ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ 25/09/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ 25/09/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (© Servizio Fotografico L'Osservatore Romano)

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ክርስቲያኖች “ጋኔን የሰውን ክብር በመግፈፍ ርሃብ እና ባርነት ውስጥ ይከታል”

“ጋኔን የሰውን ክብር በመግፈፍ ርሃብ እና ባርነት ውስጥ ይከታል”

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ “ሰይጣን  የሰውን ክብር በመግፈፍ ሰዎች ለረሃብ እና ለባርነት እንዲዳረጉ ያደርጋል”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 24/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ሰይጣን  የሰውን ክብር በመግፈፍ ሰዎች ለረሃብ እና ለባርነት እንዲዳረጉ ያደርጋል ካሉ በኃላ በዛሬው ዓለማችን ውስጥ በክርስቲያኖች ላይ በተለያዩ ዓይነት ምክንያቶች የተነሳ ለምሳሌ በባሕል ቅኝ ግዛት፣ በጦርነት፣ በረሃብ፣ በባርነት ቀንበር ሥር እንዲወድቁ በማድረግ በዛሬው ዓለማችን ባሉ ክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ የሆነ ስደት እየደረሰ ነው ብለዋል።

የዚህ ዜና አቀናባሪ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ ቫቲካን

በዛሬው ዓለማችን “በክርስቲያኖች ላይ” ብቻ ሳይሆን በመላው የሰው ልጆች ላይ ከፍተኛ የሆነ ስደት እይተፈጸመ እንደ ሆነ በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱንስታቸው እነዚህም ስደተች ስልታዊ በሆነ መልኩ በባሕል ላይ በሚቃጡ የቅኝ ግዛት ተግባሮች፣ ጦርነቶችን በማስፋፋት፣ ረሃብ እንዲከሰት በማድረግ፣ በዘመናዊ የባርነት ቅኝ ግዛት ሥር ሰዎች እንዲገቡ በማድረግ እይተፈጸመ እንደ ሚገኝ ገልጸዋል።

“ምክንያቱም” አሉ ቅዱስነታቸው ምክንያቱም አሁን ያለንበት ዓለማችን "የባርነት ዓለም" ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ጌታ ይህንን ባርነት እንድንዋጋ ብርታትን ይሰጠናል፣ በእኛ ውስጥ በሚገኘው በክርስቶስ እና በእግዚኣብሔር ኃይል ይህንን ትግል ማሸነፍ እንችላለን ብለዋል።

በእለቱ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የላቲን ሥርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በእለቱ በቀዳሚነት ከ1ኛው የሐዋሪያው ጴጥሮስ መልእክት ምዕራፍ 4፡7-13 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና በጥንት ጊዜ በነበሩ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ላይ የደረሰውን ክፍተኛ ስደት በሚያመልክተው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰርቱን ባድረገው ስብከታቸው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ስደት የክርስቲያን ሕይወት አንዱ አካል መሆኑን ገለጸው ስደት ሁሌም በክርስቲያኖች ላይ የሚቃጣ ጉዳይ እንደ ሆነ አስምረው ኢየሱስ ክርስቶስ ለአባቱ ታማኝ በመሆኑ የተነሳ በእርሱም ላይ ስደት ደርሶ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን ለማጠናከር በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል. . .

“ስደት ዛሬም ቢሆን ክርስቲያኖች እይኖሩበት የሚገኝ ሁኔታ ነው፣ ምክንያቱም ዛሬም ቢሆን በጣም ብዙ ብዙ ሰማዕታት የሚሆኑ ሰዎች፣ ለእየሱስ ባላቸው ፍቅር የተነሳ ስደት የሚደርስባቸው ብዙ ሰዎች አሉ። በብዙ ሀገራት ክርስቲያኖች መብት የላቸውም። መስቀል በአንገትህ ላይ አንጠልጥለህ ከተገኘህ ወደ እስር ቤት ትወሰዳለህ፣ በእዚህም ምክንያት በእስር ላይ የሚገኙ ብዙ ሰዎች አሉ፣ ዛሬም ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ የተነሳ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ሰዎች አሉ። ይህ ጉዳይ ዜና ሆኖ አለመቅረቡ ደግሞ በጣም የሚያስገርመው ነገር ነው። በጋዜጦች እና በቴሌቪዢን ዜናዎች ላይ እነዚህን የመሳሰሉ ዘገባዎችን አያስተላልፉም። ነገር ግን ክርስቲያኖች መሰደዳቸውን ቀጥለዋል።”

ስደት የእግዚኣብሔር አምሳያ በሆኑ ሰዎች ላይ እየደረሰ ነው

አንድ ወንድ እና አንድ ሴት የእግዚኣቢሐር ሕያው አምሳል በመሆናቸው የተነሳ ብቻ ለየት ባለ መልኩ ስደት እየተቃጣባቸው እንደ ሆነ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል. . .

“በክርስቲያኖች ላይ ይሁን በሌሎች ሰዎች ላይ እየተቃጣ በሚገኘው ስደት ጀርባ የሰይጣን እጅ አለ፣ ክርስቲያኖች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት የሚያፈራርስ እና ሰዎች የእግዚኣብሔር ሕያው አምሳል ሆነው እንዳይኖሩ የሚያደርግ ሰይጣን አለ። ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ነው ሰይጣን ይህንን ተግባሩን ማካሄድ የጀመረው፣ ይህንንም በኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ ተጠቅሶ እናገኘዋለን፣ እግዚኣብሔር በአንድ ወንድ እና በአንድ ሴት መካከል በእርሱ መልክ እና አምሳል የተፈጠረውን ሕብረት አፈራርሶ ነበር። ይህንንም ማድረግ ተሳክቶለት ነበር። ይህንንም ስኬት ያገኘው በማታለል እና በማባበል ነበር-እነዚህም ነገሮች እርሱ የሚጠቀምባቸው የጦር መሳሪያዎቹ ናቸው። ሁሌም እንዲህ ነው የሚያደርገው። ዛሬም ቢሆን ይህ ኃይል በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፣ በሰው ልጆች ላይ የተቃጣ ጥቃት አድርጌ ነው የምቆጥረው፣ ምክንያቱም ይህ የጥፋት ማዕበል በጣም እያደገ በመሄድ ላይ ስለሆነ ነው።”

ከረሃብ፣ ከባርነት፣ ከባሕል ቅኝ ግዛት፣ ከጦርነት ጀርባ ሰይጣን ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት በዓለማን ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘው ረሃብ የኢፍታዊ ተግባር ውጤት ነው፣ ይህም የሰው ልጆችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም ምንም እንኳን በዓለማችን ላይ በጣም በቂ በሚባል ደረጃ የምግብ ክምችት ቢኖርም በጣም ብዙ ሰዎች ግን ምግብ እንዳያገኙ እየተድረገ በመሆኑ የተነሳ ነው ብለዋል። የሰው ልጆችን ጉልበት ያለአግባቡ መበዝበዝን በተመለከተ  እና በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ዓይነት የባርነት ቀንበር ውስጥ የሚገኙ የሰው ልጆችን በዋቢነት በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በቅርቡ አንድ በድብቅ በተቀረጸ ተንቀሳቃሽ ምስል ወይም ቪዲዮ ላይ እንደ ተመለከቱት በአንድ እስር ቤት ውስጥ ታጭቀው የሚኖሩ እና ከፍተኛ የሆነ ጭቆና እና ጥቃት እየተፈጸመባቸው የሚገኙ ስደተኞችን መመልከታቸውን በዋቢነት ጠቅሰው ይህ ተግባር እየተፈጸመ የሚገኘው የሰው ልጆች ሰብኣዊ መብትን የሚያስጠብቅ ሕግ ከተደነገገ ከ70 ዓመታት በኃላ መከሰቱ ደግሞ በጣም የሚያሳዝን ተግባር ነው ብለዋል።

በተለያዩ ባሕሎች ላይ እየተቃጣ ያለውን ባሕልን የመቀየር የቅኝ ግዛት ዘመቻን በተመለከተ በስብከታቸው የተናገሩት ቅዱስነታቸው ከሰዎች ፈቃድ ውጪ በመሄድ የሌሎችን ሰዎች ባሕሎች ላይ ጫና በመፍጠር የሰዎችን ባሕል ለማስቀየር እንደ ሚጥሩ ገልጸው ሰብኣዊ ያልሆኑ ባሕሎችን በሌሎች ላይ በመጫን የሰው ልጆችን ሕይወት ለማበላሸት ቀን ተቀን እንደ ሚኳትኑ ገልጸዋል።

ጦርነትን በተመለከተ በስብከታቸው የተናገሩት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል. . .

“በመጨረሻም ጦርነቶችን በእግዚኣብሔር አምሳል የተፈጠሩትን የሰው ልጆችን የማጥፊያ መሳሪያ እንደ ሆነ ለማሰብ እንችላለን። በተጨማሪም ጦርነት እንዲካሄድ የሚያደርጉ ሰዎች፣ ይህን ጦርነት የሚያካሂዱት በሌሎች ሰዎች ላይ የበላይነትን እንዴት አድርገው እንደ ሚጎናጸፉ ያቅዳሉ። የሰው ልጆችን ሕይወት የሚያጠፋውን የጦር መሳሪያ የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ያሉዋቸው በጣም ብዙ ሰዎች አሉ፣ እነርሱም የሰዎችን አካልዊ፣ ግብረገባዊ እና ባሕላዊ ገጽታዎችን ያጠፋሉ። እነዚህ ሰዎች ክርስቲያኖች ናቸው ልንላቸው በፍጹም አንችልም። ምክንያቱም በእግዚኣብሔር አምሳል የተፈጠሩትን ሰዎች ያጠፋሉና። ለእዚህም ነው ሰይጣን ነው እያሳደዳቸው የሚገኘው የምለውም በእዚሁ ምክንያት ነው። አሁንም ቢሆን እነዚህ ሰዎች ክርስቲያኖችን ማሳደድ ቀጥለዋል። እኛ ይህንን በፍጹም ማንጸባረቅ የለብንም። በዛሬው ዓለማችን ስደት እየደርሰባቸው የሚገኙ ሰዎች ክርስቲያኖች ብቻ አይደሉም፣ የሰው ልጆች ሁሉ ላይ ነው እንጂ! ምክንያቱም ይህንን ስደት እያስከሰተ የሚገኘው ቁንጮ አካል ይህንን ጥቃት እየፈጸመ የሚገኘው በእግዚኣብሔር መልክ እና አምሳል በተፈጠሩ የሰው ልጆች ሁሉ ላይ በመሆኑ የተነሳ ነው። ጥቃት ይፈጽማሉ ከእዚያም የሰው ግጽታን ያጠፋሉ። ይህንን መረዳት ቀላል አይደለም፣ ይህንን በሚገባ ለመረዳት በጣም ብዙ ጸሎት መጸለይ ያስፈልጋል።”

 

 

01 June 2018, 10:35
ሁሉንም ያንብቡ >