ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ክርስቲያኖች “ጋኔን የሰውን ክብር በመግፈፍ ርሃብ እና ባርነት ውስጥ ይከታል”
ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ “ሰይጣን የሰውን ክብር በመግፈፍ ሰዎች ለረሃብ እና ለባርነት እንዲዳረጉ ያደርጋል”
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 24/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ሰይጣን የሰውን ክብር በመግፈፍ ሰዎች ለረሃብ እና ለባርነት እንዲዳረጉ ያደርጋል ካሉ በኃላ በዛሬው ዓለማችን ውስጥ በክርስቲያኖች ላይ በተለያዩ ዓይነት ምክንያቶች የተነሳ ለምሳሌ በባሕል ቅኝ ግዛት፣ በጦርነት፣ በረሃብ፣ በባርነት ቀንበር ሥር እንዲወድቁ በማድረግ በዛሬው ዓለማችን ባሉ ክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ የሆነ ስደት እየደረሰ ነው ብለዋል።
የዚህ ዜና አቀናባሪ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ ቫቲካን
በዛሬው ዓለማችን “በክርስቲያኖች ላይ” ብቻ ሳይሆን በመላው የሰው ልጆች ላይ ከፍተኛ የሆነ ስደት እይተፈጸመ እንደ ሆነ በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱንስታቸው እነዚህም ስደተች ስልታዊ በሆነ መልኩ በባሕል ላይ በሚቃጡ የቅኝ ግዛት ተግባሮች፣ ጦርነቶችን በማስፋፋት፣ ረሃብ እንዲከሰት በማድረግ፣ በዘመናዊ የባርነት ቅኝ ግዛት ሥር ሰዎች እንዲገቡ በማድረግ እይተፈጸመ እንደ ሚገኝ ገልጸዋል።
“ምክንያቱም” አሉ ቅዱስነታቸው ምክንያቱም አሁን ያለንበት ዓለማችን "የባርነት ዓለም" ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ጌታ ይህንን ባርነት እንድንዋጋ ብርታትን ይሰጠናል፣ በእኛ ውስጥ በሚገኘው በክርስቶስ እና በእግዚኣብሔር ኃይል ይህንን ትግል ማሸነፍ እንችላለን ብለዋል።
በእለቱ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የላቲን ሥርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በእለቱ በቀዳሚነት ከ1ኛው የሐዋሪያው ጴጥሮስ መልእክት ምዕራፍ 4፡7-13 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና በጥንት ጊዜ በነበሩ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ላይ የደረሰውን ክፍተኛ ስደት በሚያመልክተው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰርቱን ባድረገው ስብከታቸው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ስደት የክርስቲያን ሕይወት አንዱ አካል መሆኑን ገለጸው ስደት ሁሌም በክርስቲያኖች ላይ የሚቃጣ ጉዳይ እንደ ሆነ አስምረው ኢየሱስ ክርስቶስ ለአባቱ ታማኝ በመሆኑ የተነሳ በእርሱም ላይ ስደት ደርሶ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።
ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን ለማጠናከር በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል. . .
ስደት የእግዚኣብሔር አምሳያ በሆኑ ሰዎች ላይ እየደረሰ ነው
አንድ ወንድ እና አንድ ሴት የእግዚኣቢሐር ሕያው አምሳል በመሆናቸው የተነሳ ብቻ ለየት ባለ መልኩ ስደት እየተቃጣባቸው እንደ ሆነ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል. . .
ከረሃብ፣ ከባርነት፣ ከባሕል ቅኝ ግዛት፣ ከጦርነት ጀርባ ሰይጣን ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት በዓለማን ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘው ረሃብ የኢፍታዊ ተግባር ውጤት ነው፣ ይህም የሰው ልጆችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም ምንም እንኳን በዓለማችን ላይ በጣም በቂ በሚባል ደረጃ የምግብ ክምችት ቢኖርም በጣም ብዙ ሰዎች ግን ምግብ እንዳያገኙ እየተድረገ በመሆኑ የተነሳ ነው ብለዋል። የሰው ልጆችን ጉልበት ያለአግባቡ መበዝበዝን በተመለከተ እና በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ዓይነት የባርነት ቀንበር ውስጥ የሚገኙ የሰው ልጆችን በዋቢነት በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በቅርቡ አንድ በድብቅ በተቀረጸ ተንቀሳቃሽ ምስል ወይም ቪዲዮ ላይ እንደ ተመለከቱት በአንድ እስር ቤት ውስጥ ታጭቀው የሚኖሩ እና ከፍተኛ የሆነ ጭቆና እና ጥቃት እየተፈጸመባቸው የሚገኙ ስደተኞችን መመልከታቸውን በዋቢነት ጠቅሰው ይህ ተግባር እየተፈጸመ የሚገኘው የሰው ልጆች ሰብኣዊ መብትን የሚያስጠብቅ ሕግ ከተደነገገ ከ70 ዓመታት በኃላ መከሰቱ ደግሞ በጣም የሚያሳዝን ተግባር ነው ብለዋል።
በተለያዩ ባሕሎች ላይ እየተቃጣ ያለውን ባሕልን የመቀየር የቅኝ ግዛት ዘመቻን በተመለከተ በስብከታቸው የተናገሩት ቅዱስነታቸው ከሰዎች ፈቃድ ውጪ በመሄድ የሌሎችን ሰዎች ባሕሎች ላይ ጫና በመፍጠር የሰዎችን ባሕል ለማስቀየር እንደ ሚጥሩ ገልጸው ሰብኣዊ ያልሆኑ ባሕሎችን በሌሎች ላይ በመጫን የሰው ልጆችን ሕይወት ለማበላሸት ቀን ተቀን እንደ ሚኳትኑ ገልጸዋል።
ጦርነትን በተመለከተ በስብከታቸው የተናገሩት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል. . .