ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸሶስ “ከሙታን የተነሳው ጌታ ሁል ጊዜም ቢሆን ከእኛ ጋር ይኖራል” ማለታቸው ተገለጸ።

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በትላንታናው እለት ማለትም በሚያዝያ 13/2011 ዓ.ም ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት የትንሳሄ በዓል በታላቅ መንፈሳዊነት ተክብሮ ማለፉ ይታወሳል። ይህ በዓል በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በታላቅ መንፈሳዊነት በተከናወነው እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመሩት መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉ የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው በታላላቅ መንፈሳዊ በዓላት በተለይም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት የገና በዓል ቀን እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በተነሳበት የትንሳኤ ቀን ልማዳዊ በሆነ መልኩ አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በላቲን ቋንቋ Urbi et Orbi በአማሪኛው ለከተማው (ሮም) እና ለዓለም  የተሰኘ መልእክታቸውን አስተላፈው ካበቁ በኋላ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በመስጠት ከሚደገሙ ጸሎቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰውና በተለይም ክርስቶስ ከሙታን ከተነሳበት የትንሳኤ በዓል ጀምሮ እስከ በዓለ ሃምሳ ድረስ የሚደገመውን “የሰማይ ንግስት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ እንደ ተለመደው በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ባደርጉት አስተንትኖ እንደ ገለጹት “ከሙታን የተነሳው ጌታ ሁልም ጊዜም ቢሆን ከእኛ ጋር ይኖራል” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያሰሙትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ እና በእነዚህ ሳምንታት ውስጥ በታላቅ አግራሞት ትላንትና (ሚያዚያ 13/2011 ዓ.ም) ያከበረነውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ  የትንሳኤ በዓል በማክበር ደስታችንን እንገልጻለን። በፋሲካ በዓል ምሽት ላይ በዶ በነበረው በክርስቶስ መካነ መቃብር ላይ መላእክት የተናግሩት ቃል አሁንም ያስተጋባል። በመጀመሪያ ቅዳሜ ቀን ማታ ጎህ ሊቀድ ሲል ወደ መካነ መቃብር ስፍራ ሄደው ለነበሩት ሴቶች መላአክቱ “ለምንድነው ሕያው የሆነውን በሙታን መካከል የምትፈልጉት” እርሱ እዚህ የለም ተነስቱኋል” (ሉቃስ 24፡5-6) በማለት ተናግረው ነበር። የክርስቶስ ትንሳኤ በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ እጅግ አስደንጋጭ ክስተት የሆኑትን በኃጢአትና በሞት ላይ የእግዚአብሔር ፍቅር የተጎናጸፈውን ድል የሚያረጋግጥልን እና የሕይወት ተስፋችን እንደ ዐለት ጠንካራ መሠረት ያለው እንዲሆን ያደረገ ክስተት ነው። ይህም በሰው ልጆች አእምሮ ሊታሰብ የማይችል ነገር ተከሰተ "የናዝሬቱን ኢየሱስ [...] ከስቃይ እና ከሞት ነጻ አድርጎ እግዚአብሔር ከሞት አስነሣው” (የሐዋ. 2፡22.24)።

“የመላእክት” በመባል በሚታወቅው እለተ ሰኞ ቀን ውስጥ በስርዓተ አምልኮ ወቅት ከማቴዎስ (8፡8-15) ተወስዶ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ባዶ የነበረውን የኢየሱስ መካነ መቃብር በቅርበት እንድንመለከት ያደርገናል። ሴቶች በፍርሃትና በደስታ ተሞልተው መልካሙን ዜና ለደቀመዛሙርቱ ለማድረስ በፍጥነት እየሮጡ ነበር፣ በዚያም ጊዜ ጌታ ኢየሱስ በፊት ለፊታቸው ሆኖ ታየ። እነርሱም “ወደ ኢየሱስ ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት” (ማቴ 28፡9)። ኢየሱስ ፍርሃታቸውን በሙሉ ከልባቸው አስወግዶ ምን እንደተፈጠረ ለወንድሞቻቸው ያሳውቁ ዘንድ የበለጠ ማበረታቻ ሰጣቸው። በሁሉም ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የሴቶቹ ማለትም የመግደላዊት ማርያም እና የሌሎቹ ሴቶች ወሳኝ ሚና በመግለጽ ሴቶቹ የትንሣኤ የመጀመሪያ ምሥክሮች እንደሆኑ ያብራራሉ። ወንዶቹ በፍርሃት ተውጠው ስለነበረ በአንድ ክፍል ውስጥ ቆልፈው ተቀምጠው ነበር። ጴጥሮስና ዮሐንስ የመግደላዊት ማርያምን መልእክት ካዳመጡ በኋላ “ክፍት እና ባዶ ነው” የተባለውን የመካነ መቃብር ስፍራ ለማየት ወደ እዚያው በፍጥነት ሄዱ። ክርስቶስ ከሙታን መነሳቱን እና እርሱ ሕያው መሆኑን በቅድሚያ ያወጁት ግን ሴቶቹ ነበሩ።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ዛሬ “አትፍሩ፣ ሂዱና ይህን አውጁ . . .” (ማቴ 28፡10) በማለት ኢየሱስ ለሴቶቹ የተናገረው ቃል ዛሬም ለእኛ ያስተጋባል። በሕማማት ሳምንት ውስጥ ካከብርናቸው የጸሎተ ሐሙስ ማታ፣ ስቅለተ ዐርብ እና ከትንሣኤ በዓላት በሁኋ በመቀጠል ዛሬ ደግሞ ሕያው በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በማሰላሰል ላይ እንገኛለን። እኛም በግላችን እሱን ለማግኘት እና እርሱን ለማወጅ እና የእርሱ ምሥክሮች እንሆን ዘንድ ተጠርተናል።

በእነዚህ ቀናት ውስጥ ከጥንታዊው የፋሲካ በዓል ስነ-ስርዓት ውስጥ በተወሰደው "ክርስቶስ ተስፋዬ ከሙታን ተነስቷል!" በማለት ደግመን እንናገራለን። እኛም በእርሱ አማካይነት ተነስተናል፣ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻግረናል፣ ከኃጢአት ባርነት ወደ ፍቅር ነጻነት ተሻግረናል። እንግዲያውስ የትንሳኤው በዓል ካመጣልን  የመጽናኛ መልእክት ውስጥ ለመድረስ እንድንችል እና በእርሱ ብርሃን ታግዘን ራሳችንን ከነበርንበት የሐዘን ጨለማ እና ፍርሃት አውጥተን ወደ ተሻለ ብርሀን ላይ ለመድረስ እንችል ዘንድ እንዲረዳን እንፍቀድለት። ከሙታን የተነሳው ጌታ ከእኛ ጋር ጎን ለጎን ሆኖ ይጓዛል። እርሱን ለሚጠሩ እና እርሱን ለሚወዱት ሰዎች ይገለጻል። በመጀመሪያ ደረጃ በጸሎት አማካይነት የሚገልጽ ሲሆን በመቀጠልም ቀለል ባለ መልኩ በእመነት መንፈስ በተሞላ መልኩ በደስታ እና በአመስጋኝነት መንፈስ በምንኖርበት ወቅት እርሱ ወደ እኛ ይቀርባል። የትብብር፣ የመቀባበል፣ የጓደኝነት መንፈስ እና ተፈጥሮን እየተመለከትን በምናሰላስልበት ወቅት ሁሉ እርሱ ለእኛ ቅርብ መሆኑን እንገነዘባለን። በዚህ የትንሳኤ በዓል ወቅት ሕያው የሆነው ክርስቶስን በሕይወታችን ውስጥ ማጣጣም እንችል ዘንድ እርሱ ራሱ እንዲረዳን እንጠይቀው።

21 April 2019, 16:57