገኙትን የጦር መሳሪያዎችን ለማጋበስ የሚደረገውን ፉክክር በመተው የአገራት ባለስልጣናት ገንዘቡን ለአገራቸው ሕዝብ የኢኮኖሚ ግንባታ ያውሉት ዘንድ ጌታ እንዲደግፋቸው እጸልያለሁ። የመካነ መቃብር ስፍራ ላይ የነበረውን ድንጋይ ከፍቶ የተነሳው ክርስቶስ የተጎጂዎችን፣ የደካማዎችን፣ የድሆችን፣ ስራ አጥ የሆኑ ሰዎችን፣ የተገፉትን፣ እና ቁራሽ ዳቦ፣ መጠጊያ እና ሰብዓዊ መብታቸው እውቅና እንዲሰጠው ፈልገው ወደ ቤታችን መጥተው በሮቻችንን ለሚያንኳኩ ሰዎች ልባችንን መክፈት እንችል ዘንድ ይርዳን።

 

21 April 2019, 16:52