ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ሁሉንም ነገር በፍትህ አግባብ ብቻ መፍታት ስለማይቻል ይቅር ማድረግ ይገባል”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወይም በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሻ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የጠቅላላ የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በዛሬው እለት ማለትም በሚያዝያ 16/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደርጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከዚህ ቀደም “አባታችን ሆይ” በሚለው ጸሎት ዙሪያ ላይ በተከታታይ ሲያደርጉት የነበረው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዚህ “አባታችን ሆይ” በሚለው ጸሎት ዙሪያ ላያ በሚያዝያ 16/2011 ዓ.ም ባደርጉት የክፍል 13 የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው  “እኛን የበደሉንን ይቅር እንደ ምንል” በሚለው አባታችን ሆይ በሚለው ጸሎት ውስጥ በሚገኘው የመማጸኛ ጸሎት ላይ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ሁሉንም ነገር በፍትህ አግባብ ብቻ መፍታት ስለማይችላ ለሌሎች ይቅርታ ማደርግ ይገባል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሚያዝያ 16/2011 ዓ.ም ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ የምናደርገው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የሚያጠነጥነው እኛም የበደሉንን ይቅር እንደ ምንል” (ማቴ 6፡12) በሚለው “አባታችን ሆይ” በሚለው ጸሎት ውስጥ በሚገኘው 5ኛው የመማጸኛ ጸሎት ይዘት ላይ ይሆናል። ሰው በእግዚአብሔር ፊት ባለዕዳ መሆኑ ተገቢ መሆኑን ተመልክተናል፡ ከእርሱ ዘንድ ተፍጥሮአዊ የሆኑ ነገሮችን እና ጸጋን ጨምሮ ሁሉንም ነገር ተቀብለናል። ሕይወታችን ተፈልጋ የመጣች ብቻ ሳትሆን ነገር ግን ተወዳ ጭምር የመጣች ናት። ለመጸለይ እጆቻችንን ለመዘርጋት እንኳን ተገቢዎች አይደለንም። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ “self made man” እራሱን በራሱ የፈጠረ ማንም ሰው የለም። ሁላችንም ብንሆን የእግዚኣብሔር እና መልካም የሆነ ሕይወት እንዲኖረን ሁኔታዎችን ያመቻቹልን የብዙ ሰዎች ባለዕዳዎች ነን። የእኛ ምንነት የተገነባው በተቀበልናቸው መልካም ነገሮች ላይ ነው።

የሚጸልይ ሰው “አመሰግናለሁ” የሚለውን ቃል ይማራል እግዚአብሔር ለእርሱ ወይም ለእርሷ ቸርነቱን እንዲሰጣቸው ይጠይቃል። እኛ ይህንን ጸጋ በተቻለ መጠን ባላማቋረጥ ብንጠይቅ እንኳን ከፍለነው ልንጨርሰው የማንችለው በማያቋርጥ መልኩ የእግዚኣብሔር ባለዕዳዎች ነን፡ ምክንያቱም እኛ እርሱን ከምንወደው በላይ እርሱ እኛን እስከ ዘለዓለም ይወደናልና ነው። እንግዲያውስ በክርስትና ትምህርቶች ላይ ተመስርተን ለመኖር ስንሞክር በሕይወታችን ውስጥ ሁልጊዜም ቢሆን ይቅርታ መጠየቅ የሚገባን ነገሮች ይከሰታሉ፡ በስንፍና የተነሳ በከንቱ ያሳለፍናቸውን ቀናት፣ ልባችን በቂም የተሞላበትን እለት. . .ያለ መታደል ሆኖ እነዚህን የመሳሰሉ ልምዶቻችን ናቸው እንግዲህ “በደላችንን ይቅር በልልን” ብለን እንድንጸልይ የሚያስገድዱን።

በደንብ ካሰብንበት ይህ የመማጸኛ ጸሎት በመጀመሪያው ክፍል ላይ ብቻ ተገድቦ ሊቀር ይችል ነበር፣ ነገር ግን ኢየሱስ ከዚህ ባሻገር በመሄድ ሌላ ሁለተኛ አገላለጽ በመጠቀም ከመጀመሪያ መማጸኛ ጋር አንድ እንዲሆን ያደርገዋል። በበጎነት የተሞላው እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ያለው ግንኙነት ከወንድሞቻችን ጋር በአዲስ መልክ ሊኖረን ስለሚገባው ግንኙነት እንድናስብ ያደርገናል። መልካም የሆነው እግዚኣብሔር ሁላችንም መልካም እንድንሆን ይጋብዘናል። በዚህ ጸሎት ውስጥ የሚገኙ ሁለቱን መማጸኛዎች የሚያገናኘው “እንደ” የሚለው ቃል  ነው።

እያንዳንዱ ክርስቲያን የኃጢአት ስርዬት እንደሚያገኝ ያውቃል። ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ስለ እግዚአብሔር ገጽታ በሚናገርበት ወቅት ይጠቀምበት የነበረው አገላለጽ እርሱ በመለኮታዊ ርኅራኄ የተሞላ አድርጎ ነበር የሚያቀርበው። ለዚህም ነው ታዲያ እላችኋለሁ፤ እንደዚሁም ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ፣ ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል” (ሉቃስ 157) በማለት የተናገረው በዚሁ ምክንያት ነው። በቅዱስ ወንጌል ከልቡ ተጸጽቶ እና እግዚኣብሄር መልሶ በምሕረቱ እንዲያቅፈው ጠይቆ ያፈረ ማንም እንደ ሌለ ይናግራል።

ነገር ግን የእግዚአብሔር የተትረፈረፈ ጸጋ ሁልጊዜ ቢሆን እኛ ተግተን መሥራት እንደ ሚገባን ያሳስበናል። በጣም ብዙ የተቀበለ ሰው በጣም ብዙ መስጠት እንደ ሚገባው መገንዘብ ይኖርበታል። ወንጌላዊው ማቴዎስ "አባታችን ሆይ" በሚለው ጸሎት ውስጥ ከጠቀሳቸው ሰባት የመማጸኛ ጸሎቶች በመቀጠል እኛ ለወንድሞቻችን ይቅርታ ማደርግ እንደ ሚገባን አጽኖት ሰጥቶ “ እናንተ የበደሏችሁን ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ ደግሞ እናንተን ይቅር ይላችኋል። ነገር ግን የሰዎችን ኀጢአት ይቅር የማትሉ ከሆነ፣ አባታችሁም ኀጢአታችሁን ይቅር አይልላችሁም” (ማቴ 6፡14-15) በማለት የተናገረው በከንቱ አይደለም። እዚህ ላይ በእግዚአብሔር ፍቅር እና በባልንጀሮቻችን ፍቅር መካከል ያለውን ግንኙነት እናገኛለን። ፍቅር ፍቅርን ይጠራል፣ ይቅርታ ይቅርታን ያስገኛል። እንደገናም በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ በወንድማማችነት መንፈስ የተደረገውን ይቅርታ በተመለከተ እጅግ በጣም የሚደነቅ ምሳሌ እናገኛለን (ማቴ 18፡21-35 ወንድምን ይቅር ስለማለት)።

ምሳሌውም ይህንን ይመስል ነበር። ዐሥር ሺህ ታላንት ዕዳ ያለበትን አንድ አገልጋይ ወደ ንጉሡ ቀረበ! መልሶ ለመክፈል የማይችላ ዕዳ ነበር። በእዚያን ወቅት አንድ ተአምር ይፈጸማል፣ ያ አገልጋይ ዕዳውን ቀስ ብሎ እዲከፍል ሳይሆን የተደረገው ነገር ግን ዕዳው ሙሉ በሙሉ ተሰርዦ ሙሉ የሆነ ምሕረት ተደረገለት። ያልተጠበቀ ጸጋ። ነገር ግን ያ አገልጋይ ከጌታው ፊት እንደ ወጣ አንድ ሊከፈል የሚችል ብዙ ያልሆነ መቶ ዲናር  ብቻ የእርሱ ዕዳ ያለበትን አገልጋይ ባልንጀራውን ያቀረበለትን ተማጽኖ ችላ በማለት እንቅ አድርጎ ያዘው። በዚህ ምክንያት በመጨረሻ ላይ ጌታው ያንን አገልጋይ አስጠርቶት በእርሱ ላይ ይፈርድበታል። ምክንያቱም ይቅር ለማለት ካልሞከርክ ግን አንተም ይቅር አትባልም፣ ለመውደድ ካልሞከርክ አንተም አትወደድም።

ኢየሱስ የይቅር ባይነትን ኃይል በሰዎች ግንኙነት ውስጥ አስገብቷል። በሕይወት ሂደት ውስጥ ሁሉንም ነገር በፍትህ አጋባብ ብቻ መፍታት አይቻልም። በተለይ ለክፉ ነገር መሰናከሎች የተጋለጠ አንድ ሰው በጸጋ የተሞላ አዲስ የታሪክ ሂደት ለመጀመር ይበልጡኑ መውደድ ይኖርበታል። ክፋት የበቀል እርምጃውን ያውቃል፣ ይህ እርምጃ ካልተቋረጠ ደግሞ ዓለምን ይበክላል።

በእኔ ላይ የፈጸምከውን ነገር እኔም በአንተ ላይ እንዲሁ- የሚለውን የበቀል ሕግ- እግዚኣብሔር በእኔ ላይ ያደርገውን ነገር እኔም ለአንተ አደርጋለሁ በሚል የፍቅር ሕግ ኢየሱስ ተክቶታል።

እግዚአብሔር በተለይም ደግሞ በወንድሞቹ ሕይወት ውስጥ አስደሳች ያልሆነ እና የተሳሳተ ነገር የፈጸሙትን ሰዎች ሕይወት በአዲስ ምዕራፍ ይተካ ዘንድ ለክርስቲያኖች ጸጋውን ይሰጣል። በቃላት፣ በመተቃቀፍ፣ በፈገግታ አማካይነት የተቀበልነውን በጣም ውድ የሆነ የይቅርታ ጸጋ ለሌሎች ለመስጠት እንችላለን።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!

Photogallery

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ
24 April 2019, 15:41