ፈልግ

በጄኖቫ ድልድይ ተደርምሶ በደረሰው አደጋ ሰለባ የሆኑ ሰዎች ነፍስ ለእግዚኣብሔር በአደራ እንሰጣለን

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በነሐሴ 09/2010 ዓ.ም ከገብርኤል ብስራት ጸሎት በኋላ ያስተላለፉት መልእክት

የአውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የፍልሰታ ማሪያም አመታዊ በዓል በዛሬው እለት ማለትም በነሐሴ 09/2010 ዓ.ም  በታላቅ መንፈሳዊነት ተከብሮ ማለፉን ቀደስም ሲል መገለጻችን የሚታወስ ሲሆን ይህ የፍለሰት ማሪያም አመታዊ በዓለ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእርሳቸው መሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ማለፉን መግለጻችን ይታወሳል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው ካሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ በመቀጠል ዘወትር በታላላቅ መንፈሳዊ በዓላት እና በእለተ ሰንበት እኩለ ቀን ላይ ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከሚደግሙት በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ከሚቀርቡ የመማጸኛ ጸሎቶች መካከል አንዱ የሆነውን “የእግዚኣብሔር መልኣክ ማሪያምን አበሰራት” የሚለውን የመልኣከ ገብርኤል ጸሎት ከደገሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ በተለያዩ ዓይነት መከራዎች እና ችግሮች ውስጥ ገብተው የምሰቃዩ ሰዎችን በተጨማሪም የአካል እና የመንፈስ ስቃይ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በሙሉ ዛሬ በመንግሥተ ሰማይ ሆና ለእኛ ለምትማልደው እና የሐዘንተኞች አጽናኝ ለሆነቺው ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስቃያቸውን እና መከራዎቻቸውን ሁሉ በአደራ እንሰጣለን ብለዋል። ሰማይዊ እናታችን ለሁሉም የሰው ልጆች ምቾት፣ ብርታትና እርጋታ ከልጇ ዘንድ ታሰጥ ዘንድ እንማጸናታለን ብለዋል።

በተላንታንው እለት በጣሊያን ጄኖቫ በሚባልበት ሥፍራ አንድ ድልድይ ተደርምሶ በደረሰው አደጋ በአሰቃቂ ሁኔታ ነፍሳቸውን ላጡ እና በአካላቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች በጸሎታቸው እንደ ሚያስቡ የገለጹት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ በአደጋው ነብሳቸውን ያጡ ሰዎችን እግዚኣብሔር ነብሳቸውን በምሕረቱ እንዲቀበል የተማጸኑት ቅዱስነታቸው ከእዚያም በመቀጠል የአካል ጉዳት ለደርሰባቸው ሰዎች በቶሎ እዲያገግሙ፣ በአጠቃላይ በዚህ አደጋ የተነሳ ከፍተኛ ለሆነ ሐዘን የተጋለጡ ሰዎችን በሙሉ በመንፈስ ከእነርሱ ጋር እንደ ሚሆኑ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

15 August 2018, 17:51