ፈልግ

2023.08.05 GMG Lisbona Volontari

የናዝሬቷ ወጣት ማርያም

በቤተ ክርሰትያን ልብ ውስጥ" ማርያም ታበራለች”በትጋትና በጸጥታ ክርስቶስን ለመከተል ለምትፈልግ ወጣት ቤተ ክርስትያን ዋነኛዋ ሞዴል ናት”በጣም ወጣት ሆና እያለች" የመልአኩን መልእክት ተቀበለች" ሆኖም ግን ጥያቄ ለመጠየቅ አልፈራችም ነበር (ሉቃ 1:34) በተከፈተ ልብ እና ነፍስ መልስ ሰጠች" “እነሆኝ ባሪያህ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች” (ሉቃ 1: 38)።

“ሁልጊዜም ቢሆን በወጣቷ ማርያም 'እሺ' የማለት ብርታት እንደነቃለን" ለመልአኩ በተናገረችው በእነዚያ ቃላት ውስጥ ባለው ጥንካሬ 'እንደ ቃልህ ይሁን'“ይህ ዝም ብሎ እንደነገሩ የተቀበለ አቀባበል ወይም በስሱ የተመለሰ 'አዎንታ' አልነበረም " ማለትም “እስቲ እሺ እንሞክረውና ምን እንደሚመጣ እናያለን”" ዓይነት መልስ አልነበረም”ቁርጠኛ ውሳኔ ነበር; ሊሆን ያለውን በመቀበል ምንም ሳታቅማማ ደግማ ለማሰብም ግዜ ሳትሰጥ ነበር “እሺ” ያለችው”የእርስዋ “እሺታ” ለመከወን የተዘጋጀች" የሚመጣውን ሁሉ ለመቀበል" ያላትን ሁሉ ለመስጠት" ቃል ኪዳንን የምትሸከም ሴት መሆንዋን ከማወቅ ውጭ" ያለ ምንም ተጨማሪ ጥበቃ የሌላት ሴት የሰጠችው መልስ ነው”ስለዚህ እያንዳንዳችሁን ልጠይቅ እና: ራሳችሁን እንደ ቃል ኪዳን ተሸካሚ አድርጋችሁ ትቆጥራላችሁ ወይ? ልወስድ የምችለው ምን ዓይነት ቃል ኪዳን ነው በልቤ ውስጥ የሚገኘው? የማርያም ተልእኮ ያለ ምንም ጥርጥር እጅግ አዳጋች ነበር" ነገር ግን ከፊቷ የነበሩት ተግዳሮቶች 'አሻፈረኝ' ለማለት ምክንያቶች አልነበሩም”በእርግጥ ነገሮች ሊወሳሰቡ ይችላሉ" ነገር ግን ልክ ፍርሃት እንደሚያሽመደምደን አይደለም ምክንያቱም በቅድሚያ ነገሮች ግልጽ ወይም እርግጠኛ አይደሉም”ማርያም ምንም ዓይነት የመድኅን ፖሊሲ አልነበራትም! የሚያስከትለውን አደጋ ይሁን አለች" በዚህም ምክንያት ጠንካራ" ተጽእኖ ፈጣሪ" የእግዚአብሔር ተጽእኖ ፈጣሪ ነች$“እሺታዋ እና ለማገልገል የነበራት መሻት ከየትኛውም ጥርጣሬና ችግር ሁሉ በላይ ነበር$” ለመገለል ወይም ደግሞ ለሚምታታ አሳብ እጅ ሳትሰጥ" “የልጅዋን መከራ ተጋርታለች" በእይታዋ እየደገፈች በልብዋ ጠብቃዋለች”የመከራው ተካፋይ ብትሆንም ሽነፈት ግን ገብቷት አያውቅም”የብርታት ሴት ነበረች 'እሺታዋን' የምትደግፍ አብራ የምትሆን" የምትንከባከና የምታቅፍ ነበረች”ተስፋን የምታሳድግ ታላቅ አሳዳጊ ነበረች.... ከእርስዋ" ግትር ጽናትን" አይበገሬነትን" ሁሉን እንደገና ለመጀመር ዝግጁነትን" 'እሺ' ማለትን እንማራለን”።

ማርያም ልቧ በሐሴት የተሞላ ወጣት ሴት ነበረች (ሉቃ 1:47) በመንፈስ ቅዱስ ብርሃን የተሞላ ዐይኗን የምታንጸባርቅ" ሕይወትን በእምነት በልብዋ (ሉቃ 2: 19" 51) የምትጠብቅ ነበረች”የአክስትዋ ልጅ እየፈለገቻት እንደሆነ በሰማች ግዜ ምንም ሳትዘገይ በፍጥነት ወጥታ የሄደች በጣም ጠንካራ ሴት ነበረች”ስለ ራስዋ እቅድ ምንም አላሰበችም" 'ፈጥናም' ወደ ኮረብታማው አገር ሄደች ይላል" (ሉቃ 1:39)።

 ሕጻኑ ልጅዋ ጥበቃ ሲያስፈልገው" ማርያም ከዮሴፍ ጋር ወደ ሩቅ ምድር ሸሸች”(ማቴ 2: 13-14) በሌላም ጊዜ ከሌሎች ደቀ መዛሙርትም ጋር አብራ በመሆን የመንፈስ ቅዱስ ሙላትን ትጠባበቅ ነበር”(ሐዋ 2: 4-11) 48. ዛሬ" ማርያም እኛን ልጆችዋን በሕይወት በምናደርገው በአብዛኛው አድካሚ በሆነው ጉዟችን" የብርሃን ተስፋ እንዳይጨልም የምትጠብቅ እናት ናት”ምክንያቱም ዋናው መሻታችን እርሱ ነው: የተስፋ ብርሃን እንዳይጨለም”ሕዝብ ትመለከታለች: የምትወደውን በብዙ ጫታ መኻከል በልባቸው ጸጥታ ውስጥ ለሚፈልጓት እናታችን ማርያም ይህንን መንገደኛ ወጣት ሕዝብ ትመለከታለች”በእናታችን እይታ ውስጥ" ያለው የተስፋ ጸጥታ ነው”ወጣትነታችን እንደ አዲስ እንዲያበራ ታደርጋለች”።

ምንጭ፡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለወጣቶች እና ለተቃላልው ለእግዚአብሔር ሕዝብ ክርስቶስ ሕያው ነው፣ ተስፋችን ነው በሚል አርዕስት ከጻፉት ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ ከአንቀጽ 43-48 ላይ የተወሰደ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ ባራና በርግኔ

08 September 2023, 10:04