ፈልግ

COP28፡ የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤዎች አጠቃላይ እይታ! COP28፡ የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤዎች አጠቃላይ እይታ!  (AFP or licensors)

COP28፡ የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤዎች አጠቃላይ እይታ!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) አመታዊ የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ ‘የፓርቲዎች ኮንፈረንስ’ ወይም ‘COP28’ በመባል የሚታወቀው የአየር ንብረት ለውጥን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል የአለም መሪዎችን፣ ሚኒስትሮችን እና ተደራዳሪዎችን ያሰባስባል። ተደራዳሪዎቹ የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ማዕቀፍ (UNFCCC)፣ የኪዮቶ ፕሮቶኮል እና/ወይም የፓሪስ ስምምነትን የፈረሙ መንግስታትን ያጠቃልላል። በሲቪል ማህበረሰብ፣ በግሉ ዘርፍ፣ በአለም አቀፍ ድርጅቶች እና በመገናኛ ብዙሃን በሺዎች የሚቆጠሩ ተወካዮች የሚሳተፉበት ኮንፈረንስ ነው።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

COP (የፓርቲዎች ኮንፈረንስ) እ.አ.አ በ1992 በተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ እና የልማት ኮንፈረንስ (UNCED) የፀደቀው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት (UNFCCC) ከፍተኛ ውሳኔ ሰጪ አካል ነው ፣ “የምድር ጉባኤ” በመባል ይታወቃል ፣ በሪዮ ዴ ጄኔሮ (ብራዚል) የተካሄደው እ.አ.አ በ1990 በይነ መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ፓነል (IPCC) ከወጣው የመጀመሪያ ግምገማ ሪፖርት በኋላ ብዙም ሳይቆይ ይፋ የሆነ ነበር።

ይህ ኮንፈረንስ ባለፉት አሥርተ ዓመታት ውስጥ በአየር ንብረት ሳይንስ እውቀት ላይ በየጊዜው፣ ሁሉን አቀፍ እና ሥልጣናዊ ሳይንሳዊ ግምገማዎችን ለፖሊሲ አውጪዎች የሚያቀርብ ሲሆን በተለይም በአየር ንብረት ለውጥ እና በሰው ልጆች እንቅስቃሴ መካከል ባለው ትስስር በሺዎች የሚቆጠሩ ሥራዎችን በማጎልበት የዓለም መሪ የአየር ንብረት ሳይንቲስቶችን ያካተተ ነው። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሳይንቲስቶች በብዛት እና በጥልቀት የሚሳተፉበት ኮንፈረንስ ነው።

የመጀመርያውን የበይነ መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ፓነል ሪፖርት መሠረት በማድረግ እ.አ.አ የ1992 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስምምነት “የሰው ልጅ በአየር ንብረት ሥርዓት ላይ የሚያደርሰውን አደገኛ ጣልቃገብነት” ለመዋጋት በከፊል በከባቢ አየር ውስጥ ያለውን የግሪንሀውስ ጋዝ ክምችትን በማረጋጋት ዓለም አቀፍ የአካባቢ ስምምነትን አቋቁሟል፣ ምንም እንኳ የስምምነቱ ፈራሚዎች የባካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ አስገዳጅ እና የጊዜ ሰሌዳ ባያስቀምጡም አዋጭ የሆኑ አስተያየቶችን ግን አቅርበው ነበር። ይህን ለማድረግ ምንም ዓይነት ዒላማዎችን ወይም የጊዜ ሰሌዳዎችን ግን አላስቀመጡም።  ሆኖም ከላይ የተገለጹት የፓርቲዎች ጉባኤዎች በመባል የሚታወቁት ተሳታፊዎች አጽድቀው የነበረ ሲሆን በፓርቲዎች መካከል ተደጋጋሚ ስብሰባዎችን ማድረግ አስፈልጎ ነበር።

ስምምነቱ በመጀመርያ የተፈረመው በ154 አገሮች ነበር። እ.አ.አ ከ 2023 ዓ.ም ድረስ በ198 አገሮች ጸድቋል።

እ.ኤ.አ. በ 1994 ሥራ ላይ ከዋለ ጀምሮ UNFCCC ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ድርድር መሠረት ጥሏል። እ.ኤ.አ. ከ 1995 ጀምሮ የመጀመርያው COP1 በበርሊን (ጀርመን) ሲካሄድ ፣ ፓርቲዎች በየአመቱ የሚያስመዘግቡትን መሻሻልን ለመለካት እና ለአየር ንብረት ለውጥ ሁለገብ ምላሾችን በመስጠት ለመደራደር መሰብሰብ ጀመሩ።

ሁለት ጉልህ ስምምነቶች

ድርድሩ ሁለት ጉልህ ስምምነቶችን አስገኝቷል፡- የኪዮቶ ፕሮቶኮል (እ.አ.አ 1997) የበለፀጉ አገሮች የበካይ ጋዝ ልቀትን እንዲቀንሱ የሚያስገድድ እና የፓሪስ ስምምነት (እ.አ.አ 2015) ከ25 ዓመታት ከባድ ድርድር በኋላ 196 ፓርቲዎች የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ ቃል ገብተዋል። በማደግ ላይ ያሉ ሀገሮች እንዲረዱ የተጠናከረ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባም ከውሳኔ ላይ ተደርሶ ነበር።

ዋና አላማው በዚህ ምዕተ አመት የአለም ሙቀት መጨመር ከኢንዱስትሪ በፊት ከ 2 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በታች ከፍ እንዲል በማድረግ ለአየር ንብረት ለውጥ ስጋት የሚሰጠውን አለም አቀፋዊ ምላሽ ማጠናከር እና የሙቀት መጠኑን ወደ 1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ለመገደብ የሚደርጉትን ጥረቶችን መከተል እና መደገፍ ነበር።

ምንም እንኳን ዩናይትድ ስቴትስ ስምምነቱን የፈረመች ቢሆንም፣ የትራምፕ አስተዳደር እ.ኤ.አ. በ 2017 ከስምምነቱ ወጥቶ የነበረ ሲሆን አሁን ያለት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከተመረጡ በኋላ እ.አ.አ በ 2021 አሜሪካ እንደገና ወደ ስምምነቱ ተመልሳ እንድትገባ አስችለዋል። ይሁን እንጂ የፓሪሱ ስምምነት ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ በአፈፃፀሙ ሂደት ማለትም ልቀትን በመቀነስ ረገድ አዝጋሚ ለውጦች ታይተው ነበር።

ሌላው ትልቅ ስኬት የመጣው ከ COP -27 በሻርም ኤል ሼክ እ.ኤ.አ. 2022 የተካሄደው ጉባሄ ሲሆን ይህም ከፍተኛ የሙቀት ሞገዶች፣ በረሃማነት፣ የደን ቃጠሎ፣ የሰብል ውድመቶች ወዘተ....በአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ በእነዚህ አውዶች ዙሪያ እየተከሰቱ የሚገኙትን አሉታዊ ውጤቶች ተመልክቶ እና ገምጎሞ የመሳተካከያ ሐሳቦችን አቅርቦ የነበረ ሲሆን በተለይም ለድሃ አገራት የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ ሐሳብ አቅርቦ ነበር።

የገንዘብ ድጋፉ ተጋላጭ የሆኑ ሀገራት አስፈላጊውን አካላዊ እና ማህበራዊ መሠረተ ልማት እንዲገነቡ ያግዛል። ፈንዱ ያለ ጥርጥር ታሪካዊ እመርታ ቢሆንም፣ ስኬቱ በአብዛኛው የተመካው አገሮች ገንዘቡን በምን ያህል ፍጥነት ማሰባሰብ እና ማስኬድ በሚችሉበት መንገድ ላይ ነው የተመረኮዘው።

እ.አ.አ ከህዳር 30 እስከ ታህሣሥ 12 ቀን 2023 በዱባይ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የሚካሄደው COP-28 በፓሪስ ተደርጎ በነበረው ስምምነት ላይ የመጀመርያውን ዓለም አቀፍ ግምገማ ያካሂዳል። የቅሪተ አካል ነዳጆች ጥያቄ በድጋሚ የውይይት መነሻ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

የጊዜ ሰሌዳ

እ.አ.አ 1992-1994 - ፈር ቀዳጅ የሪዮ ምድር ስብሰባ እና UNFCCC

ጉባኤው በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ከተደረጉት የመጀመርያዎቹ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መካከል አንዳንዶቹን ያስመዘገበ ሲሆን ይህም ለወደፊቱ ስምምነቶች መሰረት ይሆናል። ከእነዚህም መካከል የአየር ንብረት ለውጥን የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ስምምነት (UNFCCC) በአየር ንብረት ስርዓት ውስጥ “አደገኛ” የሰው ልጅ ጣልቃ ገብነትን ለመከላከል ያለመ፣ የሰው ልጅ እንቅስቃሴ ለአየር ንብረት ለውጥ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አምኖ እና የአየር ንብረት ለውጥ የአለም አሳሳቢ ጉዳይ እንደሆነ ይገነዘባል። እ.ኤ.አ. በ 1994 ሥራ ላይ የዋለ የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ስምምነት ፈራሚዎችን በህጋዊ መንገድ የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ አያስገድድም እና ይህንን ለማድረግ ያለመ ኢላማ ሆነ የጊዜ ሰሌዳ አያስቀምጥም። ነገር ግን የፓርቲዎች ኮንፈረንስ ወይም COP በመባል በሚታወቁት ባፀደቁ አገሮች መካከል ተደጋጋሚ ስብሰባዎችን ይጠይቃል። እ.አ.አ እስከ 2023 ድረስ በ 198 አገሮች ጸድቋል።

እ.አ.አ 1995 - በበርሊን የ UNFCCC ፈራሚዎች የመጀመሪያ ስብሰባ (COP1)

የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ስምምነት ፈራሚዎች ለመጀመሪያው የፓርቲዎች ኮንፈረንስ ወይም COP1 በበርሊን ተሰብስበው የነበረ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ በሕጋዊ አስገዳጅ ኢላማዎች እና የጊዜ ሰሌዳዎች ላይ ወደኋላ ማፈግፈጓ የሚታወስ ነው፣ ነገር ግን የግሪንሀውስ ጋዞችን በመገደብ ላይ ያሉትን ቁርጠኝነት ለማጠናከር ከሌሎች ወገኖች ጋር በመስማማት ድርድር ውስጥ ትቀላቀላለች። የበርሊን ተልዕኮ በመባል የሚታወቀው የማጠቃለያ ሰነዱ የኪዮቶ ፕሮቶኮል ለሚሆነው ነገር መሰረት የሚጥል ቢሆንም በአፋጣኝ እርምጃ የማይወስድ ፖለቲካዊ መፍትሄ ነው ሲሉ በአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች ተተችቶ ነበር።

እ.ኤ.አ. በ1997 የኪዮቶ ፕሮቶኮል የመጀመሪያ በህጋዊ መንገድ በ COP23 የፀደቀው የአየር ንብረት ስምምነት

በጃፓን እ.አ.አ በ1997 ዓ.ም የተካሄደው የCOP3 ጉባኤ የኪዮቶ ፕሮቶኮልን ተቀብሏል፥ በህጋዊ መንገድ የሚያዘውን ስምምነት ያደረጉ ሀገራት እ.አ.አ ከ1990 ደረጃ በታች በአማካይ 5 በመቶ ልቀትን እንዲቀንሱ እና የአገሮችን ግስጋሴ የሚቆጣጠርበትን ስርዓት ዘርግቷል። ነገር ግን ፕሮቶኮሉ ከፍተኛ የካርበን ልቀት ያላቸውን ቻይና እና ህንድን ጨምሮ ታዳጊ ሀገራት እርምጃ እንዲወስዱ አያስገድዳቸውም። በተጨማሪም “cap and trade” (ካፕ-እና-ንግድ ሥርዓት ውስጥ ማለት መንግሥት የልቀት መጠን ገደብ ያስቀምጣል፣ እናም ከዚያ ካፕ ጋር የሚስማማ የልቀት አበል መጠን ይከፍላል። አመንጪዎች ለሚለቁት ለእያንዳንዱ ቶን የሙቀት አማቂ ጋዝ አበል ሊከፈላቸው ይገባል የሚል ሥርዓት ነው። ኩባንያዎች አበል ሊገዙ እና ሊሸጡ ይችላሉ እናም ይህ ገበያ የልቀት ዋጋን ያስቀምጣል) በመባል የሚታወቀውን ስርዓት ለሀገሮች የካርቦን ገበያ የልቀት ክፍሎችን ለመገበያየት እና ዘላቂ ልማትን ለማበረታታት ያስችላል። ሀገራት ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ እና የማጽደቅ ዝርዝር ጉዳዮችን አሁን መስራት አለባቸው ሲል መደንገጉ ይታወሳል።

እ.አ.አ 2001 - በቦን ውስጥ የተካሄደው ፈር ቀዳጅ ጉባኤ

የኪዮቶ ስምምነት እ.አ.አ በኅዳር 2000 ዓ.ም የተደረጉት ንግግሮች አደጋ ላይ ከወደቁ በኋላ እና ዩናይትድ ስቴትስ እ.አ.አ በመጋቢት 2001 ዓ.ም ስምምነቱን ለቃ ስትወጣ ዋሽንግተን (በፔትሮሊየም ሎቢዎች ግፊት) ፕሮቶኮሉ ለአገሪቱ "ኢኮኖሚያዊ ጥቅም" አይሰጥም ስትል ተናግራ ይህንን እንደ ችግር በማቅረብ ከስምምነቱ ራሷን አግላል ነበር። እ.ኤ.አ. በሐምሌ 2001 ዓ.ም በቦን ጀርመን ውስጥ ተደራዳሪዎች በአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ፣ በልቀቶች ግብይት ላይ የተደረጉ ስምምነቶች እና የካርበን ዝቃጮች (የተፈጥሮ ማጠራቀሚያዎች ከሚለቁት የበለጠ ካርቦን የሚወስዱ) ላይ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። በጥቅምት ወር አገሮች በኪዮቶ ፕሮቶኮል የተቀመጡ ግቦችን ለማሟላት በሚወጣው ደንብ ላይ ይስማማሉ፣ ይህም ወደ ሥራ ለመግባት መንገድ ይከፍታል።

2005 - የኪዮቶ ፕሮቶኮል ተግባራዊ ሆነ

የኪዮቶ ፕሮቶኮል ቢያንስ 55 በመቶውን የአለም በካይ ጋዝ ልቀትን የሚይዝ በበቂ ሀገራት ከፀደቀ በኋላ በየካቲት ወር ተግባራዊ ሆኖ ነበር። በተለይም በዓለም ላይ ግንባር ቀደም የካርበን አመንጪ የሆነውችውን ዩናይትድ ስቴትስን አያካትትም። እ.ኤ.አ. በ 2008 እና በ 2012 መካከል ፣ ፕሮቶኮሉ ያበቃ ሲሆን ፣ አገሮች በገቡት የገንዘብ መጠን ልቀት መቀነስ አለባቸው-የአውሮፓ ህብረት እ.አ.አ ከ1990 ስምምነት በታች 8 በመቶ ልቀትን ለመቀነስ ወስኗል ፣ ጃፓን 5 በመቶ ማድረጓን እና ሩሲያ ደረጃውን ለመጠበቅ ቆርጣ ነበር። እ.አ.አ ከ1990 ደረጃዎች ጋር ቋሚ የሆነ የልቀት መጠን እንዲኖርም ወስና ነበር።

እ.አ.አ 2007 - ለኪዮቶ 2.0 ድርድር ተጀመረ

በባሊ ኢንዶኔዥያ ከ COP13 በፊት የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ፓነል (IPCC) አዲስ ጠንከር ያለ ቃል ያለው ሪፖርት አወጣ ፣አሁንም የአለም ሙቀት መጨመር በሰው ልጆች እንቅስቃሴ “በጣም ሊከሰት የሚችል” መሆኑን ያረጋግጣል። በኮንፈረንሱ ወቅት የኪዮቶ ፕሮቶኮልን ጠንካራ ተተኪ በሚመለከት ውይይት ተጀምሮ ነበር። ነገር ግን ሁሉም በኢንዱስትሪ የበለጸጉ ሀገራት የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀትን በልዩ ዒላማዎች እንዲቀንሱ የሚጠይቅ ሰፊ የተደገፈ ሀሳብ ዩናይትድ ስቴትስ ከተቃወመች በኋላ ቆመዋል። የአሜሪካ ባለስልጣናት ታዳጊ ሀገራትም ቃል መግባት አለባቸው ሲሉ ይከራከራሉ። ዋሽንግተን በመጨረሻ ወደኋላ ትመለሳለች እና ተዋዋይ ወገኖቹ እ.አ.አ በ 2009 አዲስ የአየር ንብረት ስምምነትን የማዘጋጀት ግቡን የሚያወጣውን የባሊ የድርጊት መርሃ ግብር ተቀበሉ ።

እ.አ.አ የመስከረም 2009 - አሜሪካ ደፋር መግለጫዎችን በማውጣት የተባበሩ መንግሥታትን ተቀላቀለች  

አዲስ ስምምነት ሊደረስበት ከታቀደው ከሶስት ወራት በፊት በርካታ የአለም መሪዎች በወቅቱ የተባበሩት መንግሥታ ድርጅት ዋና ፀሃፊ በነበሩት ባን ኪሙን በተዘጋጀው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ ቃል ገብተው ነበር። የቻይናው ፕሬዝዳንት ሁ ጂንታዎ እ.አ.አ በ2020 ልቀትን በ"ዓብይ ህዳግ" ለመቀነስ ማቀዱን አስታውቀው ነበር። ይህም ቤጂንግ የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀት መጠንን ለመቀነስ ለመጀመሪያ ጊዜ ስምምነት ስታደርግ የሚያሳይ ነበር። በወቅቱ የነበሩት የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዩኪዮ ሃቶያማ በ25 በመቶ የልቀት መጠንን ለመቀነስ ቃል ገብተዋል። በወቅቱ የአሜሪካ አዲስ የተመረጡት ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በተባበሩት መንግሥታት የመጀመርያ ንግግራቸው ዩናይትድ ስቴትስ እርምጃ ለመውሰድ እና ጉዳዩን ለመምራት ቆርጣለች ሲሉ የተናገሩ ሲሆን  ነገር ግን ምንም አዲስ ሀሳብ አላቀረቡም ነበር። በወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የነበሩት ባንኮሙን  መሪዎች በኮፐንሃገን በሚካሄደው ኮንፈረንስ ላይ "ተጨባጭ ስምምነት" ላይ እንደሚደርሱ ያላቸውን ተስፋ ገልጸው ነበር።

እ.አ.አ በኅዳር 2009 - በኮፐንሃገን (ዴንማርክ) በ COP15 ላይ የደረሰው ቅሬታ

የኪዮቶ ፕሮቶኮል ተተኪ በኮፐንሃገን ውስጥ በ COP15 ይጠናቀቃል ተብሎ ይታሰብ ነበር፣ ነገር ግን ተዋዋይ ወገኖቹ አስገዳጅ ያልሆነ ሰነድ ይዘው የሚመጡት “ራሳቸው ያሰናዱት ሰነድ” ተቀባይነት ያለው ነው የሚል አመለካከት ነበራቸው። የኮፐንሃገን ስምምነት የአለም ሙቀት በ2°ሴ (3.6°F) ከቅድመ-ኢንዱስትሪ ደረጃ በላይ መጨመር እንደሌለበት አምኗል፣ ምንም እንኳን በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ተወካዮች 1.5°C (2.7°F) እንዲቀንስ ፈልገው የነበረ ቢሆንም። (እ.አ.አ የ2009 የአሜሪካ የአየር ንብረት ጸባይ ተቆጣጣሪ ‘ሜትሮሎጂ’ ማሕበር ዘገባ ከአንድ መቶ አመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከ3.5°ሴ (6.3°F) እስከ 7.4°C [13.3°F] እንደሚጨምር ይተነብያል)። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ድርድሩን ከመሩ በኋላ ስምምነቱ “በቂ አይደለም” ሲሉ ለጉባኤው ገልጸው የነበረ ሲሆን አንዳንድ አገሮች በኋላ ላይ ውሉን ለመከተል ቃል ገብተዋል - ምንም እንኳን አስገዳጅ ባይሆንም ጉዳዩን ለማስፈጸም የራሳቸውን ቃል ገብተዋል።

እ.አ.አ የ 2010 የሙቀት መቀነስ ዒላማ በ COP16 በካንኩን (ሜክሲኮ)

በኮፐንሃገን ውድቀት እና ናሳ እ.አ.አ ከ2000-2009 ከተመዘገቡት በጣም ሞቃታማ አስርት አመታት በኋላ በ COP16 ወቅት በሜክሲኮ መግባባት ላይ ለመድረስ ከፍተኛ ጫና ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን ሀገራት በካንኩን ስምምነቶች ውስጥ የአለም ሙቀት ከ 2 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በታች እንዲጨምር ለመጀመሪያ ጊዜ ቃል ገብተው ነበር። በግምት ወደ ሰማንያ የሚጠጉ ሀገራት፣ ቻይና፣ ህንድ እና አሜሪካ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት የልቀት ቅነሳ ኢላማዎችን እና እርምጃዎችን ያቀረቡ ሲሆን እናም እድገትን ለመከታተል በጠንካራ ስልቶች ላይ ተስማምተው ነበር። ነገር ግን ተንታኞች ከ 2 ° ሴልሽዬስ ዲግሪ ዒላማ በታች ለመቆየት በቂ አይደለም ይላሉ። ታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል እና በመላመድ ረገድ የ100 ቢሊየን ዶላር ፈንድ የተሰኘው አረንጓዴ የአየር ንብረት ፈንድ ተቋቁሟል። እ.ኤ.አ. በ2019 ወደ 3 ቢሊዮን ዶላር ብቻ አስተዋጽዖ ተደርጓል።

እ.አ.አ 2011- አዲስ ስምምነት በ COP17 ለሁሉም አገሮች የሚተገበር

በደርባን ደቡብ አፍሪካ የተካሄደው ኮንፈረንስ በዓለም ላይ ሦስቱ ታላላቅ የአየር ንብረት በካይ አገራት -ቻይና፣ ህንድ እና ዩናይትድ ስቴትስ በአውሮፓ ህብረት የቀረበውን ስምምነት ውድቅ ካደረጉ ከማድረጋቸው በፊት  ሊሳካ ተቃርቦ ነበር። ነገር ግን በመጨረሻ እ.አ.አ በ2015 አዲስ ህጋዊ አስገዳጅ ስምምነት ለማርቀቅ ለመስራት ተስማምተዋል። አዲሱ ስምምነት ከኪዮቶ ፕሮቶኮል የሚለየው ባደጉትም ሆነ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ላይ ተግባራዊ ይሆናል። የኪዮቶ ፕሮቶኮል በጥቂት ወራት ውስጥ ጊዜው የሚያበቃ ሲሆን የስምምነቱ ፈጻሚ ወገኖች እስከ እ.አ.አ 2017 ድረስ ለማራዘም ተስማምተው ተለያይተው ነበር።

እ.አ.አ 2012 - በዶሃ በ COP 18 ምንም ዓይነት ስምምነት አለትደረገም ነበር።

በዶሃ ለ COP18 ተደራዳሪዎች የኪዮቶ ፕሮቶኮሉን እስከ እ.አ.አ 2020 እንዲራዘም ተስማምተው ነበር፣ የተቀሩት ተሳታፊዎች ግን 15 በመቶውን የአለም ሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀትን የምያስከስቱ ናቸው። በዚህ ጊዜ ካናዳ ከስምምነቱ ወጥታለች፣ ጃፓንና ሩሲያ ደግሞ አዲስ ቃል ኪዳኖችን አንቀበልም ብለው ነበር። (ዩናይትድ ስቴትስ ፈጽሞ አልፈረመችም) የአካባቢ ጥበቃ ቡድኖች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰተውን አስከፊ የአየር ሁኔታ መጨመሩን የሚያሳይ አውሎ ንፋስ ቦፋ ፊሊፒንስን በመታበት ወቅት ውጤታማ ስምምነት ላይ አለመድረሳቸው ብዙዎችን አበሳጭቶ ነበር። ከኮንፈረንሱ ስኬት አንዱ የዶሃ ማሻሻያ ሲሆን ያደጉ ሀገራት ታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ተፅእኖ ለመቀነስ እና ለውጡን እንዲለማመዱ ለመርዳት የተስማሙበት ነበር። የስምምነቱ ልዑካን ወደ አዲስ ስምምነት በሚወስደው መንገድ ላይም ያስቀምጣል።

እ.አ.አ 2013 - የ G77 መሪ ተደራዳሪዎች በዋርሶ (ፖላንድ) በ COP19 ረግጠው ወጥተዋል

 

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የሚገኘው ቡድን 77 (G77) የአባላቱን የጋራ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማስተዋወቅ እና በተባበሩት መንግስታት የተሻሻለ የጋራ የመደራደር አቅም ለመፍጠር የተነደፈ የ135 ታዳጊ ሀገራት ጥምረት ነው።

በፖላንድ በተደረገው በ COP19 የመጀመሪያ ሳምንት የታዳጊ ሀገራት (G77) ቡድን እና ቻይና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርሰውን “ኪሳራ እና ጉዳት” ለመቋቋም የሚረዳ አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ዘዴ አቅርበዋል። ያደጉ አገሮች ስልቱን ስለሚቃወሙ የG77 መሪ ተደራዳሪዎች ከጉባኤው ረግጠው መውጣታቸው ይታወሳል። ንግግሮች በመጨረሻ እንደገና ይቀጥላሉ፣ እናም መንግስታት በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ከሚፈልጉት በታች የሆነ ዘዴን ተስማምተዋል። በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል 'REDD' በመባል በሚታወቀውና (በታዳጊ አገሮች ውስጥ ያለውን የደን መጨፍጨፍ እና የደን መራቆትን ልቀትን ለመቀነስ የሚሰራው ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥን የሚከላከሉ ተጨማሪ ከደን ጋር የተገናኙ ተግባራትን ማለትም የደን ዘላቂ አያያዝ እና የደን የካርበን ክምችቶችን መጠበቅ እና ማሻሻልን ያመለክታል) አገሮች በመባል የሚታወቀውን የደን ጭፍጨፋ ለማስቆም እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚችሉ ላይ ተስማምተዋል ነገር ግን ጉባኤው በተንታኞች "በበርካታ አመታት ውስጥ እጅግ በጣም አነስተኛ የሆነ COP" ጉባኤ ተብሎ ይገለጻል።

እ.አ.አ 2015 - ፈር ቀዳጅ የሆነ የፓሪስ ስምምነት ተደረሰ

196 ሀገራት የፓሪስ ስምምነት ተብሎ በሚጠራው በታሪክ ውስጥ እጅግ በጣም አስፈላጊው የአለም የአየር ንብረት ስምምነት ተብሎ በሚጠራው ጉባኤ ላይ ስምምነት ላይ ይደርሳሉ። ካለፉት ስምምነቶች በተለየ፣ የልቀት ቅነሳ ግቦችን ለማዘጋጀት ሁሉም ማለት ይቻላል - ያደጉ እና በማደግ ላይ ያሉ አገሮችን ይፈልጋሉ። ነገር ግን አገሮች የራሳቸውን ኢላማ መምረጥ ይችላሉ፣ እናም እነሱን ሟሟላታቸውን ለማረጋገጥ ምንም ዓይነት የማስፈጸሚያ ዘዴዎች የሉም። በስምምነቱ መሰረት ሀገራት በአገር አቀፍ ደረጃ የሚወሰኑ መዋጮዎች (NDCs) በመባል የሚታወቁ ኢላማዎችን ማቅረብ አለባቸው። እ.አ.አ በኅዳር 2016 ስራ ላይ የሚውለው የፓሪሱ ስምምነት ተልዕኮ የአለም ሙቀት መጨመርን ከ 2 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በታች ማድረግ እና ከ 1.5 ° ሴንቲግሬድ በታች ለማድረግ ጥረቶችን መከታተል ነበር። ነገር ግን ተንታኞች ይህንን ግብ ለማሳካት ተጨማሪ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ያሳስባሉ። እ.ኤ.አ. በ 2017 ፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ. ትራምፕ በሀገሪቱ ላይ "ከባድ የገንዘብ እና ኢኮኖሚያዊ ሸክሞችን" እንደሚጥል በመግለጽ ዩናይትድ ስቴትስን ከስምምነቱ አስወጡ ።

አ.አ.አ 2018 - የፓሪስ ስምምነት ደንቦች ተወስነዋል

በፖላንድ ካቶቪስ ከ COP24 ቀደም ብሎ የወጣ አዲስ የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ፓነል  ሪፖርት ጠንከር ያለ አውሎ ንፋስ እና አደገኛ የሙቀት ሞገዶችን ጨምሮ አስከፊ መዘዞችን እንደሚመጡ ያስጠነቅቃል -የአለም አማካይ የሙቀት መጠን ከቅድመ-ኢንዱስትሪ ደረጃ በ1.5°ሴልሽዬስ ከፍ ካለ እና በ2030 ወደዚያ ደረጃ ሊደርስ እንደሚችል ይተነብያል። ሪፖርቱ አገሮች ጠንካራ ኢላማዎችን ለመምታት ስምምነት ላይ እንዳልደረሱ ይናገራል። ነገር ግን አገሮች የበካይ ጋዝ ልቀታቸውን እንዴት ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸው ጨምሮ ጥያቄዎችን በሚሸፍነው የፓሪስ ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ ሕጎች ላይ በስፋት ተስማምተዋል። በካርቦን ንግድ ደንቦች ላይ ግን አይስማሙም፣ እናም ያንን ውይይት ወደ እ.አ.አ 2019 እንዲዛወር አደረጉት።

እ.አ.አ በመስከረም 2019- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃ ጉባኤ አቅዶ ነበር

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት እርምጃ ስብሰባ በኒውዮርክ ለአለም መሪዎች አዘጋጅተው የነበረ ሲሆን ሀገራት በፓሪስ ስምምነት የተሻሻሉ በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል “NDCs” Nationally Determined Contributions (በአገር አቀፍ ደረጃ የተወሰነ አስተዋፅዖ ወይም በፓሪስ ስምምነት መሠረት አገሮች በራሳቸው የሚገለጹ ብሔራዊ የአየር ንብረት ቃል ኪዳኖች ሲሆኑ፣ ዓለም አቀፉን 1.5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ለማድረስ፣ ከአየር ንብረት ተጽእኖዎች ጋር መላመድ እና እነዚህን ጥረቶች ለመደገፍ የሚያስችል በቂ ፋይናንስ ለማረጋገጥ ምን እንደሚያደርጉ በዝርዝር የሚያቀርብ ስምምነት ነው) በሚቀጥለው አመት እንዲያቀርቡ ታዘው ነበር፣ ስለዚህ ስብሰባው መሪዎች ሃሳባቸውን እንዲያካፍሉ እድል የሚሰጥ ነበር። ነገር ግን ዩናይትድ ስቴትስ እና ቻይናን ጨምሮ የዓለማችን ከፍተኛ የካርበን አመንጪ ሀገራት መሪዎች አልተሳተፉበትም ነበር። በጉባኤው ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድረጅ ዋና ጸሐፊ አቶ አንቶኒዮ  ጉተሬዝ ሀገራት እ.አ.አ በ2030 የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀትን በ45 በመቶ ለመቀነስ እና እ.አ.አ በ2050 ከካርቦን ልቀት ነጻ የሆነ ደረጃ ላይ ለመድረስ እቅድ እንዲያቀርቡ ጠይቀው ነበር።

እ.አ.አ በታኅሳስ 2019- በማድሪድ (ስፔን) ውስጥ በ COP25 የእድገት እጥረት

COP25 በዋና ዋና የአየር ንብረት ጉዳዮች ላይ ለአመታት ሳይንቲስቶች ከባድ ማስጠንቀቂያዎች ቢያቀርቡም የሙቀት ማዕበልን ያስመዘገቡ እና እርምጃ የሚጠይቁ የአለም አቀፍ ተቃውሞዎች ቢኖሩም በዋና ዋና የአየር ንብረት ጉዳዮች ላይ መሻሻል አሳይቷል ። ተደራዳሪዎች ለአለም አቀፍ የካርበን ገበያ ህጎችን ማጠናቀቅ አልቻሉም፣ እናም በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለተጎዱ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የባህር ውሃ መጠን ከፍ ማለት እና ከፍተኛ የአየር ጠባይ ማካካሻ ማድረግ ላይ እስካሁን አልተስማሙም። የኮንፈረንሱ የመጨረሻ መግለጫ ሀገራት በፓሪሱ ስምምነት መሰረት የገቡትን የአየር ንብረት ቃል እንዲጨምሩ በግልፅ የሚጠይቅ አይደለም፡ ዋና ጸሃፊ አቶ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ንግግሮችን ላይ ጊዜ በማባከን እድሉን እንዳልተጠቀሙበት  ገልፀው ነበር።

እ.አ.አ የካቲት 2020 - በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ንግግሮች ለሌላ ጊዜ ተላልፈዋል

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኮቪድ-19 በመባል በሚታወቀው አዲስ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት በመጀመርያ እ.አ.አ ለታኅሳስ 2020 የታቀደውን COP26ን እስከ እ.አ.አ 2021 ማራዙም የሚታወቅ ሲሆን ሀገራት በግላስጎው በተካሄደው ጉባኤ በፓሪስ ስምምነት የተቀመጡትን የልቀት ቅነሳ ግቦቻቸውን ያጠናክራሉ ተብሎ ሲተበቅ ነበር። ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት፣ ብዙ ሀገራት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በእጅጉ የሚቀንሱ ብሄራዊ አስገዳጅ በቤት ውስጥ የመቀመጥ ሕግን ሲተገበሩ በዓለም ዙሪያ የበካይ የአየር ንብረት ልቀቶች መቀነስ አሳይተው ነበር። ነገር ግን ባለሙያዎች እንደሚተነብዩት እነዚህ የልቀት መጠኖች መቀነሳቸው፣ መንግስታት ውጤቱን እንዲያሳድጉ ግፊት ሲደረግባቸው እና የሚታገለውን ኢኮኖሚያቸውን ለማዳን ሲሉ የአየር ንብረት ለውጥ የሚገቱ ክንውኖችን ችላ እንዲሉ አድርጓቸው ነበር።

እ.አ.አ በሐምሌ 2021 - ግላስጎው (ስኮትላንድ) ውስጥ ከCOP26 በፊት አገራት ቃል ገብተዋል

የፓሪስ ስምምነት ፈራሚዎችን በአጠቃላይ ወደ 60 በመቶ የሚጠጉ ከአንድ መቶ በላይ ሀገራት የተሻሻሉ NDCs  COP26 በፊት ለማቅረብ ቀነ-ገደቡን ያሟሉ ሲሆን አንዳንድ ከፍተኛ ልቀቶች የበለጠ ትልቅ ዓላማ ያላቸውን ኢላማዎችን ያቀርባሉ። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዩናይትድ ስቴትስ እ.አ.አ በ2005 ከነበረችበት ደረጃ ግማሽ ያህሉን እ.አ.አ በ2030 ልቀት ለመቀነስ እንደምትፈልግ አስታውቀዋል፣ ይህም የፕሬዚዳንት ኦባማ ቁርጠኝነት በእጥፍ ይጨምራል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ቻይና እና ህንድ እ.አ.አ በ2019 በግምት አንድ ሶስተኛውን ለአለም አቀፍ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀቶች አስተዋጾ የሚያደርጉ ሲሆን የመጨረሻውን ቀነ-ገደብ አምልጠዋል። በሚቀጥለው ወር የወጣው ሪፖርት እንደሚተነብየው በሚቀጥሉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ የአለም ሙቀት ከ1.5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ሊደርስ ወይም ሊያልፍ እንደሚችል ይተነብያል።

እ.አ.አ 2021 - 1.5°C ግብ በግላስጎው በCOP26 ተይዟል

የCOP26 ፕሬዝዳንት አሎክ ሻርማ በኮንፈረንሱ ወቅት የተደረጉት ቁርጠኝነት የፓሪስ ስምምነት ሙቀትን ወደ 1.5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ “ሕያው” የመገደብ ግብ ይጠብቃል፣ ነገር ግን የልብ ምቱ ደካማ ነው። የመጨረሻው ስምምነት የግላስጎው የአየር ንብረት ስምምነት ሀገራት የድንጋይ ከሰል አጠቃቀምን እና የቅሪተ አካል ነዳጅ ድጎማዎችን እንዲቀንሱ ይጠይቃል - ሁለቱም ለተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ስምምነት የመጀመሪያዎቹ - እና መንግስታት እ.አ.አ በ 2022 መገባደጃ ላይ የበለጠ ታላቅ የልቀት ቅነሳ ኢላማዎችን እንዲያቀርቡ ያሳስባል። በተጨማሪም ልዑካን በመጨረሻም ለዓለም አቀፍ የካርበን ገበያ ደንቦችን ማዘጋጀት፣ ትናንሽ የሃገሮች ቡድኖች በደን መጨፍጨፍ፣ በሚቴን ልቀት፣ በከሰል ድንጋይ እና በሌሎች ላይ ጉልህ የሆነ የጎን ስምምነቶችን ያደረጉ ሲሆን ነገር ግን ተንታኞች እ.አ.አ ለ 2030 እና ከዚያ በላይ ሀገራት የገቡትን ቃል ቢከተሉም የአለም አማካይ የሙቀት መጠን አሁንም በ 2.1 ° ሴ (3.8°F) ይጨምራል ሲሉ ተንብየዋል።

እ.አ.አ 2022 - በሻርም ኤል ሼክ በ COP27 ኪሳራ እና ጉዳት ላይ ለውጥ

በ COP27 በሻርም ኤል ሼክ፣ ዝርዝሮቹ ሳይወሰኑ ቢቀሩም ድሆች እና ተጋላጭ ሀገራትን በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለሚደርሰው ኪሳራ እና ጉዳት ለማካካስ ፈንድ ለማቋቋም ለመጀመሪያ ጊዜ ተስማምተው ነበር።  እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ የኮንፈረንሱ የመጨረሻ መግለጫ የአለም የገንዘብ ተቋማት የአየር ንብረት ቀውሱን ለመቅረፍ አሰራራቸውን እንዲያሻሽሉ ጥሪ አቅርቧል። ነገር ግን አገሮች ሁሉንም የቅሪተ አካል ነዳጆች አጠቃቀም ለማቆም ቃል አይገቡም፣ እናም እ.አ.አ በ2025 ከፍተኛ የልቀት መጠን ላይ ለመድረስ የቀረበው ግብ ከመግለጫው ተወግዷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አቶ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የቅሪተ አካል ነዳጆችን መጠቀም መቀጠል ለፕላኔታችን "ድርብ ችግር" ማለት ነው ሲሉ በወቅቱ መናገራቸው ይታወሳል።

29 November 2023, 16:13