ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በደብሊን የሚያደጉትን 24ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በይፋ ጀመሩ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በትላንትናው ምሽት ይህ 24ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት በተሰካ እና ፍሬያማ በሆነ ሁኔታ ይጠናቀቅ ዘንድ በሳንታ ማሪያ ማጆሬ ባዚሊካ ተገኝተው ጸሎት ካደርሱ በኋላ በነሐሴ 19/2010 ዓ.ም በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 03:15 ላይ በሮም ከተማ ከሚገኘው እና በ15ኛው ክፍለ ዘመን በኖረው የጌታን የመጨረሻ እራት እና ሞናሊዛን በመሳሰሉ ድንቅ በሆኑ ስዕሎቹ በሚታወቀው በሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ ስም ከተሰየመው ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማርፊያ በመነሳት ጉዞዋቸውን ጀምረው 1,890 ኪሎ ሜትሮችን በአየር ላይ አቋርጠው የ3፡15 ደቂቃ ጉዞ ካደረጉ በኋላ በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከረፋዱ 6፡30 ላይ ደብሊን ዓለማቀፍ የአውሮፓላን ማረፊያ ጣቢያ መደረሳቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዱስነታቸው የአየርላንድ ዋና ከተማ ወደ ሆነችው ወደ ደብሊን 24ኛውን ዓለማቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ማለትም በነሐሴ 19/2010 ዓ.ም ወደ ደብሊን በአውሮፕላን ባቀኑበት ወቅት የአውሮፕላን የአየር የበረራ ክልሎቻቸውን ላቋረጡባቸው የሲውዘርላንድ፣ የፈረንሳይ እና የእንግሊዝ ሀገር ርዕሰ ብሔር ለሆኑት እንደ ተለመደው በተሌግራም መልእክት ማስተላለፋቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በቴለግራም ባስተላለፉት መልእክት የአውሮፕላን የበረራ የአየር ክልላቸውን ላቋረጡባቸው ለሲውዘርላድ፣ ለፈረንሳይ እና ለእንግሊዝ ሀገር መሪዎች እና ለሕዝቦቻቸው ሰላም እና ብልጽግናን መመኘታቸን ለመረዳት ተችሉዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በአየርላንድ ዋና ከተማ በደብሊን የሚያደርጉትን 24ኛውን ዓለማቀፍ ሐዋሪያዊ ጉብኝት ዛሬ ማለትም በነሐሴ 19/2010 ዓ.ም ጥዋት መጀመራቸውን እና በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከረፋዱ 6፡30 ላይ ዳብሊን ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ መድረሳቸውን ቀደም ሲል መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ቅዱስነታቸው በዚያው ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል።

በደብሊን ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማርፊያ ጣቢያ ተገኝተው ለቅዱስነታቸው አቀባበል ካደርጉ ግለሰቦች መካከል የሀገሪቷ ምክትል ጠቅላይ ሚንስቴር በስፍራው ተገኝተው ለቅዱስነታቸው ደማቅ አቀባበል ማድረጋቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን የሀገሪቷ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጽዕን ጳጳሳትን ጨምሮ በርካ ግለሰቦች ለቅዱስነታቸው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

25 August 2018, 16:45