ፈልግ

በእስራኤል እና በፍልስጤም እስላማዊ ቡድን ሃማስ መካከል በተደረገው ስምምነት ታጋቾች ሲለቀቁ በእስራኤል እና በፍልስጤም እስላማዊ ቡድን ሃማስ መካከል በተደረገው ስምምነት ታጋቾች ሲለቀቁ 

ሃማስ ጠልፎ ከወሰዳቸው ውስጥ በርካታ ሙስሊሞችም እንደሚገኙ ተነገረ

መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም. የሐማስ ታጣቂዎች ወደ እስራኤል ገብተው ጥቃት ባደረሱበት ወቅት ታግተው ከተወሰዱት በርካታ የአረብ ሙስሊም ዝርያ ካላቸው (ቤዱዊን) ሰዎች መካከል የ16 ዓመቷ አይሻ ከአባቷ እና ከሁለት እህት ወንድሞቿ ጋር ይገኙበታል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የእስራኤል ፓስፖርት ያላት የ16 ዓመቷ የአረብ ሙስሊም የሆነችው አይሻ እስካሁን ዬት እንዳለች ለማወቅ አልተቻለም ተብሏል። እጅግ በጣም አስደንጋጭ በነበረው መስከረም 26 ቀን ጠዋት ላይ አይሻ ከወንድሞቿ ሀምዛ እና ቢላል ጋር በመሆን አባቷን የሱፍን እስከ ሥራ ቦታው ተከትላ ሄዳ ነበር። የሱፍ ሁሌ በማለዳው ከሚኖርበት በኔጌቭ ውስጥ የምትገኘውን የአረብ ሙስሊሞች ከተማ የሆነችውን ራሃትን ለቆ ሆሊት አከባቢ ወደሚገኝ የእስራኤላዊያን የእርሻ ቦታ ሥራ ለመስራት ይሄዳል።

በዚያን ቀን ጠዋት ሶስት ልጆቹን ይዞ ነበር ወደ ሥራ የሄደው። አራቱም በእርሻው ቦታ ላሞችን ኢያለቡ ነበር በአሸባሪው የሃማስ ታጣቂዎች የታገቱት። እንደ ቤዱዊን ባለስልጣናት ገለፃ ከሆነ ታፍነው የተወሰዱት የአረብ ሙስሊሞች ወይም ቤድዊኖች እነ አይሻ ብቻ አልነበሩም፥ በጋዛ ዙሪያ ባለው ኪቡዚም ውስጥ ይሠሩ የነበሩ ተጨማሪ ሰባት ሰዎችም ሊኖሩ እንደሚችሉ ተነግሯል።

በከባድ የስኳር ህመም የሚሰቃየው እና ከፍተኛ የኢንሱሊን ተጠቃሚ ለሆነው የሱፍ የደህንነት ስጋት እንዳለ ቢነገርም፥ የበለጠ አሳሳቢ የሆነው ግን የአይሻ ሁኔታ ነው። በአሁኑ ወቅት ታጋቾችን የመፍታት ሂደቱ ላይ ቅድሚያ እየተሰጠ ያለው ለልጃገረዶች እና ለወጣት ሴቶች ቢሆንም አይሻ ግን እስከ አሁን ድረስ አልታየችም።

የሚያሰጋው ነገር፥ ሃማስ ሙስሊሞችን እንደሚያፍን ወይም ከዚህ የከፋ እንደሚያረግ እና ተጠያቂው እሱ እንደሆነ እንዲሁም በእስራኤላዊያን እርሻ ላይ በመስራቱ ብቻ መላውን ቤተሰብ እንደ “ተባባሪ” ሊቆጥር ይችላል የሚለውን ክስ ሀማስ ከፍልስጤማዊያን አስተሳሰብ ለመደበቅ እየሞከረ እንደሆነም አንዳንድ ተንታኞች እየተናገሩ ይገኛል።

ከአይሻ እና ከቤተሰቦቿ ጋር በተያያዘ ታጋቾቹ በሀማስ ዋሻዎች ውስጥ መታሰራቸው እርግጠኛ መሆን ባይቻልም፥ ሀማስ ሙስሊሞችን ማፈኑን አምኖ ላለመቀበል መረጃዎችን ደብቆ ሊሆን ይችላል የሚል ፅንሰ-ሀሳብም በብዙዎች ዘንድ አለ።

በእስራኤል ውስጥ ወደ 220,000 የሚጠጉ የአረብ ሙስሊም ቤዱዊኖች እንዳሉና አብዛኛዎቹም በኔጌቭ በረሃ አካባቢ እንደሚኖሩ፣ የተቀሩት ሌሎች ቤዱዊኖች ደግሞ የሚኖሩት በሰሜን በገሊላ እና በጄዝሪል ሸለቆ መካከል ሲሆን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ በሚወስደው መንገድ በይሁዳ ውስጥ በቁጥር አነስ ያሉ የቤዱዊን ማኅበረሰቦች እንዳሉም መረጃዎች ያመላክታሉ።

ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ ቤዱዊኖች የእስራኤል ዜግነት ያላቸው ቢሆንም፥ የእስሬል መንግስት በበረሃ ውስጥ ይኖሩ የነበሩትን ብዙ ማህበረሰቦችን ወደ አዲስ ከፊል የከተማ ሰፈሮች ለማዛወር/ለማስፈር ባወጣው ዕቅድ ምክንያት በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከእስራኤል ጋር ያለው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሻከረ መምጣቱ ይነገራል።

ከእስራኤል ዲፕሎማቶች ውስጥ ብቸኛው ክርስቲያን የሆኑት በአዘርባጃን የእስራኤል አምባሳደር ጆርጅ ዴክ የወጣት አይሻ ጉዳይ እንዳሳሰባቸው በኤክስ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ገልፀዋል።

አምባሳደር ዴክ ለጣሊያን ዕለታዊ ጋዜጣ ለሆነው ለላ’ኦዘርቫቶሬ ሮማኖ ሲናገሩ “ከሌሎቹ ልጆች እና ወጣት ልጃገረዶች በተለየ ሁኔታ ሃማስ አይሻን እስከ አሁን ድረስ ያልለቀቀበት ምክንያት ሐማስ ሙስሊሞችንም እንደሚያፍን አምኖ መቀበል ስላሳፈረው እንደሆነ የሚያመላክት አንድ ማስረጃ ነው፥ ሀማስ በሰው ህይወት ላይ ያለው ንቀት ከሃይማኖታዊ አንድነት የበለጠ አስፈላጊ መሆኑን ስለሚያሳይ የእርሷ ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። ይህ አቤቱታ ለሀማስ ጆሮ ይደርስ ዘንድ፣ እንዲሁም ለእስራኤል እና ለመላው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይደርስ ዘንድ ለአይሻ ስል ታትሞ እንዲወጣ ወስኛለሁ። አይሻ ልክ እንደ ሁሉም እኩዮቿ በአስቸኳይ ወደ ቤቷ እንድትመለስ እንፈልጋለን” በማለት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

እንደ እሳቸውም ያለ እስራኤላዊ አለ፥ ክርስቲያን እስራኤላዊ ዲፕሎማት፥ በሙስሊም ጽንፈኞች ለታገተች ወጣት ሙስሊም ሴት የሚፋለም።
 

30 November 2023, 13:40