ፈልግ

 በአሜሪካ፣ በፔንስልቬንያ ግዛት ውስጥ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ማምረቻ በአሜሪካ፣ በፔንስልቬንያ ግዛት ውስጥ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ማምረቻ   (AFP or licensors)

በዓለም ላይ በየዓመቱ ለወታደራዊ ወጪ የሚወጣው ገንዘብ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል ተባለ

የስቶክሆልም ዓለም አቀፍ የሰላም ምርምር ኢንስቲትዩት (SIPRI) በቅርቡ ያደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በ 2015 ዓ.ም. ብቻ በዓለም አቀፍ ደረጃ የወጣው ወታደራዊ ወጪ ወደ 2.443 ትሪሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱ የተነገረ ሲሆን፥ ዓመታትን ባስቆጠሩ ውጥረቶች እና በክልላዊ ግጭቶች ተገፋፍተው፣ እንደ አሜሪካ፣ ቻይና እና ሩሲያ ያሉ ከፍተኛ የጦር ወታደራዊ ወጪ አውጪዎች የጭማሪውን ደረጃው ሲመሩ፥ ክልላዊ የሆኑ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች እና አዳዲስ የሚከሰቱ እሳቤዎች በዓለም ዙሪያ የወታደራዊውን ወጪ ከፍ እንዲል አድርገውታል ተብሏል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ባለፈው ዓመት ማለትም በ 2015 ዓ.ም. የዓለም ወታደራዊ ወጪ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ከፍ ያለ ሲሆን፥ በአስደናቂ ሁኔታ 2.443 ትሪሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በከፍተኛ ደረጃ የ6.8 በመቶ እድገት እንዳሳየና፣ ይህም ከ2001 ዓ.ም. ወዲህ የታየው ከፍተኛው ጭማሪ እንደሆነ ተነግሯል።

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ፣ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የሚታዩት ከፍተኛ ውጥረቶች፣ ጂኦፖለቲካዊ ፉክክር እና ክልላዊ ግጭቶች ለታየው ከፍተኛ ጭማሪ ምክንያት እንደሆኑ ያሳያል።

ከፍተኛ ወጪ አውጪዎች

የስቶክሆልም ዓለም አቀፍ የሰላም ምርምር ኢንስቲትዩት እንደገለጸው በ2015 ዓ.ም. ዩናይትድ ስቴትስ፣ ቻይና እና ሩሲያን ጨምሮ 10 ከፍተኛ ገንዘብ አውጭዎች ወታደራዊ ወጪያቸውን መጨመራቸውን የዘገበ ሲሆን፥ እንደ ሪፖርቱ መሰረት አምስቱ ከፍተኛ ወታደራዊ ወጪ የሚያወጡ ሃገራት ዩናይትድ ስቴትስ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ሩሲያ ሲሆኑ፥ በ2013 ዓ.ም. ዩናይትድ ስቴትስ 916 ቢሊዮን ዶላር ለጦር ኃይሏ በመመደብ ቀዳሚውን ስፍራ እንደያዘች እና የቻይናው መከላከያ በበኩሉ 296 ቢሊዮን ዶላር በመመደብ የሁለተኝነት ደረጃ እንደያዘች የተዘገበ ሲሆን፥ እንደ ጃፓንና ታይዋን ያሉ ጎረቤት አገሮች ደግሞ የመከላከያ በጀታቸውን ከበፊቱ ማጠናከራቸው ሪፖርቱ ያመላክታል።

ክልላዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች

በተቋሙ በተገለጹት በአምስቱ መልክአ ምድራዊ  ክልሎች ወታደራዊ በጀቶቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መምጣታቸውን ሲሆን፥ በአካባቢያቸው ባለው ውጥረት እና የጸጥታ ስጋቶች ምክንያት በአውሮፓ፣ እስያ፣ ኦሺኒያ እና መካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ ጭማሪዎች ታይተዋል።

በአውሮፓ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ እና ጀርመንን ጨምሮ የኔቶ አባላት ወታደራዊ በጀታቸውን ከፍ ያደረጉ ሲሆን፥ ይህም በሩሲያ በኩል ያለውን ክልላዊ አለመረጋጋትን ያሳያል ተብሏል።

በተለይም ሩሲያ ራሷ በሚያስደንቅ ሁኔታ ወታደራዊ ወጪዋን በ 24 በመቶ በማሳደግ 109 ቢሊዮን ዶላር የመደበች ሲሆን፥ ዩክሬን ግን ባላባራው ግጭት ውስጥ ሆና ወታደራዊ ወጪዋ 51 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ እና ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የወጪ ልዩነት ያጠባል ተብሏል።

እየጨመረ የመጣው ውጥረት

ረጅም ጊዜያትን ባስቆጠሩት ግጭቶች እና እየተባባሱ በመጡ ውጥረቶች ምክንያት ግጭት ውስጥ የሚገኘው መካከለኛው ምስራቅ በወታደራዊ ወጪ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱ የተጥቀሰ ሲሆን፥ በ2015 ዓ.ም. 200 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። በአስር ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው የሆነው ይህ ጭማሪ የክልሉን ተለዋዋጭ ሁኔታ የሚያሳይ እና በቁልፍ ተዋናዮች መካከል ያለውን ዘላቂ የጦር መሳሪያ ውድድር አጉልቶ አሳይቷል።

በተመሳሳይ መልኩ፣ መካከለኛው አሜሪካ እና ካሪቢያን ሃገራት ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ የ54 በመቶ የወታደራዊ ወጪን ያሳዩ ሲሆን፥ ይህም በዋነኝነት የወንጀል ደረጃዎች በመጨመራቸው እና የውስጥ ደህንነት ተግዳሮቶች በመባባሳቸው ነው ተብሏል።

በዚሁ ዓመት ህንድ በአለም አቀፍ ደረጃ አራተኛዋ ትልቅ ወታደራዊ ወጪ ያወጣች ሃገር ስትሆን፥ ይህም እያደገ ከመጣው ስትራቴጅያዊ ፍላጎቶቿ እና በክልላዊ የደህንነት ስጋቶች ምክንያት እንደሆነም ተገልጿል።

በተጨማሪም እንደ ዴሞክራሳዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ደቡብ ሱዳን ያሉ ሀገራት እየጨመሩ በመጡ የደህንነት ስጋቶች እና የውስጥ ግጭቶች ምክንያት ወታደራዊ ወጪያቸው በመቶኛ ከፍተኛ ጭማሪ አስመዝግበዋል።
 

23 April 2024, 15:25