ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  (AFP or licensors)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የክርስትና አባት እና እናት ልጆቻቸው የእምነት ጎዳናን ተከትለው ያድጉ ዘንድ ማገዝ ይኖርባቸዋል”

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በግንቦት 08/2010 ዓ.ም. ባደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስስ አስተምህሮ እንደ ገለጹት “የክርስትና አባት እና እናት ልጆቻቸው የእምነት ጎዳናን ተከትለው ያድጉ ዘንድ ማገዝ ይኖርባቸዋል” ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ወይም ደግሞ እዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የእዚሁ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው በሚያዝያ 03/2010 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ ትኩረቱን ባደረገው የክፍል አንድ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ “ምስጢረ ጥመቀት የክርስትና ሕይውት መሰረት ነው” ማለታቸውን መገለጻችን ይታወሳል። በሚያዝያ 10/2010 ዓ.ም. አሁንም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ባደርጉት የክፍል ሁለት አስተምህሮ “ምስጢረ ጥምቀት የክርስትና እምነት ምልክት ነው” ማለታቸውን መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን በሚያዝያ 18/2010 ዓ.ም. አሁንም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ባደርጉት ክፍል ሦስት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ምስጢረ ጥምቀት “ክፉ መንፈስን የማሸንፊያ መሳሪያ ነው” ማለታቸውን ቀደም ባሉት ዝግጅቶቻችን መዘገባችን ይታወሳል። በሚያዝያ 24/2010 ዓ.ም. አሁንም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ባደረጉት ክፍል አራት የትምህርተ ክርስትሶስ አሰትምህሮ እንደ አገለጹት “አንድ ሰው ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ክርስቶስን መከተል በፍጹም አይችልም” ማለታቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በግንቦት 01/2010 ዓ.ም. ደግሞ አሁንም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ መሰረቱን ባደርገው የክፍል አምስት አስተምህሮ እንደ ገለጹት “ምስጢረ ጥምቀት ዳግም እንድንወለድ ያደረግናል” ማለታቸው መዘገባችን ያትወሳል።

በዛሬው እለት ማለትም በግንቦት 08/2010 ዓ.ም አሁን በምስጢረ ጥመቀት ዙሪያ ላይ ባድርጉት የክፍል ስድስት አስተምህሮ እና በእዚህ በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ ላልፉት አምስት ሳምንታት ስያደርጉት የነበረው አስተምህሮ ማብቂያ ላይ እንደ ገለጹት “የክርስትና እናት እና የክርስትና አባት” ልጆቻቸው የእምነት ጎዳናን ተከትለው ያድጉ ዘንድ ልያስተምሩዋቸው እና ሊረዱዋችው የገባል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 08/2010 ዓ.ም.  በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ አድርገውት የነበረውን የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

“የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!”

“ ከእዚህ ቀደም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ስናደርግው የቆየነውን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በዛሬው እለት ይጠናቀቃል። ይህ ምስጢረ ጥምቀት የሚሰጠን መንፍሳዊ ጸጋ በዓይናችን የሚታይ ነገር ባይሆንም ነገር ግን ይህ በጥምቀት አዲስ ፍጡር የሆኑ ሰዎች በጥምቀታቸው ወቅት ነጭ ልብስ እና የበራ ሻም በተሰጣቸው ሰዎች ልብ ውስጥ የሚሰራ መስጢር ነው። በጥምቀት ውሃ የታጠቡ እና አዲስ ፍጥረት የሆኑት ሁሉ እውነተኛ በሆነው ጽድቅ እንዲሁም ቅድስና እግዚአብሔርን እንዲመስል ተጠርተዋል (ኤፌሶን 4፡24)፣ ከመጀመሪያዎቹ ዘመናት አንስቶ ንዑሰ ክርስቲያን የሚያንጸባርቅ አዲስ ልብስ ይለብሱ እደነበረ የሚታወቅ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ ደግሞ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እና ለመንፈስ ቅዱስ ተገዢዎች መሆናቸውን ያሳያል። ይህ ነጭ ልብስ በምሳሌያዊ አገላለጽ በእዚህ ምስጢር አማካይነት የተከሰተውን ነገር የሚገልጽ ሲሆን ይህም ወደ መልኮታዊ ክብር መቀየራችንን ያስታውሳል። ክርስቶስን መልበስ በተመለከተ ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ሲናግር ምስጢረ ጥምቀትን የተቀበሉ ሰዎች ሁሉ የተቀበሉትን ጸጋ መንከባከብ እንደ ሚኖርባቸው ሲያስረዳ “እንግዲህ የተቀደሳችሁና የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ምርጦች እንደመሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ጨዋነትንና ትዕግሥትን ልበሱ፤ 13እርስ በርሳችሁ ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ጌታ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ሌላውን ይቅር በሉ። 14በእነዚህ ሁሉ ላይ ሁሉን በፍጹም አንድነት የሚያስተሳስረውን ፍቅርን ልበሱት” (ቆላሲያስ 3፡12-14) በማለት ይናገራል። በምስጢረ ጥምቀት ስነ-ስረዓት ወቅት የሚሰጠው ነጭ ሻማ ከፋሲካ ሻማ የሚወጣውን የእሳት ነበልባል ያመለክታል፣ ይህም የምስጢረ ጥምቀት ውጤታማነትን የሚያሳይ ሲሆን “የክርስቶስን ብርሃን ልበሱ” በማለት ካህኑ በሚናገርበት ወቅት ያስታውሰናል። እነዚህ ቃላት ብርሃን የሆነው እኛ ሳንሆን ብርሃን የሚሰጠን ከሙታን የተነሳው እና ጨለማን ድል ያደርገውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ሆነ ያሳየናል። እኛም ይህንን ድንቅ የሆነ ብርሃን እንድንቀበል ተጠርተናል፣ በፋሲካ ወቅት የሚብራው ሻማ ለእያንዳንዱ ሻማ ብርሃን እንደ ሚሰጥ በእዚህም መልኩ ከሙታን የተነሳው ጌታ ምስጢረ ጥምቀትን በተቀበሉ ሰዎች ልብ ወስጥ ይንበለበላል፣ ብርሃን እና ኃይል ይሰጣቸዋል። በእዚህም ምክንያት ነው እንግዲህ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ምስጢረት ጥምቀት “የብርሃን ጥምቀት” እየተባለ የሚጠራው በእዚህ ምክንያት ነው፣ ምስጢረ ጥምቀትን የተቀበለ ሰው ደግሞ ብርሃን የተሞላ ሰው ነው የሚባለውም በእዚሁ ምክንያት ነው። በእውነትም የአንድ ክርስቲያን ሕይወት ተግባር ሊሆን የሚገባው “ሁልጊዜ እንደ ብርሃን ልጆች ሆነው መጓዝ እና በእምነት ጸንተው መኖር ነው”። ምስጢረ ጥምቀትን የተቀበለው ሕጻን ልጅ ከሆነ ደግሞ ይህ ጉዞ ተግባራዊ የሚሆነው በወላጆቹ እና እንዲሁም በክርስትና አባት ወይም እናት አማይነት ሲሆን ምስጢረ ጥምቀትን በተቀበሉ ሕጻናት ውስጥ ያለውን ብርሃን በመንከባከብ ሕጻናቱ በእመንት ጠንክረው ወደ ፊት በብርታት እንዲጓዙ ማድረግ ይገባል። “ልጆች የክርስትና ትምህርት የማግኘት መብት አላቸው”። ይህም ሕጻናት ቀስ በቀስ እግዚኣብሔር በክርስቶስ አማካይነት ያቀደውን የደኽንነት እቅድ እንዲከተሉ በማድረግ በተጠመቁበት ወቅት የተቀበሉት እመነት ጠብቀው እንዲያድጉ ያደርጋል። ለክርስቶስ መኖራችንን፣ ለመጠበቅ፣ ለመከላከልና፣ ለማስፋፋት የእኛን መንገድ የሚያበራ መብራት፣ ምርጫዎቻችንን የሚቀይር ብርሀን፣ ጌታን ለመገናኘት ልባችንን የሚያሞቅ ነበልባል፣ ከእኛ ጋር ተመሳሳይ መነገድ ላይ በመጓዝ ላይ የሚገኙ ሰዎችን በመመልከት መርዳት እንድንችል የሚያደርገን እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ ከእርሱ ጋር ኅብረት ፈጥረን እንድንቀጥል የሚይደርግን ብርሃን ነው። በእዚያን ጊዜ ይለናል የዩሐንስ ራይ መጽሐፍ “ከእንግዲህ ወዲህ ሌሊት አይኖርም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሓይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ” (ራይ 22፡5) ይሆናል። የምስጥረ ጥምቀት አሰጣጥ ስነ-ስረዓት የእግዚኣብሔር ማኅበረሰብ የሆኑት የእግዚኣብሔር ልጆች በሚደግሙት “አባታችን ሆይ የሚለው ጸሎት” ከተጸለየ በኃላ ይደመደማል። በእርግጥ በምስጢረ ጥምቀት አማካይነት እንደ ገና የተወለዱ ሕጻናት መንፈስ ቅዱስን በምልኣት የሚቀበሉት ምስጢረ ሜሮን በሚቀበሉበት ቀን እና የጌታ እራት ተካፋዮች በሚሆኑበት እለት እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን በእግዚኣብሔር በመተማመን “አባታችን ሆይ” የሚለውን ትርጉም በደንብ በሚረዱበት ወቅት ይሆናል። በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ እያደርግነው የምንገኘውን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በምናጠናቅቅበት በዛሬው እለት እያንዳንዳችሁ በቅርቡ ለንባብ የበቃውን Gaudete et exsultate “ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ” የሚለውን ሐዋሪያዊ ቃለ ሞዳን ውስጥ እንደ ተጠቀሰው “ምስጢረ ጥምቀትን በተቀበልንበት ወቅት የተቀበልነውን ጸጋ የቅድስና ፍሬ እንዲያፈራ ማድረግ ያስፈልጋል። ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክፍት በማድረግ ዓላማውን በእኛ እንዲተገብር ፍቀዱለት። ምክንያቱም የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሁልጊዜ ከእናተ ጋር ስለሆነ በፍጹም ተስፋ አትቁረጡ፣ የቅድስናን ፍሬ የሚያስገኘውን መንፈስ ቅዱስን ተላብሳችሁ ለመኖር ሞክሩ። ”

16 May 2018, 13:12