ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ . በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ . በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ማርያም ከእግዚኣብሔር ጋር እንዴ መነጋገር እንደ ሚገባን ታስተምረናለች

የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በትላንትናው እለት ማለትም በታኅሳስ 03/2011 ዓ. የጓዳሎፔው እመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል። የጓዳሎፔው የእመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ የሚገኘው በሜክስኮ ከተማ ሰሜናዊ ክፍል ነው፡፡ ይህ ቤተመቅደስ የተሠራው ቴፔያክ ሂል በሚባለው ኮረብታ ሥር ነው፡፡ እመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም ለሁዋን ድየጎ የታየችውም በዚያው ኮረብታ ሥር ነበር፡፡ እመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም በጓዳሎፔ ለሁዋን ድየጎና ለአጎቱ ሁዋን ቤርናርዲኖ የተገለጸችው አምስት ጊዜ እንደ ነበረ የቤተመቅደሱ ታሪክ ያስረዳናል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ እመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም በጓዳሎፔ የተገለጸችው ለሁዋን ድየጎ ሲሆን እ.አ.አ. በታህሣሥ 9 ቀን 1531 ዓ.ም. ጧት በማለዳ ነበር፡፡ ይህም የተከሠተው ሕንዳዊው ካቶሊክ ሁዋን ዲየጎ ጥላተሎልኮ በሚባለው ስፍራ ወደሚገኘው ቤተክርስቲያን ለቅዳሴ ጸሎትና ትምህርተ ክርስቲያን ለመማር ሲሄድ ሳለ ነበር፡፡

ሁዋን ዲያጎ በኮረብታው ከፍተኛ ስፍራ ብሩህ ብርሃን ከማየቱም በላይ ወደ ኮረብታው ላይ ከፍ ብሎ እንዲወጣ የሚጋበዝ የሴት ድምፅ ሰማ፡፡ በኮረብታው ከፍተኛ ስፍራ ሲወጣም በሚደነቅ ሰማያዊ ብርሃን መካከል የቆመችውን ሴት አየ፡፡ ዘለዓለም ድንግል የሆነችው የእውነተኛው አምላክ እናት፣ እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም እንደ ሆነችም ነገረችው፡፡ እዚያም ለሰው ሁሉ እናታዊ ፍቅሯን፣ ርኀራኄዋንና ጥበቃዋን የምትገልጽበት ቤተመቅደስ በስሟ እንዲሠራ እንደምትፈልግም ነገረችው፡፡ እንዲህም አለችው፤ “እኔ መሐሪት እናትህ ነኝ፡፡ ይኸውም ላንተና እኔን ለሚወዱ፣ በእኔም ለሚተማመኑና አማላጅነቴን ለሚጠይቁ ለሰው ልጆች በሙሉ መሐሪት እናት ነኝ፡፡ ስለሆነም ወደ ሜክስኮ ከተማ አቡን ዘንድ ሄደህ እመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም ፍላጎትዋን እንድናገር ወደ እርስዎ ልካኛለች ብለህ ንገራቸው” አለችው፡፡ እመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም ለሁዋን ድየጎ ለሁለተኛ ጊዜ የተገለጸችው ለመጀመሪያ ጊዜ በተገለጸችበት በዚያው ቀን ማለትም እ.አ.አ. በታህሣሥ 9 ቀን 1531 ዓ.ም. ነበር፡፡ በየዓመቱ ከ18-20 ሚሊዮን መንፈሳውያን ተጓዦች የጓዳሎፔን እመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም ባዚሊካ ይጎበኛሉ፡፡ በዚህ ዐይነት የጓዳሎፔው እመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም ባዚሊካ በሁኑ ዘመን በመላው ዓለም ካሉት ብዙ ሰዎች ከሚጐበኙአቸው ታላላቅ የክርስቲያን ቤተመቅደሶች አንዱ ከመሆኑም ሌላ በዓለም ካሉት ትላልቅ መንፈሳዊ ጉዞ ከሚደረግባቸው ማዕከላትም አንዱ ነው (ዶ/ር አባ አንጦኒዮስ አልቤርቶ፡ 132)፡፡

ይህ የጓዳሎፔ የእሜቤታችን ቅድስት ማርያም አመታዊ በዓል በትላንትናው እለት ማለትም በታኅሳስ 03/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ከቅድስት ድንግል ማርያም ሕይወት ትህትናን እንማራለን ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 03/2011 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው አቅርበነዋል ተከታተሉን።

“ማርያምም እንዲህ አለች።  ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ደርጋለች፤  የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል” (ሉቃስ 1፡46-48)። የማርያም የውዳሴ መዝሙር የሚጀምረው በዚሁ መልኩ ነው፣ በዚህም ሁኔታ ማርያም የመጀመርያዋ “የቅድሱ ወንጌል ውዳሴ” አስተማሪ ለመሆን በቃች፣ እግዚኣብሔር ለአባቶቻችን የገባውን ቃል በማስታወስ የእግዚኣብሔርን መለኮታዊ ምሕረት በውዳሴ መልክ እንድናቀርብ ትጋብዘናለች።

ማርያም በተልዕኮ እና በተስፋ ጥበብ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ብዙ ቃላትን ወይም ፕሮግራሞችን ሳይሆኑ ነገር ግን እርሷ ያስተማረችን ዘዴ በጣም ቀላል የሚባል ዘዴ ነው፡ መጓዝ እና ውዳሴ ማቅረብ የሚሉት ናቸው።

 

መሄድ

መልኣኩ ገብርኤል ማርያምን ካበሰራት በኋላ እርሱ በፍጥነት ተነስታ ሄደች በማለት ቅዱስ ወንጌል ይናገራል። በፍጥነት ነገር ግን ያለምንም ጭንቀት ተነሳት በመራመድ ለመውለድ ወደ ተቃረበችው ወደ ኤልሳቤጥ ዘንድ ሄደች፣ በቃና ዘገሊላ ሰርግ ላይ የወይን ጠጅ ባለቀባቸው ጊዜ በፍጥነት ተነስታ ወደ ኢየሱስ ሄደች፣ በእድሜ የተነሳ ግራጫ የሆነ ጸጉሯን ቢሆንም ነገር ግን በፍጥነት ተነስታ በልጇ መስቀል ሥር ለመሆን ፈልጋ ወደ ጎልጎታ ሄደች፣ በዚያ በጨለማ እና በጭንቀት ወቅት እርሷ አልተደበቀችም፣ ልጇን ጥላ አልሄደችም፣ በዚያው በመስቀል ስር ለመቆየት ወደ እዚያው መሄድን መረጠች።

ሁዋን ዲየጎ ለመገናኘት በማሰብ ወደ ቴፔያክ ተራራ ሄዳለች፣ አሁንም ቢሆን እርማጃዋን ሳታቋርጥ በመላው በላቲን አሜርካ አህጉር በመጓዝ ቅዱስ በሆኑ ምስሎቿ አማካይነት ወይም በትንሼይ መዳሊያዋ አማካይነት፣ በአንድ ሻማ ላይ በተሳለ ምስሏ ወይም በእርሷ ስም በተሰራ መቁጠሪያ ወይም ለእርሷ በሚደረግ አንድ ጸጋ የሞላሽ ማርያም ሆይ በሚል ጸሎት አማካይነት ማርያም አሁንም ቢሆን በመራመድ ወደ ቤታችን፣ ወደ ማረምያ ቤቶች፣ ወደ ሆስፕታሎች፣ አረጋዊያን ወደ ሚኖሩባቸው ቤቶች፣ ወደ ትምህርት ቤቶች ወድ አንድ የሕክምና መስጫ ጣቢያ . . .ወዘተርፈ አሁንም ቢሆን ማርያም በመጓዝ ላይ ትገኛለች። “እኔ እናትህ  እዚህ አለሁልህ” ትለናለች። እርሷ እንደ እናት በመሆን ረጋ ብላ በመካከልችን ትመላለሳለች፣ በቤተሰብ ህይወት ውስጥ ትገኛለች፣ በህይወታችን ውስጥ ያሉትን በርካታ መከራዎች እንድቀሉን ታደርጋለች፣ በማዕበል ውስጥ ብንሆንም እንኳን ጸንተን እንድንቆም ታስተምረናላች።

ከማርያም መድረስ ወዳለብን ቦታ በጽናት መራመድ እንዳለብን እንማራለን። ከማርያም ወደ አከባቢያችን እና ወደ ከተማዎች በመጓዝ በዚያ ተስፋ የቆረጡ ሰዎችን፣ አቅም ያጡ ሰዎችን ለመጉብኘት መጓዝ እንዳለብን እንማራለን። ከማርያም ልባችንን በመላክ ነገሮች ለመሙላት ያስችለን ዘንድ መላክ የሆኑ ተግባሮችን ለማከናወን መጓዝ እንዳለብን እንረዳለን።

የውዳሴ መዝሙር

 “ማርያምም እንዲህ አለች።  ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤  የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና” በማለት ይህህን ታላቅ ነገር በሕይወቷ ያከናወነውን እግዚኣብሔር በመዝሙር እያወደሰች ሄደች። እርሷ መልካም እናት እንደ መሆኗ መጠን ለሌሎች እናቶችም ሳይቀር  ሕይወታቸውን በውዳሴ መዝሙር ሞልተው እንዲኖሩ ታስተምራለች። ለሌሎች እናቶችም ተስፋ ትሆናለች። ማርያም ኤልሳቤጥን በተገናኘችበት ወቅት በማህጸኗ ያለው ልጅ በደስታ ዘለለ፣ የሰላምታዋን ቃል በሰማች ወቅት ኤልሳቤጥ በደስታ ለእግዚኣብሔር የወዳሴ መዝሙር አቀረበች፣ ልጇን ኢየሱስን ወደ ቤተ መቅደስ በወሰዱበት ወቅት ስምዖን የተባለ የእድሜ ባለጸጋ ሰው ልጁን ባየው ጊዜ ትንቢት ተፈጸመ በማለት አገልጋይህን በሰላም አሰናብተው በማለት እግዚኣብሔርን በውዳሴ አመሰገነ።

የማርያም የሕይወት ስኬት ምንጭ የሆነው ለእግዚኣብሔር ጥሪ “እነሆኝ እንዳልከኝ ይሁንልኝ” በማለቱ ኣየገኘችው የሕይወት ስኬት ሲሆን እኛም ይህንን ለእርሷ ሕይወት እንማራለን። ብርታት እንዲኖረን ታስተምረናለች፣ ከእግዚኣብሔር ጋር እንዴ መነጋገር እንደ ሚገባን ታስተምረናለች፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ማንም ሰው የማይደፍረውን ነገር በታልቅ እምነት እና ተስፋ መቀበል እንዳለብን ታስተምረናለች።

ከማርያም ሕይወት ትሁት የመሆን አስፈላጊነትን እንማራለን፣ ከማርያም ሕይወት እኛ ትልቅ የምንባል ሰዎች ብንሆንም ራሳችንን ዝቅ አድርገን መመልከት እንደ ሚገባን እንማራለን። ከማርያም ሕይወት እውነተኛ ሰዎች ሆነን መኖር እንደ ሚገባን እናማራለን። ከማርያም ሕይወት ያገኘነውን ደስታ ከሰዎች ጋር መቋደስ እንደ ሚገባን እንማራለን። ከማርያም ሕይወት የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ እንዴት መሆን እንደ ምንችል እንማራለን። ከማርያም ሕይወት የእግዚኣብሔርን ቃል እንዴት መስማት እንደ ሚኖርብን፣ ከሰማን በኋላ ደግሞ እንዴት በተግባር ላይ ማዋል እንደ ሚኖርብን እንማራለን።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
12 December 2018, 16:01