ፈልግ

ሃሎ መተማመን የተሰኘው አለማቀፍ ድርጅት በአፍጋኒስታን ፈንጂ ሲያመክን ሃሎ መተማመን የተሰኘው አለማቀፍ ድርጅት በአፍጋኒስታን ፈንጂ ሲያመክን  

የተቀበሩ ፈንጂዎችን ማጽዳት መላውን ማህበረሰብ ሁሉ ይታደጋል ተባለ!

“ሃሎ መተማመን” (HALO Trust) የተሰኘው ዓለም አቀፍ ድርጅት የተቀበሩ ፈንጂዎችን እና በግጭቶች ወቅት ጥቅም ላይ ውለው እንደ ተቀበሩ የተረሱ ፈንጂዎችን ለማስወገድ እንዲሁም ማህበረሰቦችን በተቻለ መጠን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ህይወታቸውን እንዴት መገንባት እንደሚችሉ ለማስተማር ይሰራል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"በመሬት ውስጥ የሚቀበሩ ፈንጂዎች የጦር መሳሪያዎች ናቸው፣ እናም እነሱን ለማስወገድ “HALO Trust” የተሰኘው ድርጅት ይህንን ተግባር ያከናውናል”። ውስብስብ እና በመጨረሻም ኢሰብአዊ ለሆነ እውነታ የሚሰጥ ቀላል ምላሽ ነው። ግጭት ሲያበቃ ከኢኮኖሚና ከፖለቲካ ባለፈ ቅሪቶችን ጥሎ ያልፋል። በአንድ ወቅት የመላው ቤተሰብ እና ማህበረሰቦች መኖሪያ የነበሩ ሥፍራዎች የጦር ሜዳዎች ሆነው ሊገኙ ይችላሉ፣ ጦርነት ካበቃ በኋላ ወደ ኋላ ለመመለስ የሚሞክርን ሁሉ የሚያስፈራሩ ያልፈነዱ መሳሪያዎች በመሬት ሥር ተቀብረው እና ተደብቀው ይገኛሉ።

የሃሎ መተማመን

የሃሎ መተማመን ድርጅት በሰብአዊ ፍጡራን ላይ አደጋ እንዳይደርስ ለማድረግ ፈንጂዎችን በማምከን ላይ የተሰማራ ድርጅት ነው።  “ይህም ፈንጂዎችን እና ሌሎች ያልፈነዱ ተመሳሳይ የጦር መሣሪያዎችን በማፅዳት ግጭት ካበቃ በኋላ ወደ ኋላ ወደ ቀያቸው ለመመለስ የሚፈልጉ ሰዎችን ለመደገፍ የተቋቋመ ድርጅት ነው። አቶ ካሉም ፔብልስ አሁን ከሰላሳ በላይ አገሮች ውስጥ ለሚሠራው በሃሎ መተማመን ድርጅት የሚሠራ የመካከለኛው እስያ የክልል ኃላፊ ነው።

ለቫቲካን ዜና እንደተናገሩት እንደ አለመታደል ሆኖ "በመሬት ውስጥ የሚቀበሩ ፈንጂዎች ባሉባቸው አገሮች ሁሉ ላይ መቅሰፍት አለ" ብለዋል።

ቀድሞውንም አብቅቶ በነበረው ግጭት ንጹሐን ሰለባዎች

በዚምባብዌ፣ በካምቦዲያ፣ በአፍጋኒስታንም ሆነ በሌሎች ቦታዎች የሃሎ መተማመን ድርጅት  እንደ ክሊኒኮች እና ትምህርት ቤቶች ያሉ ቦታዎችን ለማፅዳት እንደሚሰራ እና እንደ ፈንጂ ያሉ ነገሮች መሬት ላይ የሚወድቁበትን እና "በመጨረሻም በወንዶች ፣ በሴቶች እና ሕጻናት ላይ ሞት በማስከተል ጉዳት ያደርሳሉ" ሲል ያስረዳል። በእዚህ በመሬት ውስጥ በተቀበሩ ፈንጂዎች የሚጎዱት በአብዛኛው ሕጻናት እንደ ሆኑ የተናገሩት ኃላፊው ይህ የሚሆንበት ምክንያት ደግሞ ሕጻናት ለጨዋታ በሚወጡበት ጊዜ ያልፈነዱ ፈንጂዎችን በሚረግጡበት ወቅት አደጋው እንደሚደርሳባቸው አክለው ገልጿል።

ፈንጂዎቹ በእርግጠኝነት በእነሱ ላይ ያነጣጠሩ አይደሉም ሲሉ ያብራራሉ፣ እነዚህ መሳሪያዎች በዋናነት በወታደራዊ አውድ ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላሉ ፣ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ “ሲቪሎች የሆኑ ወንዶች ፣ ሴቶች እና ሕፃናት ብዙውን ጊዜ የፈንጂ ሰለባ ይሆናሉ” ብለዋል ።

በአፍጋኒስታን ብቻ ባለፉት ሶስት አመታት 3,000 ሰላማዊ ዜጎችን በፈንጂ አደጋ ተገድለዋል። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ልጆች ናቸው ያሉት በሃሎ መተማመን ድርጅት የመካከለኛው እስያ የክልል ኃላፊ የሆኑት አቶ ካሉም ፔብልስ "እኛ የምናውቃቸው እነዚህ ብቻ ናቸው፣ ከእዚህ የባሰ ሊኖር ይችላል" ብሏል።

ወደ ቤት የመመለስ አደጋዎች

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በአገሪቱ ውስጥ ለመሰፈር እየሞከሩ ነው እና በሚሰፍሩባቸው አካባቢዎች የተቀበሩ ፈንጂዎችን ወይም ሌሎች ተመሳሳይ ያልፈነዱ ጥይቶች የጦርነት ቅሪት ያገኛሉ። ብዙ ጊዜ “እነዚህ ያልፈነዱ መሳሪያዎች በገጠር የሚኖሩትን ህዝብ እየጎዱ ነው” ሲሉ ኃላፊው አክለው ገልጿል።

በነዚህ ጉዳዮች ላይ ያለው ችግር አንድ ፈንጂ አንድ ግዙፍ መሬት የመጠቀም ችሎታዎን ሊገድበው ይችላል - ብዙውን ጊዜ እምቅ የእርሻ ቦታ - "ስለዚህ አንድ የተቀበረ ፈንጂ በመላ ቤተሰብ መተዳደሪያ ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል" ያሉት አቶ ካሉም ፔብልስ የሃሎ መተማመን ድርጅት ስራዎች "የምግብ እጦት በጣም የከፋ ስለሆነ ቤተሰቦች በምግብ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ ወይም ስጋት እንዳለ የሚያውቁትን መሬት የመጠቀም አደጋን በማስወገድ ቦታዎችን ከአደጋ ነጻ ማድረግ ነው” ሲሉ አክለው ገልጿል።

“በአፍጋኒስታን በምሠራበት ወይም በቅርቡ በሄድኩበት ቦታ፣ ሌላ አማራጭ ለሥራ የመቀጠር ዘዴ የሌላቸው ቤተሰቦች የቆሻሻ ብረታ ብረት የሚሰበስቡበት አሉታዊ የመቋቋሚያ ስትራቴጂ አለ፣ ያንንም በገንዘብ ይሸጣሉ። ነገር ግን ያ እንደ አፍጋኒስታን ባሉ ቦታዎች ላይ ያለው የተጣሉ ብረታብረቶች ያልፈነዱ ፈንጂዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ በጣም አደገኛ ነው። ስለዚህ የምናየው ሕጻናት እና ሴቶች ወደ ውጭ ወጥተው የተጣሉ ብረታብረቶችን  ሲሰበስቡ ነው ይህን ሲያደርጉም በዚህ ምክንያት ራሳቸውን እየጎዱ ወይም እየገደሉ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

በዚምባቡዌ  ልጆች ፈንጂ በሚገኝበት ቦታ አከባቢ ስያልፉ የምያሳይ ምስል
በዚምባቡዌ ልጆች ፈንጂ በሚገኝበት ቦታ አከባቢ ስያልፉ የምያሳይ ምስል

ማህበረሰቦችን ማስተማር

ስለዚህ፣ ሌላው የሃሎ መተማመን ስራ ጠቃሚ አካል ማስተማር እና ግንዛቤ መፍጠር ነው።

በብዙ አገሮች አቶ ካሉም ፔብልስ እንደ ተናገሩት “ልንቋቋመው የሚገባን የሥራው መጠን በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ ሁሉንም ነገር ማጽዳት አንችልም” በማለት ያብራራሉ። በዚህ ምክንያት ማህበረሰቦች ስለ ፈንጂ እቃዎች ስጋት እና አንድ የተወሰነ ነገር ከተገኘ ምን ማድረግ እንዳለባቸው መማር አለባቸው። “በአፍጋኒስታን ውስጥ፣ በማህበረሰቦች ውስጥ ላሉ ሌሎች ሴቶች ያንን ትምህርት የሚሰጡ ሴቶች አግኝተናል። የችግሩ ስፋት በጣም ትልቅ ስለሆነ ልንወስደው የሚገባ ወሳኝ እርምጃ ነው” ብለዋል።

በፍጋኒስታን የፈንጅ ማጽዳት ሥራ ሲከናወን የምያሳይ ምስል
በፍጋኒስታን የፈንጅ ማጽዳት ሥራ ሲከናወን የምያሳይ ምስል

የአካባቢ ሥራ ፈጠራ እና ስልጠና

በእርግጥ ቀጣዩ እርምጃ እነዚህን በምሬት ውስጥ የተቀበሩ ፈንጂዎችን ማምከን እና ለማጽዳት መሞከረ ነው። የሃሎ መተማመን ድርጅት ቡድኖች ከአለም አቀፍ እና ከክልላዊ ሰራተኞች የተዋቀሩ ናቸው። እኛ የምናደርገው የአካባቢ ማህበረሰቦችን ነው የምንቀጥረው። ምንም ዓይነት የስራ አማራጮች ለሌላቸው ግለሰቦች ስራ እንሰጣቸዋለን እና በመላው አለም እነዚያን በመሬት ውስጥ የተቀበሩትን ፍንጂዎች ማጽዳት እንዲችሉ እናሠለጥናቸዋለን። አቶ ካሉብ ፔብልስ አክለው እንደ ተናገሩት ከሆን የትኛውም የሰራተኛ አባል በፍፁም አደጋ ላይ እንደማይወድቅ እና ሁሉም ሰው ብዙውን ጊዜ ለክልሉ የተለየ እና ብዙ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣውን ስርዓት ለማጥራት ጥልቅ የስነ-ምግባር ስልጠና እንደሚወስድ አፅንዖት ሰጥው ተናግረዋል።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የድጋፍ ድምፅ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ በየካቲት 28/2024 ዓ.ም ባደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ላይ ያቀረቡት ጸሎቶች ወሳኝ በሆነ ጊዜው ውስጥ የቀረበ ጸሎት ነው። እ.አ.አ መጋቢት 1/2024 ዓ.ም የፀረ-ሰው ፈንጂ ክልከላ ስምምነት የተፈረመበት 25ኛ አመት የሚከበርበት እለት ነው።

አቶ ካሉብ ፔብልስ እንዳሉት ከሆነ “በታሪክ ውስጥ በጣም ስኬታማ ከሆኑት አንዱ” በማለት ገልጾታል ፊርማው “ወታደራዊ የሆኑ ፈንጂዎች ከማጥመድ ወደ ዛሬው የሃሎ መተማመን የሰብአዊ የፈንጅ ማምከን” ለውጥ መጀመሩን የሚያመለክት ነው።

በካምቦዲያ የፈንጅ ማምከን ሥራ ሲከናውን የምያሳይ ምስል
በካምቦዲያ የፈንጅ ማምከን ሥራ ሲከናውን የምያሳይ ምስል

ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ እና በተፈጥሮ ሰብአዊነት

የቅዱስ አባታችንን ድምጽ እንደ የድጋፍ ድምጽ በመጠቀም በመሬት ውስጥ የተቀበሩትን ፈንጆች የማጥራት ስራን እና ሕይወታቸውን ለዚህ ተግባር የወሰኑትን ሰዎች ሁሉ እንዲደግፉ ማድረግ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው። "ለ20 እና 30 ዓመታት ፈንጂዎችን በራሳቸው ማህበረሰብ ውስጥ ለማጽዳት ሲሰሩ የነበሩ ሰዎችን አይቻለሁ። ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ፣ እና በእጃቸው እና በጉልበታቸው ይህንን የፈንጅ ማጽዳት ሥራ የምያከናውኑ ሰዎች ለሚያደርጉት ጥረት ጸሎት እና ምስጋና ይገባቸዋል። ይህ ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ እና በተፈጥሮ ሰብአዊነት የተሞላ ተግባር ነው እና ሁሉንም የሃሎ መተማመን  ሰራተኞች እና ሌሎች በአለም ዙሪያ ለሰው ልጅ ጥቅም አደገኛ ስራ እየሰሩ ያሉትን ለማመስገን እወዳለሁ ካሉ በኋላ አቶ ካሉብ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 

01 March 2024, 11:33