ፈልግ

2022.06.09 Capo Verde - Giovani della Diocesi di Santiago

ወጣት ቅዱሳን

የቤተ ክርስትያን ልብም ሕይወታቸውን ለክርስቶስ በሰጡ" አንዳንዶቹ ደግሞ የሰማዕት ሞት ለመሞት እንኳን ሳይቀር ለመሞት በተዘጋጁ በወጣት ቅዱሳን የተሞላች ነች”የወጣቱ ክርስቶስ ውድ ምልክቶች ነበሩ" አንጸባራቂ ምስክርነቶቻቸው ያበረታቱናል ከድካማችንም ያነቁናል”ሲኖዱ እንዳመለከተው" “ብዙ ወጣት ቅዱሳን ወጣትነታቸውን ባለው ውበታቸው ሁሉ የሚያንጸባርቁ" በዘመናቸውም የለውጥ እውነተኛ ነቢያት የሆኑ ናቸው”ተምሳሌትነታቸው የሚያሳየን" ክርስቶስን ለማግኘት ራሳቸውን አሳልፈው በሰጡ ግዜ" ወጣቶች ምን የማድረግ ችሎታ እንዳላቸው ነው”።

“በወጣት ቅዱሳን አማካይነት ቤተ ክርስትያን መንፈሣዊ ፍቅርን እና ሐዋርያዊ ጥንካሬን ለማደስ ትችላለች”ከብዙ ወጣት ሕዝብ መልካም ሕይወቶች የሚወጣ የቅድስና ቅባት" የቤተክርስትያን እና የዓለምን ቁስል ሊፈውስ" ሁልጊዜ  ወደምንጠራበት ወደ ፍቅር ሙላት እንደገና ሊያመጡን: ቅዱሳን ወጣቶች ወደ ቀደመው ፍቅራችን እንድንመለስ ሊያነሣሡን ይችላሉ”(ራዕ 2:4)። አንዳንድ ወጣት ቅዱሳን ወደ ሙሉ ሰውነት ፈጽሞ አልደረሱም" ሆኖም ግን ወጣትነታችንን የምናሳልፍበት ሌላውን መንገድ አሳይተውናል”እስቲ በየራሳቸው መንገድ እና በተለያዩ ዘመናት የቅድስና ሕይወት የመሩ አንዳንዶችን እንመልከት”።

በሦስተኛው ክፍለ ዘመን" ቅዱስ ሴባስተያን የፕሪቶሪያን ጋርድ ወጣት ካፕቴን ነበር”እንደሚባለው ከሆነ አዘውትሮ ስለ ክርስቶስ ይናገርና" እምነቱን እንዲተው እስከ መገደድ ድረስ የስራ ባልደረቦቹን ወደ እምነት ለማምጣት ይሞክር ነበር”እምነቱን ባለመተዉም ምክንያት በቀስት ተወጋ" ቢወጋም ስላልሞተ ክርስቶሰን ያለ ምንም ፍርሃት ማወጁን ቀጠለበት”በመጨረሻውም ተደብድቦ ሞተ”።

የአሲሲው ቅዱስ ፍራንሲስ" ገና ወጣት እና ትልልቅ ሕልሞች የነበሩት ሰው" ኢየሱስ ልክ እንደ እርሱ በድኽነት በመኖር በምስክርነቱ ቤተ ክርስትያንን እንደገና እንዲያንጽ ሲነግረው ጥሪውን ሰማ”የነበረውንም ሁሉን ነገር በደስታ ተወ አሁን የዓለምአቀፍ ወንድማማችነት ቅዱስ ነው" የሁሉም ወንድም”ጌታን ስለ ፍጥረቶቹ ከፍ አደረገ”ፍራንሲስ በ1226 ዓረፈ”።

ቅድስት ጆአን በ 1412 ተወለደች”ወጣት ገበሬ ልጅ ነበረች" በለጋ እድሜዋም ቢሆን" ፈረንሳይን ከወራሪ ጠላት ተከላከለች”ባህርይዋ" ድርጊቶችዋ እና እምነቷን እንዴት እንደምትኖረው በትክክል ስላልተረድዋት" በእሳት ተቃጥላ እንድትሞት ሆነች”።

የተባረከው እንድርያስ ወጣት የዐሥራ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን ቬትናማዊ ነበር”የሃይማኖት ትምህርት አስተማሪ ነበር እና ሚሽነሪዎችን ያግዝ ነበር”በእምነቱ ምክንያት ለእስር ተዳርጎ ነበርና እምነቱን እንዲተው ቢገደድም እምቢ በማለቱ" ተገደለ”እንድርያስ ሲገደልም የኢየሱስን ስም እየጠራ ነው የሞተው”።

በዚያው ክፍለ ዘመን" የሰሜን አሜሪካ ተወላጅ የነበረችው ቅድስት ካቴሪ በእምነቷ ምክንያት ያሳድዷት ስለነበር ለማምለጥ ስትል በዱር ከሦስት ኪሎ ሜትር በላይ በእግር ተጉዛለች”ራሷን ለእግዚአብሔር በመሰዋት ስትሞት “ኢየሱስ እወድሃለሁ” እያለች ሕይወቷ አለፈ”።

ቅዱስ ዶሚኒክ ሳቪዮ ያለውን መስዋዕት ሁሉ ለማርያም ሰዋ”ቅዱስ ዶን ቦስኮ ቅድስና ከሚያካትተው አዘውትሮ መደሰትንም ጭምር ነው ብሎ ስለነገረው" ልቡን ወደሌላው በሚተላለፍ ደስታ እንዲሞላ ፈቀደ”በጣም ወደተጣሉና ወደተረሱ ጓደኞቹ መቅረብ ፈለገ”ዶሚኒክ በዐሥራ ዐራት ዓመት እድሜው" “እንዴት የሚያስደንቅ ስሜት ነው የሚሰማኝ!” እያለ ሕይወቱ አለፈ”።

ቅድስት ተሬዛ ዘ ሕጻኑ ኢየሱስ በ 1873 ነበር የተወለደችው”በዐሥራ አምስት ዓመት እድሜዋ" ብዙ ተግዳሮቶችን ካለፈች በኋላ የካርሜላይት ኮንቬንትን መቀላቀል ተሳካላት”ተሬዛ የጌታን ፍቅር በትንሽ መንገድ በእምነት እየኖረች በቤተ ክርስትያን ልብ ውስጥ የፍቅር እሳት እንዲነድድ በጸሎት ትተጋ ነበር”

ቼፋሪዮ ናሙንቹራ ወጣት አርጀንቲናዊ" የገጠራማው ተወላጆች አለቃ ልጅ ነበር”ወደ ጎሣው በመመለስ ኢየሱስ ክርስቶስን የማስተዋወቅ መሻት ውስጡን የሞላው ወጣት የሳሊዢያን ሴሚናሪያን ሆኖ ነበር”በ 1905ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ”።

የተባረከው ኢሲዶር ባካንጃ በኮንጎ የተወለደ እምነቱን የመሰከረ ሰው ነበር”ክርስትናን ለሌሎች ወጣቶች በማብሰሩ የተነሣ ቶርች የተደረገ ማለትም የተሠቃየ ወጣት ነበር”ገዳዩን ይቅር እያለ በ 1909 ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ”።

በ 1925 የሞተው የተባረከው ፓየር ጂዮርጂዎ ፍራሳቲ “በዙሪያው ሁሉ ያለውን አብሮ በሚወስድ ሐሴት የተሞላ" በሕይወቱ ውስጥ የነበሩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንኳን የሚቋቋም ደስታ የነበረው ወጣት ነበር$” 22 ፓየር እንደሚለው በቅዱስ ቁርባን የተቀበለውን የየሱስን ፍቅር" ድኾችን በመርዳት እና በመጎብኘት ምላሽ መስጠት እንደሚፈልግ ነበር”።

የተባረከው ማርሴል ካሎ በ 1945 ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ ወጣት ፈረንሳዊ ነበር”በኦስትሪያ የኮንሰንትሬሽን ካምፕ ውስጥ ታስሮ በከባድ ስራ ውስጥ ሌሎች እስረኞችን በእምነት የሚያበረታታ ወጣት ነበር”።

በ 1990 ያረፈችው" ወጣቷ የተባረከችው ቺያራ ባዳኖ" “ሥቃይ እንዴት በፍቅር እንደሚለወጥ የተለማመደች ነበረች .... የሠላምዋና የደስታዋ ቁልፍ በጌታ ላይ ያላት ሙሉ እምነት እና ህመምዋን ለእርሷና እንዲሁም ለሌሎች ሲል የሚገልጽበት ምስጢራዊ አገላለጽ ነው ብላ መውሰዷ ነበር”።

እነዚህ እና ሌሎችም ብዙ ወጣቶች ምናልባትም በጸጥታ ሆነው ወንጌልን በሚገባ በሙላት የኖሩ" በሙሉ ደስታ ውስጥ እንድትሆን ለቤተ ክርስትያን የሚማልዱ" የበረቱ ወጣቶች ለምድር የቅድስና ምስክርነት ያለቸው ይኖሩ ይሆናል”።

ምንጭ፡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለወጣቶች እና ለተቃላልው ለእግዚአብሔር ሕዝብ ክርስቶስ ሕያው ነው፣ ተስፋችን ነው በሚል አርዕስት ከጻፉት ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ ከአንቀጽ 49-63 ላይ የተወሰደ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ ባራና በርግኔ

15 September 2023, 13:51