ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የክርስትና አባት እና እናት ልጆቻቸው የእምነት ጎዳናን ተከትለው ያድጉ ዘንድ ማገዝ ይኖርባቸዋል”
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ወይም ደግሞ እዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የእዚሁ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው በሚያዝያ 03/2010 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ ትኩረቱን ባደረገው የክፍል አንድ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ “ምስጢረ ጥመቀት የክርስትና ሕይውት መሰረት ነው” ማለታቸውን መገለጻችን ይታወሳል። በሚያዝያ 10/2010 ዓ.ም. አሁንም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ባደርጉት የክፍል ሁለት አስተምህሮ “ምስጢረ ጥምቀት የክርስትና እምነት ምልክት ነው” ማለታቸውን መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን በሚያዝያ 18/2010 ዓ.ም. አሁንም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ባደርጉት ክፍል ሦስት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ምስጢረ ጥምቀት “ክፉ መንፈስን የማሸንፊያ መሳሪያ ነው” ማለታቸውን ቀደም ባሉት ዝግጅቶቻችን መዘገባችን ይታወሳል። በሚያዝያ 24/2010 ዓ.ም. አሁንም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ባደረጉት ክፍል አራት የትምህርተ ክርስትሶስ አሰትምህሮ እንደ አገለጹት “አንድ ሰው ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ክርስቶስን መከተል በፍጹም አይችልም” ማለታቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በግንቦት 01/2010 ዓ.ም. ደግሞ አሁንም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ መሰረቱን ባደርገው የክፍል አምስት አስተምህሮ እንደ ገለጹት “ምስጢረ ጥምቀት ዳግም እንድንወለድ ያደረግናል” ማለታቸው መዘገባችን ያትወሳል።
በዛሬው እለት ማለትም በግንቦት 08/2010 ዓ.ም አሁን በምስጢረ ጥመቀት ዙሪያ ላይ ባድርጉት የክፍል ስድስት አስተምህሮ እና በእዚህ በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ ላልፉት አምስት ሳምንታት ስያደርጉት የነበረው አስተምህሮ ማብቂያ ላይ እንደ ገለጹት “የክርስትና እናት እና የክርስትና አባት” ልጆቻቸው የእምነት ጎዳናን ተከትለው ያድጉ ዘንድ ልያስተምሩዋቸው እና ሊረዱዋችው የገባል” ማለታቸው ተገልጹዋል።
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 08/2010 ዓ.ም. በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ አድርገውት የነበረውን የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።