ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ማርያም የእምነት እና የበጎ ሥራ አብነት ናት” አሉ።

በመሠረቱ ማሪያም አማና ስለተቀበለች የተባረከች ነች፣ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት መቻል የእምነት ፍሬ ነው። ዘካሪያስ ግን ባለማመኑ እና በመጠራጠሩ የተነሳ ዲዳ እና መስማት የተሳነው እንዲሆን ተደረገ

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!
በዚህ በአራተኛው የስብከተ ገና ሳምንት ሰንበት ስርዓተ አምልኮ የሚያተኩረው ማርያም፣ ድንግል የሆነች እናት፣ የዓለም አዳኝ የሆነውን ኢየሱስን ለመውለድ በመጠባበቅ ላይ እንደ ሆነች ይገልጻል። እይታችንን የፍቅር እና የእመነት ተምሳሌት በሆነችው በእርሷ ላይ በማድረግ በእነዚህ ለመውለድ በቀሩዋት ጥቂት ወራት ውስጥ እርሷ ምን ታስብ እንደ ነበረች ጥያቄ ማንሳት ይገባል። የዚህ ጥያቄ ምላሽ ደግሞ ዛሬ በተነበበልን ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰውና ማርያም የእድሜ ባለጸጋ የሆነችውን ዘመዷን ኤልሳቤጥን ለመጎብኘት መሄዱዋን በሚገልጸው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ውስጥ እናገኛለን (ሉቃስ 1፡39-45)። መልኣኩ ገብርኤል ለማርያም ዘመዷ የሆነችው ኤልሳቤጥ ማርገዟንና እነሆ ካረገዘች 6ኛ ወሯ እንደ ሆነ ገልጾላት ነበር (ሉቃስ 1፡26.36)። ከዚያም ኢየሱስን በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ አማካይነት የጸነሰቺው ድንግል፣ በናዝሬት አቅራቢያ ከሚገኘው የገሊላ መንደር በፍጥነት ተነስታ በይሁዳ ተራሮች አከባቢ ወደ ሚገኘው የአክስቷ ቤት ታቀናለች።
“ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ማርያም ለኤልሳቤጥ ሰላምታን አቀረበች” (ሉቃስ 1፡40) በማለት ቅዱስ ወንጌል ይናገራል። በእርግጠኛነት ማርያም ኤልሳቤጥ በማርገዟ በጣም ተደስታ ነበር፣ በተመሳሳይ መልኩም ኤልሳቤጥ በማርያም ማርገዝ ተደስታ “በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው! የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? (ሉቃስ 1፡42-32) በማለት ትናገራለች። ከዚያም በፍጥነት “አንቺ እግዚኣብሔር የተናግረውን ሁሉ የሚፈጽም መሆኑን በማመንሽ ምንኛ የታደልሽ ነሽ” (ሉቃስ 1፡45) በማለት ማርያምን ታወድሳለች።
እርግጥ ነው እምነት በነበራት በማርያም እና ጥርጣሬ በነበረው፣ መልአኩ የሰጠውን የተስፋውን ቃል ያላመነው፣ በዚህም ምክንያት ዮሐንስ እስኪወለድ ድረስ ዲዳ እንዲሆን በተደረገው፣ የኤልሳቤጥ ባል በነበረው በዘካሪያ እና በማርያም መካከል ትልቅ ልዩነት አለ።
ይህ የትዕይንት አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘቱን ምሥጢራዊ በሆነ ልዩ ብርሃን ለማንበብ ይረዳናል። ይህ ግንኙነት በጣም ድንቅ በሚባሉ ተዐምራት ያልተሞላ፣ ነገር ግን በእምነት እና በፍቅር የተሞላ መሆኑን እንማራለን። በመሠረቱ ማሪያም አማና ስለተቀበለች የተባረከች ነች፣ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት መቻል የእምነት ፍሬ ነው። ዘካሪያስ ግን ባለማመኑ እና በመጠራጠሩ የተነሳ ዲዳ እና መስማት የተሳነው እንዲሆን ተደረገ። ረጅም የሆነ ጸጥታ ውስጥ በመሆን በእመንት ለማደግ ይችላል፣ ያለ እምነት ደግሞ አንድ ሰው የእግዚአብሔርን አጽናኝ የሆነ ድምጽ መስማት አይችልም፣ እኛም ለወንድሞቻችን የሚሆን የመጽናኛ እና የተስፋ መልእክቶችን መናገር አንችልም። ይህንን ደግሞ በእየቀኑ የምናየው እውነታ ነው፣ እምነት የሌላቸው ወይም በጣም ትንሽ እምነት ያላቸው ሰዎች ወደ አንድ ሰው ቀርበው ስለ አንዳንድ ሁኔታዎች ይነግሯቸዋል፣ ነገር ግን እነዚያ ቃላት ጥንካሬ ስለሌላቸው ልብን መንካት አይችሉም። እመነት ስለሌለው ቃላቶቹ ኃይል የላቸውም፣ እመነት ከሌለ ደግሞ ልብን ዘልቆ የሚገባ ቃላትን ለሌሎች መናገር አይችልም። እመንት የሚበለጽገው ደግሞ በጎ የሆኑ የፍቅር ሥራዎችን በማከናወን ነው። ወንጌላዊው እንደ ሚተርከው “ማርያም በፍጥነት ተነስታ ወደ ኤልሳቤጥ ሄደች” (ሉቃስ 1፡39) በማለት ይናገራል፣ በፍጥነት ያለምንም ጭንቀት፣ ነገር ግን በፍጥነት፣ በሰላም ሄደች ይለናል። "ተነስታ" የሚለው ቃል በጣም አሳሳቢ የሆነ አካላዊ መግለጫ ነው። የወደፊቱ ልጇን ለመውለድ ለመዘጋጀት ቤቷ ውስጥ መቆየት ትችል ነበር፣ ነገር ግን ከእርሷ ከራሷ ይልቅ ለሌላ ማሰብን ፈለገች፣ በሆዷ ውስጥ የተሸከመችው ወይም የያዘቺው ጌታ ደቀ-መዝሙር መሆኑና አስቀድማ በተግባር ገለጸች። ኢየሱስ የተወለደበት ሁኔታ የሚጀምረው ቀለል ባለ የበጎ አድራጊነት ስሜት ተነሳስቶ ነው፣ በተጨማሪም እውነተኛ ልግስና ሁልጊዜ የእግዚአብሔር ፍቅር መገለጫ ፍሬ መሆኑን ያሳየናል።
በዛሬው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ የተነበበውና ማርያም ኤልሳቤጥን ለመጉብኘት መሄዷን የሚገልጸው ቅዱስ ወንጌል የገናን በዓል በሚገባ ማክበር እንችል ዘንድ በማድረግ መልካም የሆነ እምነት ልቦና እንድኖረን እኛን በማዘጋጀት መልካም የሆኑ የበጎ አድራጎት ተግባራትን እንድንፈጽም ያጠነክረናል ያነሳሳናልም። ይህ ጥንካሬ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው፣ የማርያምን ድንግል የሆነ ማህፀን ፍሬያማ እንዲሆን ያደረገው እና አረጋዊት የነበረችውን ዘመዷን ለማገልገል በፍጥነት እንድትሄድ ያነሳሳት የፍቅር መንፈስ ነው። ልክ በሁለቱ እናቶች መካከል በተደረገው ግንኙነት ወቅት እንደምናየው እና በእርሱ የሚታመኑ ትናንሽ የሚባሉ ሰዎች በጌታ አማካይነት የምያገኙትን ታላቅ ደስታ እንመለከታለን።
ድንግል የሆነቺው እመቤታችን ቅድስት ማርያም የገናን በዓል ራሳችንን መአከል ባደረገ መልኩ ሳይሆን “እኔ” ከማለት ይልቅ “አንተ” በማለት ኢየሱስን ማዕከል በማድረግ እና አሁንም “አናንተ” በማለት ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን የሕይወታችን ማዕከላ በማድረግ የተቻለንን የበጎ አድራጎት ተግባር ማከናወን እንችል ዘንድ ጸጋውን እንድታሰጠን ልንማጸናት ይገባል። በመጨረሻም ሥጋ ለብሶ ሰው በመሆን በመካከላችን ማደር ለፈለገው ለእግዚኣብሔር ልጅ በሕይወታችን እና በልባችን ውስጥ እንዲወለድ ቦታ ልናዘጋጅለት ይገባል።

 


 

23 December 2018, 16:13