ፈልግ

አንድ የአከባቢው ነዋሪ በእስራኤል ደቡብ ጋዛ ሰርጥ በራፋህ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ በተጎዳ መንገድ ላይ መኪና እየነዳ አንድ የአከባቢው ነዋሪ በእስራኤል ደቡብ ጋዛ ሰርጥ በራፋህ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ በተጎዳ መንገድ ላይ መኪና እየነዳ  (AFP or licensors)

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በራፋህ መሻገሪያ በኩል ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ መደረጉን አወደሱ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በራፋ መሻገሪያ በኩል የመጀመሪያዎቹ ሲቪሎች ጋዛን ለቀው ወደ ግብፅ እንዲገቡ ያስቻለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አድንቀዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በራፋ መሻገሪያ በኩል የመጀመሪያዎቹ ሲቪሎች ጋዛን ለቀው ወደ ግብፅ እንዲገቡ የተደረገውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አድንቀዋል።

ማቋረጫው ረቡዕ ዕለት በከፊል ተከፍቷል

ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ባይደን በተለይ ኳታር በድርድሩ ላይ ላደረገችው ድጋፍ አመስግነዋል።
ጥቅምት 22, 2016 ዓ.ም. ሐሙስ ዕለት ተጨማሪ ሲቪሎች በራፋህ መሻገሪያ በኩል ጋዛን ለቀው እንደወጡ ተዘግበዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረቡዕ ዕለት ከ400 በላይ ሰዎች በማቋረጫው ድንበር ለቀው እንደወጡ አሳውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ጦር ወታደሮቿ ወደ ጋዛ ሰርጥ ዘልቀው መግባታቸውን ገልፃለች። አንድ የእስራኤል ጦር ሃይሎች አዛዥ እንደተናገሩት 'እስካሁን የእስራኤል ጦር በጋዛ ከተማ ድንበር ላይ ነበሩ' ብለዋል። አሁን ግን ከምድር፣ ከባህር እና ከአየር ሃይል የተውጣጡ ወታደሮች በሰሜን ጋዛ የሚገኘውን የሃማስ መከላከያ መስመር ሰብረው መግባታቸው ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰዓት የምድር ላይ ውግያው በሰሜናዊ የጋዛ ሰርጥ አከባቢ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል አምስት ዋና ዋና ጦርነቶች እየተደረጉ ናቸው ተብሏል።

ይህ በእንዲህ እያለ የእስራኤል የቦምብ ጥቃት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 9,000 ሰዎች መሞታቸውን በጋዛ የሚገኘው የሃማስ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገልጿል።
 

02 November 2023, 15:19