ፈልግ

ካርዲናል ጆሴፍ ዊሊያም ቶቢን ካርዲናል ጆሴፍ ዊሊያም ቶቢን  

በቤተክርስቲያን ተልዕኮ ውስጥ ምዕመኑን ተካፋይ ማድረግ ያስፈልጋል

“በእግዚአብሔር የተመሠረተ ሕያው ብዝሃነት፣ ሰብዓዊ ክብርና ሰላማዊ አንድነት በምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት (በአመሰያ) ሀገራት”

የቤክርስቲያን መሪዎች የሚያደጉት መነኛውም ጉባሄ በቤተክርስቲያን ተልዕኮ የአስተዳደር መዋቅር ውስጥ የትብብር መዋቅሮችን በመገንባት አስተዋጾ ማድረግ እንደ ሚገባው ተገለጸ።

በአሁኑ ወቅት “በእግዚአብሔር የተመሠረተ ሕያው ብዝሃነት፣ ሰብዓዊ ክብርና ሰላማዊ አንድነት በምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት (በአመሰያ) ሀገራት” በሚል መሪ ቃል ከሐምሌ 6-16/2010 ዓ.ም በሀገራችን በኢትዮጲያ መዲና በአዲስ አበባ 19ኛው የምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት ጉባኤ በመካሄድ ላይ እንደ ሚገኝ ቀደም ሲል መገለጻችን ይታወሳል።

በእዚህ ጉባሄ ላይ ከተጋበዙ እንግዶች መካከል አንዱ የሆኑት በኒዋርክ የኒው ጄርሲ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ክቡር ካርዲናል ጆሴፍ ዊሊያም ቶቢን መገኘታቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እርሳቸው በእዚሁ 19ኛው የምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባሄዎች ኅብረት ጉባኤ ላይ ተገኝተው ባደርጉት ንግግር እንደ ገለጹት የምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባሄዎች ኅብረት ሀገራት በቀጠናው የሚገኙ ሕዝቦችን ወደ እግዚኣብሔር ማምጣት እንደ ሚገባቸው በቀጠናው የሚደረጉ ማነኛቸውም የቤተክርስቲያኗ እንቅስቃሴዎች በኅበረት እና በጋር በመደጋገፍ ላይ በተመሰረተ መልኩ መከናወን እንደ ሚገባቸው ጨምረው ገለጸዋል።

ካርዲናል ጆሴፍ ዊሊያም ቶቢን እንደ ገለጹት የቤክርስቲያን መሪዎች የሚያደጉት መነኛውም ጉባሄ በቤተክርስቲያን ተልዕኮ የአስተዳደር መዋቅር ውስጥ የትብብር መዋቅሮችን በመገንባት አስተዋጾ ማድረግ እንደ ሚገባው ገለጸዋል።

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ ሰነድ እንደ ሚያስረዳው መነኛውም የቤተክርስቲያኒቷ መንፈሳዊ ተልዕኮ መከናወን የሚገባው የእግዚኣብሔርን ሕዝብ ባካተተ መልኩ መሆን እንደ ሚገባው፣ አንድ ቤተክርስቲያን እንደ መሆናችን መጠን እርስ በእርሳችን በመደጋገፍ ሊደረግ የሚገባ ተልዕኮ እንዲሆን እንደ ሚያሳብ ካርዲናል ጆሴፍ ዊሊያም ቶቢን አስታውሰዋል።

በምስጢረ ጥምቀት እና በምስጢረ ሜሮን አማካይነት ሁሉም የቤተክርስቲያኒቱ አባለት መንፈስ ቅዱስን በመቀበላቸው የተነሳ ሁሉም የክርስቲያን ማኅበረሰብ በጋራ በአንድ ድምጽ የጋራ በሆኑ የእምነት እና የስነ-ምግባር ጉዳዮች ላይ በአንድ ድምጽ መወሰን እና መነጋር እንደ ሚኖርባቸው አሳስበዋል።

በቤተክርስቲያኒቷ ውስጥ የሚካሄዱ መነኛቸውም ጉባሄዎች ሕዝቡ የቤተክርስቲያን አስተዳድሪዎችን ከሁሉም በላይ እንደ ሆኑ አድርጎ የሚቆጥሩ ከሆነ ያንን የሚፈለገውን በቤተክርስቲያን ውስጥ ሊኖር የሚገባውን ኅበረት እና አንድነት ማረጋገጥ በጣመ አስቸጋሪ እንደ ሚሆንም ካርዲናል ጆሴፍ ዊሊያም ቶቢን ጨምረው ገልጸዋል።

ሕበረት ያላት ቤተክርስቲያን ታዳምጣለች፣ ይህም ደግሞ የቤተክርስቲያን መሪዎችን መንፈሳዊ ስልጣን የሚገዳደር እንዳልሆነ የጠቀሱት ካርዲናል ጆሴፍ ዊሊያም ቶቢን  የቤተክርስቲያን አጠቃላይ መዋቅራዊ አስተዳደር እንደ አንድ ፒራሚድ ከላይ ወደ ታች ሳይሆን ነገር ግን በተቃራኒው ከታች ወደ ላይ እንደ ሆነ አስታውሰው ይህም ደግሞ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች የተጠሩት የእግዚኣብሔርን ሕዝብ ለማገልገል እንደ ሆን የሚያስ መዋቅር ነው ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

በአሁኑ ወቅት “በእግዚአብሔር የተመሠረተ ሕያው ብዝሃነት፣ ሰብዓዊ ክብርና ሰላማዊ አንድነት በምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት (በአመሰያ) ሀገራት” በሚል መሪ ቃል ከሐምሌ 6/2010 ዓ.ም በሀገራችን በኢትዮጲያ መዲና በአዲስ አበባ 19ኛው የምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት ጉባኤ በመካሄድ ላይ እንደ ሚገኝ ቀደም ሲል መገለጻችን የሚታወስ ሲሆን ይህ ጉባሄ በሐምሌ 16/2010 ዓ.ም እንደ ሚጠናቀቅ ከስፍራው የደርሰን ዘገባ ያስረዳል።

15 July 2018, 11:42