ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በግንቦት 12/2010 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በግንቦት 12/2010 ዓ.ም   (ANSA)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፦ “መንፈስ ቅዱስ ልብን እና ክስተቶችን የመቀየር ኃይል አለው”

የግንቦት 12/2010 ዓ.ም “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” ጸሎት

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በተነሳ በሃምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ ለሐዋሪያቱ የላከበት የጴራቂሊጦስ በዓል በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 12/2010 ዓ.ም ተከብሮ ማለፉ ይታወቃል። ይህ የጴራቂሊጦስ በዓል በግንቦት 12/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በርካታ ቄሳውስት እና ምዕመናን በተገኙበት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት መንፈስ ቅዱስ ልብን እና ክስተቶችን የመቀየር ኃይል አለው ማለታቸው ተገልጹዋል

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ

ክቡራት እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 12/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያስሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

“የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!”

“በኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ ላይ ያተኮረው የፋሲካ ወቅት ዛሬ በምናከብረው የጴራቅሊጦስ በዓል የደመደማል። ይህ ክብረ በዓል ሐዋሪያት ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ጋር በጋራ ጸሎት በማድረግ ላይ በነበሩበት ወቅት መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ ወርዶ እንደ ነበረ ያስታውሰናል (ሐዋ. 2፡1-11)። የቤተክርስቲያን ቅድስና ጅማሬውን ያገኘው በእዚያ ወቅት ሲሆን ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ የቅድስና ምንጭ ነው፣ ለተወሰኑ ምርጥ ለሆኑ ሰዎች ብቻ የሚሰጥ ነገር ሳይሆን ለሁሉም የሚሰጥ ተልዕኮ ነው። በእርግጥ በምስጢረ ጥምቀት ሁላችንም የክርስቶስ መለኮታዊ ሕይወት ተካፋዮች መሆናችን የሚታወቅ ሲሆን በምስጢረ ሜሮን አምካይነት ደግሞ በዓለም ውስጥ የእርሱ መስካሪዎች ሆነናል። እግዚኣብሔር የሰው ልጆችን ለመቀደስ እና ለማዳን የፈልገው በግለሰብ ደረጃ እና በመካከላቸው ምንም ግንኙነት እንዳይኖር አድርጎ ሳይሆን ነገር ግን አንድ ሕዝብ እንዲሆኑ በማድረግ፣ በእውነት አማካይነት እርሱን እንዲያውቁት እና እርሱን በቅድስና እንዲያገለግሉት በማድረግ ነው። እግዚኣብሔር የደኽንነት እቅዱን በጥንት ጊዜ በነበሩት ነብያት አማካይነት መግለጹ ይታወቃል። ሕዝቅኤል በትንቢቱ “መንፈሴን በውስጣችሁ አሳድራለሁ፤ ሥርዐቴን እንድትከተሉና ሕጌን በጥንቃቄ እንድትጠብቁ አደርጋለሁ። ለቀድሞ አባቶቻችሁ በሰጠኋቸው ምድር ትኖራላችሁ፤ ሕዝቤም ትሆናላችሁ፤ እኔም አምላክ እሆናችኋሁ (ሕዝቅኤል 36:27-28) ይለናል። ነቢዩ ኢዩሔል “መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ፤ በእነዚያ ቀናት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎች ላይ እንኳ፣መንፈሴን ፈሳለሁ። የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ፣ እርሱ ይድናል (ኢዩኤል 2፡28-32) ይለናል። እነዚህ ሁሉ ትንቢቶች “አማላጅ እና ዘላቂነት ባለው መልኩ የመንፈስ ቅዱስን ዋስትና በሚሰጠን” በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተፈጻሚነትን አግኝተዋል። ዛሬ መንፍስ ቅዱስ የወረደበትን ቀን እያከበርን እንገኛለን። ከጴንጤ ቆስጤ ቀን ጀምሮ እስከ ጊዜው ፍጻሜ ድረስ፣ ይህም በክርስቶስ ምልኣት እስከምናገኝ ድረስ፣ ለመንፈስ ቅዱስ ድርጊቶች ራሱን ክፍት ለሚያደርጉ ሰዎች ሁሉ እና ትሁት ለመሆን ለሚሞክሩ ስዎች ሁሉ የሚሰጥ ስጦታ ነው። እውነተኛ የሆነ ደስታን እንድናጣጥም የሚያደርገን መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። መንፈስ ቅዱስ ወደ እኛ ውስጥ ገብቶ ደንዳናነታችንን ያስወግዳል፣ እናም ልባችንን በመክፈት እና ውስጣዊ ብስለትን በመፍጠር ከእግዚአብሔር እና ከባልንጄሮቻችን ጋር ያለንን ግንኙነት ያበረታታል። ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ “የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ ታማኝነት፣ ገርነት፣ ራስን መግዛት ነው” (ገላቲያ 5፡22) ይለናል። እነዚህን ሁሉ ፍሬዎች ገቢራዊ እንድናደርግ የሚረዳን መነፈስ ቅዱስ ነው። ለእዚህ ነው እንግዲህ ዛሬ ይህንን እግዚኣብሔር የሰጠንን ታላቅ ጸጋ እያከበርን የምንገኘው። ዛሬውም ቢሆን በዘመናችን ቤተክርስቲያን በእዚህ መንፈስ ቅዱስ በመታደስ፣ ቅዱስ ወንጌልን በሕይወታችን በደስታ ለመኖር እና ለመመስከር የታደሰች ወጣት ቤተክርስቲያን እንድዲሰጠን “በውስጣችን ለእግዚኣብሔር ክብር የተገባን ቅዱሳን እንሆን ዘንድ በውስጣችን ያለን መንፈስ እንድታነሳሳልን” የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማሪያምን አማላጅነት ልንማጸን ይገባል። ”

20 May 2018, 14:45