ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ ምስጢረ ተክሊል መፈጸም ከባድ የሆነ ጉዳይ ቢሆንም ነገር ግን ዋጋ አለው!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በአየርላንድ ዋና ከተማ በደብሊን በአሁኑ ወቅት እያደርጉ የሚገኙትን 24ኛውን ዓለማቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝ በመቀጠል በአየርላንድ ከሚገኙ የምንግሥት ባለስልጣናት እና የሲቪክ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በአጠቃላይ 250 ያህል ተጋብዥ እንግዶች በተገኙበት የዚህን 24ኛ ሐዋርያዊ ጉብኝት የመጀመርያ ኦፊሴላዊ ንግግር ካደረጉ በኋላ በደብሊን የሚገኘውን በጥንታዊነቱ የሚታወቀውን እና በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም የሚጠራውን ካቴድራል ለመጎብኘት ወደ እዚያው ማቅናታቸው እና በዚያ ስፍራ እርሳቸውን ለሚጠባበቁ ምዕመናን ቅዱስነታቸው የዚህን 24ኛው ዓለማቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት ሁለተኛውን ኦፊሴላያዊ ንግግር አድረገዋል። ይህንን የቅዱስነታቸውን ንግግር በአጭሩ እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በደብሊን በሚገኘው ጥንታዊ በሆነው እና በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በሚጠራው ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው በዚያ እርሳቸውን በመጠባበቅ  ላይ ለነበሩ ምዕመናን ቅዱስነታቸው ንግግር ማድረጋቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደርጉት ንግግር እንደ ገለጹት “የተከበራችሁ ወዳጆቼ በዚህ በማርያም ስም በሚጠራው ታሪካዊ ካቴድራል ውስጥ እናንተን በማግኘቴ የተሰማኝን ልባዊ ደስታ ለመግለጽ እወዳለሁ” በማለት ንግግራቸውን መጀመራቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዚህ ካቴድራል ውስጥ ለዘመናት ምስጢረ ተክሊል የሚሰጥበት ታሪካዊ የሆነ ካቴድራል እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

በዚህ ካቴድራል ውስጥ ብዙ የፍቅር ጸጋዎች የተገኙበት፣ በዚህ ካቴድራል ውስጥ ምስጢረ ተክሊል ያሰሩ ሰዎች ብዙ ጸጋን በመቀበላቸው የተነሳ ምስጋና ለእግዚኣብሔር የሚያቀርቡበት በመሆኑ የተነሳ ለዚህ ቅዱስ ስፍራ ያላቸውን አክብሮ ብዙ ምዕመናን እየገልጹ እንደ ሚገኙ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

የደብሊን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብጹዕ ጳጳስ ማርቲን ደማቅ አቀባበል ስላደርጉልኝ ላመስግናቸው እወዳለሁ በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱነታቸው በዚህ በተቀደሰ ስፍራ ላይ ለተገኛችሁት ለበርካታ አመታት ያህል በምስጢረ ተክሊል ሕይወት ውስጥ የቆያችሁት እና እንዲሁም ምስጢረ ተክሊል ለመፈጸም በመዘጋጀት ላይ ከምትገኙ ምዕመናን ጋር በዚህ ቅዱስ በሆነ ሥፍራ ለመገናኘት በመብቃቴ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል።

በወቅቱ ቅዱስነታቸው ንግግር ከማድረጋቸው በፊት ቪንሰንት እና ትሬዛ የሚባሉ ሁለት ምዕመናን ለሃምሳ አመታት ያህል በምስጢረ ተክሊል ሕይወት ውስጥ የቆዩ ምዕመናን ስለ የሃምሳ አመት የምስጢረ ተክሊል ጉዞዋቸው በተመለከተ ምስክርነት ሰጥተው እንደ ነበረ በማስታወስ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ለሰጡት ቪንሰንት እና ትሬዛ ስለሰጡት ምስክርነት ቅዱስነታቸው አመስግነው በእነዚህ 5ኦ አመታት ውስጥ ለተቀበሉት ጸጋ እግዚኣብሔርን አመስግነው፣ በተጨማሪም በእነዚህ 50 አመታት ውስጥ በምስጢረ ተክሊል ሕይወት ውስጥ በቆዩባቸው ረጅም ጊዜያት የገጠማቸውን ተግዳሮቶች እና እነዚህን ተግዳሮት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያሳዩትን ቁርጠኝነት ቅዱስነታቸው እንደ ሚያደንቁ ገልጸዋል።

ሁል ጊዜም ቢሆን የአረጋዊያንን እና የአያቶቻችንን ምስክርነት ማዳመጥ በጣም አስፈላጊ እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም ከአረጋዊያን እና ከአያቶቻችን ታሪክ በጣም ብዙ የምንማራቸው ነገሮች በመኖራቸው የተነሳ መሆኑ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው አረጋዊያን በተለይም ደግሞ በምስጢረ ተክሊል ሕይወት ውስጥ የኖሩ አረጋዊያን በሕይወታቸው ጉዞ ያገኙትን ከፍተኛ ደስታ እና በሕይወታቸው ውስጥ የገጠማቸውን ተግዳሮቶች ለእኛ በማስተላለፍ ከሕይወታቸው እንድንማር ከፍተኛ አስተዋጾ ስለምያደርጉ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በስፍራው የተገኙ አንዳንድ ወጣት ምስጢረ ተክሊል ለመፈጸም የተዘጋጁ ወጣቶች ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጹሁፍ አንዳንድ ጥያቄዎችን ማቅረባቸውን ከስፍራው ከደረሰን ዜና ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ወቅት እነዚህን ጥያቄዎች በተመለከተ በሰጡት ምላሽ እንደ ገለጹት የቀረበላቸው ጥያቄ በአጠቃላይ ሲታይ ለመመለስ አስቸጋሪ የሆነ ጥያቄ ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን “ምስጢረ ተክሊል መፈጸም ማለት እንዲሁ በአንድ ጀልባ ላይ ተሳፍሮ መሄድ ማለት እንዳልሆነ” ቅዱስነታቸው በአጽኖት ገለጸዋል። ምስጢረ ተክሊል መፈጸም ማለት እግዚኣብሔር በሚፈልገው መልኩ መኖር ማለት እንደ ሆነ፣ እስከ ሕይወት ፍጻሜ ድረስ በዕየለቱ ጥረት የሚጠይቅ፣ እስከ መጨረሻው እርስ በእርስ በመደጋገፍ፣ በመረዳዳት፣ አንዱ ለሌላው ትኩረት በመስጠት እስከ መጨረሻው ድረስ መኖር የሚገባው የሕይወት ጥሪ መሆኑን ቅዱነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በእርግጥ ዛሬ በምንኖርበት ዓለማችን አለመታደል ሆኖ ከስከ ሕይወት ፋጻሜ የሚቆዩትን እውነተኛ የሆኑ ነገሮችን የመፈለግ ስሜት በክፍተኛ ደረጃ እየጠፋ፣ በአንጻሩ ጊዜያዊ የሆኑ ነገሮችን ብቻ መጠቀም እየተለማመድን መጥተናል ያሉት ቅዱስነታቸው ለምሳሌም ከራበኝ እና ከጠማኝ ረሃቤን እና ጥማቴን በቶሎ ለማስታገስ እችላልሁ፣ ነገር ግን ያ ጥጋብ ቢበዛ ከአንድ ቀን በላይ አይቆይም፣ እንደ ገና ካልበላን እና ካልጠጣን ተመልሰን እንራባለን ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንን እና ይህንን የመሳሰሉ በጣም ብዙ የሚባሉ ክስተቶች በዓለማችን ላይ እየተከሰቱ ስለሚገኙ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ በሚገኘው ዓለማችን “በጣም አስፈላጊ እና ውድ የሆነ እስከ መጨረሻው ጊዜ ድረስ መቆየት የሚችል ምንም ነገር የለም ወይ? ፍቅር እስከ መጨረሻ መቆየት አይችልም ወይ?” በማለት ቅዱስነታቸው ጥያቄ ማንሳታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል። ዛሬ የምንኖርበት ዓለማችን በብዙ ነገሮች ተተብትበን የብዙ ባህሎች ባርያ ሆነን እንገኛለን ያሉት ቅዱስነታቸው በዚህ ባሕል ውስጥ ተወልደው ያደጉ ወጣቶች ብያንስ ብያንስ ከወላጆቻቸው የወረሱትን ባሕል ተጠቅመው ሁሉም ነገር ጊዜያዊ በሆነው ዓለማችን ውስጥ “ዘላቂ የሆነ ፍቅር እንዲኖር” መሥራት እና መጠበቅ ይኖርብናል ብለዋል።

“ፍቅር ለእኛ እና ለጠቅላላው ሰብአዊ ቤተሰብ እግዚአብሄር ያለመልን ህልም እንደሆነ እናውቃለን” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “እባካችሁን ይህንን በፍጹም እንዳትረሱ ‘እግዚኣብሔር ለእያንዳንዳችን ሕልም አለው’ ይህንን ሕልም እያንዳንዳችሁ እውን ማድረግ በፍጹም እንዳትረሱ” ብለዋል።

“በጋራ ለቤተሰብ መጸለይ ይገባል፣ መልካም እና ጤነኛ የሆኑ ነገሮችን ብቻ ለማውራት ሞክሩ” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እናታችን የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተሰብ ሕይወት ውስጥ ዘልቃ እንድተገባ መፍቀድ የገባል በተለይም ደግሞ በማኅበርሰባችን ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ተገለው የሚገኙትን ቤተሰቦች በጸሎት ማሰብ ይገባል ብለዋል።

“ከእኔ እና ከዓለም ዙርያ የተሰበሰቡ የቤተሰብ ተወካዮች በሚገኙበት፣ ምስጢረ ተክሊል የተቀበሉ አረጋዊያን እና ወጣት ባለትዳሮች፣ እንዲሁም ምስጢረ ተክሊልን ለመቀበል በመዘጋጀት ላይ የሚገኙ ወጣቶች በተገኙበት  በዛሬው ምሽት ለቤተሰብ ጸሎት በማድረግ እግዚኣብሔር የእምነትን ስጦታ ስለሰጠን እና ክርስትያንዊ ቤተሰብ የሚመሰረትበትን ምስጢረ ተክሊል የሰጠንን እግዚኣብሔር በጋር ማመስገን ይገባናል” ያሉት ቅዱነታቸው የእግዚኣብሔር የቅድስና፣ የፍትህ፣ የሰላም፣ እና የተማኘነት መንግሥት በምድር ላይ ይሰፍን ዘንድ የበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይኖርብናል ካሉ በኋላ በተለይም ደግሞ በፍቅር ጸንተን መኖር እድንችል እንዲረዳን መጸለይ ያስፈልጋል ካሉ በኋላ እዚህ ለተገኛችሁ ለሁላችሁም፣ ለቤተስቦቻችሁ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ በሙሉ ሐዋርያዊ ቡራኬዬ ይደርሳችሁ ካሉ በኋላ ቅዱነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!

Photogallery

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ በደብሊን የሚገኘውን የቅድስት ድንግል ማርያም ጥንታዊ ካቴድራል በጎበኙበት ወቅት
25 August 2018, 10:52