ፈልግ

የፍልስጤም እና የእስራኤል ጦርነት የፍልስጤም እና የእስራኤል ጦርነት  (AFP or licensors)

በጋዛ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም የሚደረግ ጥረት መቀጠሉ ተገለጸ

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛ የሚካሄደውን ጦርነት እንዲቆም የሚጠይቅ ድምጽ መጭው ሐሙስ እንደሚሰጥ ታውቋል። በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛ የሚካሄደው ጦርነት እንዲቆም የሚያግዝ አዲስ ጥረት ማድረጉ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ዲፕሎማቶች አሜሪካ ድምጽን በድምጽ ለመሻር በሚያስችላት ውሎች ላይ ሲወያዩ በመቆየታቸው የተነሳ የድምጽ አሰጣጡ ሂደት በዚህ ሳምንት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ መዘገየቱ ታውቋል። የተባበሩት መንግሥታት በጋዛ የሚደረገውን የዕርዳታ አቅርቦት ለመከታተል የሚያግዝ የጽሑፍ ሃሳብ ሌላው ተጨማሪ የውይይት ነጥብ እንደ ሆነ ታውቋል።

ለጋዛ ሕዝብ ዕርዳታ እንዲደርስ በማለት ድምጿን ያቀረበችው የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፥ የፀጥታው ምክር ቤት የሚያደርገው ሙከራ እንዳይሳካ የሚያደርግ ብዙ ሕዝብ ስቃይ መኖሩን ገልጻለች። በሌላ አካባቢ በኢራን የሚታገዝ እና ሊባኖስ ውስጥ የሚገኝ የሂዝቦላህ ቡድን ከእስራኤል ጦር ጋር በድንበር አካባቢ ባደረገው ጦርነት በሰሜኑ የእስራኤል ከተሞች ላይ ሮኬቶችን መተኮሱን እስራኤል ተናግራለች።

የሊባኖስ ራዲዮ፥ የእስራኤል አየር ሃይል ከድንበር ብዙም በማይርቅ ደናማው አካባቢ የአየር ድብደባ መፈጸሟን ዘግቧል። ጋዛ ውስጥ ካን ዮኒስ አቅራቢያ ውጊያው የቀጠለ ሲሆን፥ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በጋዛ ውስጥ ከሐማስ አለቆች መኖሪያ ቤቶች ጋር የተገናኙ ዋሻዎችን ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።

ማክሰኞ ታኅሳስ 9/2016 ዓ. ም. የሐማስ መሪ ካይሮ ውስጥ ባደረጉት ውይይት፥ ሌላ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ እና እስረኞች እና ታጋቾችን ለመለዋወጥ ሃሳብ ማቅረባቸው ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ የሐማስ ታጣቂዎች መስከረም 26/2016 ዓ. ም. በእስራኤል ላይ ጥቃት ከፈጸመ በኋላ እስራኤል በጀመረችው ዘመቻ 20,000 ሰዎች መሞታቸውን ጋዛ ውስጥ በሐማስ የሚመራው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።

 

 

23 December 2023, 14:43