ፈልግ

የሰማይ ንግሥት የሚለው ጸሎት ምንድን ነው የሰማይ ንግሥት የሚለው ጸሎት ምንድን ነው 

የሰማይ ንግሥት የሚለው ጸሎት ምንድን ነው

ይህ የሰማይ ንግሥት የሚለው መዝሙር ከሌሎች ኣራት የማርያም መዝሙሮች ማለትም የኣዳኛችን እናት የሰማይ ንግሥትና ጸጋን የተሞላሽ ከሚሉት ጋር የማርያም መዝሙር በመባል ይታወቃል።እኣኣ ማለትም በ 1742 ርሊጳ ቤኔዴክቶስ 14ኛ ይህ የሰማይ ንግሥት የሚለው ጸሎት የክርስቶስን ከሞት መነሳት በማስመልከት የእግዚኣብሔር መልኣክ ማርያምን ኣበሰራት በሚለው ተተክቶ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ ተቁሞ እንዲደገም አዘዋል።

የዚህ ዝግጅት አዘጋጅ እና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ይህም ጸሎት ልክ እንደ የእግዚኣብሔር መልኣክ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በጠዋት በቀትርና በማታ የሚደገም ሲሆን ዓላማውም ቀኑን ለእግዚኣብሔርና ለማርያም ለመዋጀት ነው።ይህ ጥንታዊ  መዝሙር ልክ እንደ አንድ ጥንታዊ ሃይማኖታዊ እምነት ከኣምስተኛው እስከ ዐሥረኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ሲሆን በስፋት የተሰራጨው ግን በ 13ኛው ክፍለ ዘመን ፍራንቺስካውያን በሚደግሙት የመዝሙር ጸሎት ከሰፈረ በኋላ ነው። መዝሙሩርም በኣራት ኣጠር ባሉ ስንኞች የተዋቀር ሲሆን ሁሉም ስንኞች ሃሌ ሉያ በሚለው ቃል ይደመደማሉ። ይህም ጸሎት ምዕማናን ሁሉ ማርያምን የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ በማለት የክርስቶስን ከሞት መነሳት ኣብረው ይወድሳሉ።እኣኣ በሚያዝያ 6 2015 ርሊጳ ፍራንቼስኮስ ከፋሲካ ቀጥሎ ባለው ቀን የሰማይ ንግሥት የሚለው ጸሎት ሲመሩ ይህንን ጸሎት በምናደርስበት ጊዜ ልባችን በምን ዓይነት ሁኔታ መድገም እንዳለበት ምክራቸውን ለግሰዋል።እመቤታችን ድንግል ማርያም ደስ እንዲላት ጩኸታችንን ወደ እርሷ እናቀርባለን ምክንያቱም በማህጸኗ ተሸክማው የነበረ ቃል እንደገባልን ከሙታን ተነስቷል ራሳችንንም በእርሷ ኣማላጅነት ሥር እናስገዛለን። በእርግጥም የእኛ ደስታ የማርያም ደስታ ግልባጭ ነው ምክንያቱም እመቤታችን ድንግል በትልቅ እምነት ማርያም የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሁሉንም ክስተቶች በልቧ ጠብቃ ይዛለችና። ይህንን ጸሎት ሁሉም በታላቅ መንፈሳዊ ልጅነትና ደስታ ይዘምሩታል ምክንያቱም እናታቸው ደስተኛ ናትና።

22 April 2019, 17:01